ልጥፎች

የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ #ምን ሊያሳኩ ይሆን ሚዲያ ላይ ከች ያሉት። #አልገባኝም።

ምስል
  • "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የሚገርመው ከቃለ ምልልሱ ዜናው። «መንግስት የጤና ባለሙያወችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ #በትኩረት እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ ከ EBCጋር በነበራቸው ቆይታ ገለጹ።» "መልከ ጥፋን በሥም ይደግፋ" ዓይነት ዜና። የትኛውም የማህበረሰብ ንቅናቄ የፋክት መልስ ነው የሚሻው። የት ላይ ይሆን በትጋት እዬተሠራበት መሆኑ የተገለጸው? ፍዝዝ ያለ ቃለምልልስ ነው ያዳመጥኩት። ፈጽሞ የጤና ባለሙያወች ሰላማዊ ንቅናቄ የዶር መቅደስ ዳባ፤ የእራሳቸው በኽረ ጉዳይ ስለመሆኑ ሚኒስትሯ አልገለፁም።   #አላስጠጉትም ። ጠያቄዋም በዚህ ዙሪያ ያለችው የለም። ይህ የጤና ባለሙያወች ከራህብ ጋር፤ ከመኖር ዋስትና ጋር፤ ከዘላቂ ተስፋ ጋር የቀረበን #ብሄራዊ #ሰላማዊ ንቅናቄ በዚህ ውሽልሽል ሁነት የሚገኝ የፖለቲካዊ ትርፍ የለም። የጤና ባለሙያወች ፋክት ገብ ጥያቄ በፍጹም #ፕሮፖጋንዳም አያስፈልገውም የዳቦ ጥያቄ ነውና።    ምን አልባት እኔ እምጠረጥረው፤ ንቅናቄው ቆይቶ ሲጠነክር እንደ ተለመደው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ #መፍትሄ እና መንገድ እኔው ነኝ ብለው ሊወጡ ይችሉ ይሆናል። እሱን ልጠብቅ እንጂ ቀጥታ ኃላፊነት ያለው የሚኒስተር መ/ ቤቱ ግን ጉዳዬ አላለውም። ወይንም እንደ ተለመደው የስሻሊዝም ቅኝት ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር አጋብቶ አዲስ ትረካም እጠረጥራለሁኝ።    የሆነ ሆኖ አጭርም ስለሆነ ደግሜ አዳምጫለሁኝ። ምንም #የረባ ፍሬ ነገር የለውም ቃለምልልሱ። 445 ላይክ አለው። የማይገባ ኩነትም ገባኝ የሚል ማህበረሰብ ማግኜቱ ሌላው ግራሞቴ ነው። ጥያቄ ጊዜን፤ ሁኔታን፤ ቦታን አስተውሎ በጊዜ መልስ ካልተሰጠው ሲሞላ ይፈሳል፤ ሲከር ይበጠሳል ይሆናል። ለ...

መረጃ ከመዋለ ንዋይ በላይ ልዩ #አቅም ነው። መረጃ ተቋምም ነው ብቁ መሪ ከሰጠው። ማሸነፍ አህዱ የሚለው ከመረጃ አቅምም #ንጥርነትም ነው። ስለሆነም ይህን ቃለ ምልልስ አቃሎ ማየት አዲስ ገብነትን ያመለክታል።

ምስል
  መረጃ ከመዋለ ንዋይ በላይ ልዩ #አቅም ነው። መረጃ ተቋምም ነው ብቁ መሪ ከሰጠው። ማሸነፍ አህዱ የሚለው ከመረጃ አቅምም #ንጥርነትም ነው። ስለሆነም ይህን ቃለ ምልልስ አቃሎ ማየት አዲስ ገብነትን ያመለክታል።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"   https://www.youtube.com/watch?v=6VsVFjZeDvU «በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የተደረገ ቆይታ -ክፍል 2»   እንዴት አደርን ማህበረ - ቅንነት?   ክፍል ሁለት ትናንት ማምሻ ላይ ነበር የተለቀቀው። እኔ ያዳመጥኩት ዛሬ ነው። በነገራችን ላይ ይህ የመጀመሪያ ውይይት የተካሄደበት ስቴዲዮ ቀለሙ የዩቱብ ቻናሌ #ቋሚ ቀለም ነው። እኔ ቀለም ስለምውድ ዩቱብ ቻናሌን ሳዥጎረጉረው ባጅቼ አንድ ቀን ግን ወሰንኩኝ። የቤት ውስጥ ቀለሜም ወደ ዩቱብ ቻናሌ ቀለም ይጠጋል። ይህ ቀለም ወደ 15 ዓመት ይሆነዋል ምርጫዬ ውስጥ ከታደመ እንደማለት። ዩቱብ ቻናሌን #እንድወደው ፤ ተግቼ እንድሰራበት ነው የቢጫ እና የአረንጓዴ ውህድ ቀለምን የወሰንኩት። #ትርጉሙም ይመቸኛል።    ቀለሙም ግጥሜ ነው። የተጠጋጋ ወደ ዓመት ለሚሆን ጊዜ ለቴስት፤ #ውሳኔየ ወደ 8 ወር አስቆጥሯል ለዩቱብ ቻናሌ ቋሚ ቀለም ሲሆን። ትናንት Eurovision Song Contest የ2025 በሲዊዝ ባዝል ከተማ ላይ ሥርዓቱ ሲከፈት ከነበሩት ሞደሬተሮች፤ አንዷ ሞደሬተርም የክብር ልብስ ምርጫዋ ይህ ቀለም ነበር። ቀለሜን ስላገኜሁም ይመስለኛል ጓጉቼ ያደመጥኩት ልበል ይሆን? ክፍል ሁለትንም ሁለት ጊዜ አዳመጥኩት።   ይህ ቃለ ምልልስ ከህወሃት እጮኝነት ተስፋ ጋር እንዳይቆራረጡ ጭራሽ አጀንዳቸው ያልሆነ ሚዲያወች አይቻለሁኝ። ...

የታሰሩ ጋዜጠኞችን በሚመለከት ልዩ መንፈሳዊ አጽናኝ ስጦታ ከባቲካን ተደመጠ። CPJ አጋዥ እዮር ላከለት። የልብ የሆነ ቅድስና።

ምስል
  የታሰሩ ጋዜጠኞችን በሚመለከት ልዩ መንፈሳዊ አጽናኝ ስጦታ ከባቲካን ተደመጠ። CPJ አጋዥ እዮር ላከለት። የልብ የሆነ ቅድስና። https://www.bbc.com/amharic/articles/czr87edg0neo «አዲሱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በእስር ላይ ያሉ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ»   13 ግንቦት 2025, 07:22 EAT   «አዲሱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ ቫቲካን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር በተገናኙበት ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ ጥሪ አቀረቡ።»   «ጳጳሱ "እውነትን ፈልገው ለመዘገብ" ሲሉ ለእስር ለተዳረጉ ጋዜጠኞች ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽ፣ የሚደርስባቸው ስቃይ "የአገራትን እና የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ህሊና የሚፈትን ነው" ብለዋል።»   «የፕሬስ ነጻነት መጠበቅ አለበት ያሉት ፖፕ ሊዮ 14ኛ፣ መገናኛ ብዙኃንም ይህ "ውድ የሆነው ስጦታ" የመናገር ነጻነት መጠበቅን ማረጋገጥ አለባቸውም።»   «ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ እንደሚለው ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት 361 ጋዜጠኞች ታስረዋል። ባለፈው ሐሙስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ ሆነው የተመረጡት ሊቀ ጳጳስ ጨምረውም ጋዜጠኞች በዓለም ላይ ያሉት ኢፍትሃዊነት እና ድህነት ትኩረት እንዲያገኙ ሚናቸውን እንዲእጡ ጥሪ እርበዋል።»   «መገናኛ ብዙኃን በሚከፋፍሉ ወገንተኛ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከማተኮር ይልቅ እውነትን በመዘገብ "ለጽንፈኝነት እና ጥላቻ" መድረክ እንዳይሰጡ አሳስበዋል።»   "መልዕክታችንን የምናስተላለፍበት መንገድ በመሠረታዊነት ወሳኝ ነው፤ የቃላት እና የምሥሎች ጦርነትን ባለመቀበል፣ የጦርነት አቅጣጫን መቃወም አለብን።"   "ኃይል እና ጩ...

#ሁለት ጊዜ የተደመጠ #ዕድለኛ ቃለምልልስ።

ምስል
  #ሁለት ጊዜ የተደመጠ #ዕድለኛ ቃለምልልስ። https://www.youtube.com/watch?v=fl_dSegYcYg&t=392s   "በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የተደረገ ቆይታ -ክፍል 1"   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም፤ ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"   እንዴት ናችሁ ቤተ ቅንነት። ደህና ናችሁን?   ህወሃት ተሰረዘ፤ ህወሃት #ቀጠነ ፤ ህወሃት #ወደለ ፤ ህወሃት ነፍሱ ከሥጋው ተለየችም በውነቱ የእኔ አጀንዳ አይደለም። #ተጠቃሚ የነበሩት ሰርክ ይወዝወዙለት። አይደለም የህወሃት መስለሉ - #መሰልሰሉ ፤ ጎልቶ ቢወጣ በለስ ቀንቶት አልደነቅበትም። ለምን?? የምፈልገውን ፍላጎቴን ጸጥ ባለ ዊዝደም ገብ ሂደት ሥልጣኑን ፈቅዶ እና ወዶ ከማዕከላዊ መንግሥት ገዢነነት ተሰናብቷል። እራሱም ድምጽ ሰጥቶ። ለዚህም ነው ሙሉ ፯ ዓመት ጸጥ ብዬ እምከታተለው። ከሚወቅሱትም ሆነ፦ ተስፋ አድርገው ምልሰቱን ከሚመኙትም፤ ከሚሞግቱለትም ወገን አልነበርኩም።    ህወሃትን በዘመነ #ጋሜዬ ገና ጩጬ ሳለሁ፤ በፖለቲካ ሆነ በዕድሜ የማውቀው ድርጅት ነው። ሻብያንም እንዲሁ። የሆነ ሆኖ ያን "የቆጡን አወርድ ብላ" እንደሚባለው #መታበዩ መራራ ስንብቱን አጎናጽፎታል። "አልጠግብ ባይ" ምን ሲል ያድራል እንደሚባለው። ዕድሜ #ለሃምሌ ፭ቱ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ክስተት ማብቃቱን ዓውጆልናል። በሌላ በኩል መቼወንም ዘመን ህወሃት አውራ የዞግ ፓርቲ ሆኖ #ራሱን ችሎ እንደማይመጣም እርግጠኛ ነኝ። ስለሆነም ቅንጣት አቅም አላዋጣም።    ህወሃት ከሌላ ተቋም እራስ ሊወረድ ግን ይገባል። #መክሰስም ፦ #መወንጀልም ካለበት ትዕቢተኛውን የወቅቱን የትግራይ ክልል መስተዳድር የ...