ልጥፎች

ከቢቢሲ BBC አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። ረሃብን ማሰር?

ምስል
  ከቢቢሲ አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው። ረሃብን ማሰር?   • ከቢቢሲ አሁን ያገኜሁት መረጃ ነው።       https://www.bbc.com/amharic/articles/cn8zxd33d0xo «አንድ ሱዳናዊ ሐኪምን ጨምሮ ከ80 በላይ የጤና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ» «ከሰሞነኛው የጤና ባለሙያዎች ከፊል የሥራ ማቆም አድማ ጋር በተያያዘ በመላው አገሪቱ ከ80 በላይ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸውን የንቅናቄው አስተባባሪዎች አመለከቱ።   የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተለይም በትላልቅ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያገለግሉ በርካታ የጤና ባለሙያዎችን እያሰሩ እና እያወከቡ መሆኑን አንድ የንቅናቄው አስተባባሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።   ከጎንደር ዩኒቨርስቲ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ከተወሰዱት የሕክምና ባለሙያዎች መካከል አንድ ሱዳናዊ ሐኪም መኖሩን ባልደረቦቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል።    "ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ ላብራቶሪ ባለሙያዎችን" ጨምሮ በርካታ የጤና ባለሙያዎች ለወከባ፣ ለድብደባ እና ለእስራት እንደተዳረጉ ገልፀዋል። የንቅናቄው አስተባባሪዎች ባሰባሰቡት መረጃ መሠረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ባለሙያዎች መካከል ዘጠኙ ሴት የጤና ባለሙያዎች ናቸው። 'የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ' በሚል ስያሜ የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄን ጨምሮ የጤና ሥርዓቱን ያስተካክላሉ ያሏቸው 12 ጥያቄዎችን ያነሱ ባለሙያዎች፤ ከግንቦት 5/2017 ዓ.ም. ጀምሮ የከፊል የሥራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ገልፀዋል።   ከዚሁ አድማ ጋር በተያያዘ አዲስ አበባ የሚገኙትን ጥቁር አንበሳ እና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በርካታ የጤና ባለሙያዎች ከሆስፒታል እና ከቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች እየተወ...

የኢትዮጵያ ሃኪሞች ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ #ቀይ #የደም #ሴል ጥያቄ ሊታይ ይገባል። #የፖሊሲ አዲስ ጥሪም አለበት።

ምስል
  የኢትዮጵያ ሃኪሞች ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ #ቀይ #የደም #ሴል ጥያቄ ሊታይ ይገባል። #የፖሊሲ አዲስ ጥሪም አለበት። ህክምና ሁልጊዜ #በአስቸኳይ ጊዜ ውስጥ ነው።    " ሥራውን ሁሉ የሚያስገኝ እርሱ ጥበብን አስተምሮኛልና የተገለጸውንና የተሠወረውን ሁሉ አወቅሁ።" (መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ፯ ቁጥር ፳፩)     ብልህነት ቢኖር፤ ለህዝብ ርህርህና ያለው መንፈስ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢኖር፤ ህዝቤ የእኔ #ውስጤ ነው የሚል ፖለቲካ እና ፖለቲከኛ ቢኖር በውነቱ የሃኪሞች ጥያቄ የኢትዮጵያ የቀይ ሴል ጥያቄ ስለሆነ #መሪ አጀንዳ አድርጎ መውሰድ ይገባ ነበር። ህክምና ህንፃ ግንባታ አዬደለም። የሰው ልጅ የትርታ ፋክት እንጂ። የትኛውም የፖለቲካ አቋም፤ ወይንም የፖለቲካ ተቋም እስትንፋሱ የሰው ልጅ ጤንነት ነውና። ይህን በኽረ ጉዳይ #የካድሬ ማሳ ማድረግ አስፈላጊ አይመስለኝም።   ብዙወቹ የብልጽግና ዘመን ሰጥ ካድሬወች፤ በርካታ የግል የሚዲያ ሰራተኞች፤ አክቲቢስቶች እኮ ከአብይዝም ጋር የመጡ ናቸው። አብይዝምን መደገፍ መብት ቢሆንም ተመክሮ፤ ስክነት ሳይሆን እንደ ግል የተሻለ ዕድል ምቾት ላይ ያተኮሩ፤ ወይንም የተጽዕኖ ፈጣሪነት ረሃብተኞች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህም ሆኖ አብይዝምን ስለደገፋ ብቻ ጥልቅ እና ውስብስቡን የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንዲተነትኑ የሚሰጣቸው ዕድል ይገርመኛል።    ፖለቲካ የዳማ፤ የካርታ ጨዋታ አይመስለኝም። ግጥግጦሽም አይመስለኝም። የፖለቲካ ሳይንስነቱ ሆነ ፍልስፍናነቱ እራሱ ያንሰዋል ባይ ነኝ። የመኖር 13ኛው #ፕላኔት ፖለቲካው ስለሆነ። ሌላው ቀርቶ በፖለቲካ ተምሮ የመጨረሻ የዕውቀት ዳር ደርሶ፤ መምህርም ሆኖ ካልሰራበት ይልቅ፤ ሳይማር ግን በመደበኛ በሥርዓቱ፤ በደንቡ፤ በዲስፕሊኑ ...

የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ #ምን ሊያሳኩ ይሆን ሚዲያ ላይ ከች ያሉት። #አልገባኝም።

ምስል
  • "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የሚገርመው ከቃለ ምልልሱ ዜናው። «መንግስት የጤና ባለሙያወችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ #በትኩረት እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስተሯ ዶር. መቅደስ ዳባ ከ EBCጋር በነበራቸው ቆይታ ገለጹ።» "መልከ ጥፋን በሥም ይደግፋ" ዓይነት ዜና። የትኛውም የማህበረሰብ ንቅናቄ የፋክት መልስ ነው የሚሻው። የት ላይ ይሆን በትጋት እዬተሠራበት መሆኑ የተገለጸው? ፍዝዝ ያለ ቃለምልልስ ነው ያዳመጥኩት። ፈጽሞ የጤና ባለሙያወች ሰላማዊ ንቅናቄ የዶር መቅደስ ዳባ፤ የእራሳቸው በኽረ ጉዳይ ስለመሆኑ ሚኒስትሯ አልገለፁም።   #አላስጠጉትም ። ጠያቄዋም በዚህ ዙሪያ ያለችው የለም። ይህ የጤና ባለሙያወች ከራህብ ጋር፤ ከመኖር ዋስትና ጋር፤ ከዘላቂ ተስፋ ጋር የቀረበን #ብሄራዊ #ሰላማዊ ንቅናቄ በዚህ ውሽልሽል ሁነት የሚገኝ የፖለቲካዊ ትርፍ የለም። የጤና ባለሙያወች ፋክት ገብ ጥያቄ በፍጹም #ፕሮፖጋንዳም አያስፈልገውም የዳቦ ጥያቄ ነውና።    ምን አልባት እኔ እምጠረጥረው፤ ንቅናቄው ቆይቶ ሲጠነክር እንደ ተለመደው ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ #መፍትሄ እና መንገድ እኔው ነኝ ብለው ሊወጡ ይችሉ ይሆናል። እሱን ልጠብቅ እንጂ ቀጥታ ኃላፊነት ያለው የሚኒስተር መ/ ቤቱ ግን ጉዳዬ አላለውም። ወይንም እንደ ተለመደው የስሻሊዝም ቅኝት ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር አጋብቶ አዲስ ትረካም እጠረጥራለሁኝ።    የሆነ ሆኖ አጭርም ስለሆነ ደግሜ አዳምጫለሁኝ። ምንም #የረባ ፍሬ ነገር የለውም ቃለምልልሱ። 445 ላይክ አለው። የማይገባ ኩነትም ገባኝ የሚል ማህበረሰብ ማግኜቱ ሌላው ግራሞቴ ነው። ጥያቄ ጊዜን፤ ሁኔታን፤ ቦታን አስተውሎ በጊዜ መልስ ካልተሰጠው ሲሞላ ይፈሳል፤ ሲከር ይበጠሳል ይሆናል። ለ...

መረጃ ከመዋለ ንዋይ በላይ ልዩ #አቅም ነው። መረጃ ተቋምም ነው ብቁ መሪ ከሰጠው። ማሸነፍ አህዱ የሚለው ከመረጃ አቅምም #ንጥርነትም ነው። ስለሆነም ይህን ቃለ ምልልስ አቃሎ ማየት አዲስ ገብነትን ያመለክታል።

ምስል
  መረጃ ከመዋለ ንዋይ በላይ ልዩ #አቅም ነው። መረጃ ተቋምም ነው ብቁ መሪ ከሰጠው። ማሸነፍ አህዱ የሚለው ከመረጃ አቅምም #ንጥርነትም ነው። ስለሆነም ይህን ቃለ ምልልስ አቃሎ ማየት አዲስ ገብነትን ያመለክታል።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"   https://www.youtube.com/watch?v=6VsVFjZeDvU «በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የተደረገ ቆይታ -ክፍል 2»   እንዴት አደርን ማህበረ - ቅንነት?   ክፍል ሁለት ትናንት ማምሻ ላይ ነበር የተለቀቀው። እኔ ያዳመጥኩት ዛሬ ነው። በነገራችን ላይ ይህ የመጀመሪያ ውይይት የተካሄደበት ስቴዲዮ ቀለሙ የዩቱብ ቻናሌ #ቋሚ ቀለም ነው። እኔ ቀለም ስለምውድ ዩቱብ ቻናሌን ሳዥጎረጉረው ባጅቼ አንድ ቀን ግን ወሰንኩኝ። የቤት ውስጥ ቀለሜም ወደ ዩቱብ ቻናሌ ቀለም ይጠጋል። ይህ ቀለም ወደ 15 ዓመት ይሆነዋል ምርጫዬ ውስጥ ከታደመ እንደማለት። ዩቱብ ቻናሌን #እንድወደው ፤ ተግቼ እንድሰራበት ነው የቢጫ እና የአረንጓዴ ውህድ ቀለምን የወሰንኩት። #ትርጉሙም ይመቸኛል።    ቀለሙም ግጥሜ ነው። የተጠጋጋ ወደ ዓመት ለሚሆን ጊዜ ለቴስት፤ #ውሳኔየ ወደ 8 ወር አስቆጥሯል ለዩቱብ ቻናሌ ቋሚ ቀለም ሲሆን። ትናንት Eurovision Song Contest የ2025 በሲዊዝ ባዝል ከተማ ላይ ሥርዓቱ ሲከፈት ከነበሩት ሞደሬተሮች፤ አንዷ ሞደሬተርም የክብር ልብስ ምርጫዋ ይህ ቀለም ነበር። ቀለሜን ስላገኜሁም ይመስለኛል ጓጉቼ ያደመጥኩት ልበል ይሆን? ክፍል ሁለትንም ሁለት ጊዜ አዳመጥኩት።   ይህ ቃለ ምልልስ ከህወሃት እጮኝነት ተስፋ ጋር እንዳይቆራረጡ ጭራሽ አጀንዳቸው ያልሆነ ሚዲያወች አይቻለሁኝ። ...