#ዝምታ ቢከበር ምንኛ በታደልን ነበር በኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅም እና አቋም።
#ዝምታ ቢከበር ምንኛ በታደልን ነበር፦ በኢትዮጵያ የፖለቲካ አቅም እና አቋም። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" #ጠብታ ። ለጭካኔ ሴራ ፖለቲከኛው ለአቦይ ስብኃት ነጋ የአልማዝ ጉንጉን አሰርቶ በግል ማክበር መብት ነው። የምስጋና ሴሪሞኔውን አደራጅቶ መምራትም የማይሸሹት ሞጋች ህሊና ከፈቀደ መፈጸም ይቻላል። በሌላ በኩል የህወሃት ዶግማ በመንፈሱ የታተመ ዜጋ ለአቤቱ ህወሃት የወርቅ ሃውልት በይፋ ማሰራትም ሙሉ መብት አለው። ጭካኔን እንደምናወግዘው ሁሉ ጭካኔ ናፈቀኝ ማለትም መብት ነው። በእኔ ላይ የጭካኔን አውራ አምጥቶ ለመጫን መሞከር ግን አይፈቀድም። ይህ ዱላም፤ ዝምተኛ የሆነ ስውር ጭቆና በጫናም ነው። ግፍም ነው። ስለሆነም ……… #መቃብር አይናፍቀኝም። እኔ አዎን እኔ #ጉድጓድ አይናፍቀኝም። #ገደል አይናፍቀኝም። ቤተ - መቃብር አይናፍቀኝም። ሳጥናኤላዊ #ጭካኔ አይናፍቀኝም። #የጥላቻ ማምረቻ ቱቦ አይናፍቀኝም። የዞግ ፖለቲካ ፈላስፋ ሽው አይለኝም። የገዳይ የተሃድሶ ኦፕሬሽን #ካፒቴን አይናፍቀኝም። #የክፋ ሃሳብ አፍላቂ፥ አናጺ እና የጸረ ሰው ሹፌር ትዝ አይለኝም። የሴራ ቸረቸራ ቧንቧ ትዝ አይለኝም። የውድመት መሐንዲስ ትዝ አይለኝም። #ሬሳም አይናፍቀኝም። የጸረ ሰላም ኒዩክለስ አልፈልግም። የጭካኔ ቅሪት አካል የኑዛዜ የምክር አገልግሎትም አይናፍቀኝም። መቼውንም። #በድል ይረሳል ወይንስ ይለመዳል? ልመዱ ብቻ ሳይሆን በትንሳኤውም ሳቁለት¡ ማለፊያ¡ ወሸኔ¡ በሉት እየተባልን ነው። ይህን ርዕስ በዘመነ ህወሃት ደጋግሜ ጽፌበታለሁኝ። የደጉ ዘሃበሻ እና የደጉ ሳተናው ቋሚ አምደኛ በነ...