ልጥፎች

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ)፣

  ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ)፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የበይነ መረብ ጋዜጠኞች ለሆኑት ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት እስማማው እና ዳዊት በጋሻው "ፍትሃዊ" እና "ግልጽ የሆነ" የፍርድ ሂደት እንዲያሠፍኑ ዛሬ ባስተላለፈው መልዕክት ጠየቀ።    አራቱ ጋዜጠኞች በአማራ ክልል በተከሠተው ግጭት ሳቢያ ለሦስት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ መሆናቸውን የገለጠው ተቋሙ፣ ጋዜጠኞቹ የተከሰሱበት የሽብር ወንጀል የሞት ቅጣት ወይም የእድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑን ጠቅሷል።    ተከሳሾቹ ጋዜጠኞች በመጪው ሚያዝያ 23 የክስ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ባለፈው ጥር 28 ቀን ባዋለው ችሎት ማዘዙን ዋዜማ በወቅቱ መዘገቧ አይዘነጋም።   ዋዜማ ራዲዮ February 24, 2026

በአሁኑ ወቅት ዶር ሲሳይ አውግቼው የት ናቸው???

  የፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው #የመታፈናቸው ጉዳይ እጅግ አሳስቦኛል።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ይድረስ ስለ ሰው ልጅ የመኖር መብት ግድ የሚላችሁ ንጹሃን ሁሉ።   ታፋኙ ዶር ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ንጹህ በሆነ ሆኔታ ሙሁሩ #የሰባዓዊ #መብት ሁኔታ ግድ የሚላቸው ናቸው። #አዛኝ እና #አጽናኝ የማይደክሙ ናቸው። የሠሩት ቤት የኦነግ አማጽያን ሲያፈርሱት መልሰው አስተባብረው ያስገነቡታል።   እንዲህ ዓይነት #እናት #አንጀት ፤ #ሩህሩህ ፤ አዛኝ እና አጽናኝ ሰብዕና በእስር ዘመኑን እንዲገፋ መደረጉ አልበቃ ብሎ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠው ተብሎ #አፋኝ አዘጋጅቶ ሌላ ትራጀዲ መሥራት፤ የዲፕሎማሲው መስመር ላቀ፤ አደገ፤ ተመነደገ ለሚል መንግሥት ኢሜጁን እራሱ በራሱ #ያበላሸዋል ። ከሁሉም እግዚአብሄር ያዝናል።   በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያለችበት ወከባ ምርጫው፤ የአገራት ርብርቦሽ እና ጥድፊያ፤ ፍጥጫው አገር ውስጡም ውጩም የሰከነ የፖለቲካ መስመር ይጠይቃል። እንዲህ መንፈስን የሚገምስ አሳዛኝ ትራጀዲ የማስተዋል #ፍቀት እንጂ ብልህነት አይደለም።   አሁን ጭንቀቴ የእኔ መሰወሩ በዘለቄታ #እንዳይቀጥል ፤ አካላቸውን #እንዳያጎድሉት ፤ #አዕምሯቸውን #እንዳያበላሹት ነው። የእያንዳንዱ ያፈኝ ሥነ - ልቦና እንዴት እንደተዋቀረ ይታወቃል። እራስ እግሩ #ጥላቻ ፤ እራስ እግሩ #በቀል እና #ቂም የጠጣን መንፈስ ለማስተካከል ተቋም እራሱ የለም። ህወሃት ያበቀለው የክፋ ሃሳብ ድፍድፍ እንዳለ ነው። ከእነ ሙሉ መዋቅሩ። በዚህ ዙሪያ ምንም አልተሰራም።   ጨካኞችን፤ በቀለኞችን፤ #ሃግ የሚል ተቋም የለም። ያሻቸውን ባሻቸው ልክ እስከፈለጉ ድረስ የክፋ ሃሳብ ሠራዊቶች እንዲፈጽሙ ተፈቅዶላቸ...

#የሃሳብ #ጭስ እና ዓለማችን። #በእኛ ባልሆነ ጊዜ አለመኖራችን ያመሳጠረ ክስተት። #ፈጣሪ አምላክ በካህሊ ሥልጣኑ ለዓለማችን #ሰላም ያውርድ። አሜን።

ምስል
  #የሃሳብ #ጭስ እና ዓለማችን። #በእኛ ባልሆነ ጊዜ አለመኖራችን ያመሳጠረ ክስተት። #ፈጣሪ አምላክ በካህሊ ሥልጣኑ ለዓለማችን #ሰላም ያውርድ። አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውምጽ።"   ግን ሦስት ዕርዕሰ ጉዳይን በአንድ የወግ ገበታ። እችለው ይሆን????   #የ27 /02/2026 የደጓ ቪንተርቱር የጨረቃ ነገር።   ዕለተ አርብ ከውጭ ቆይቼ ወደ ቤቴ ስገባ ሰማይ ማዬት ስለምወድ ዋና በራችን እዬከፈትኩ ሰማይን ተመለከትኩ። #ጨረቃ ወጥታለች። በእስልምና ዕምነት ዘንድ ረመዳን ተናፋቂ ፆም ነው። ፆሙ መጠናቀቁ የሚታወቀው ጨረቃ ከወጣች ነው። አሁን ፆሙ አጭር ጊዜ ላይ እያለ ስለምን ጨረቃ #እንደወጣች በቀን አልገባኝ ስላለ ቲክቶክም፤ ፌስቡኬ ላይም አጋራሁኝ። ጨረቃ ከወጣች ፆሙ ይቀጥላል፤ ወይንስ ይጠናቀቃል? እሱ ግራ ገብቶኝ ነበር ፖስት ያደረኩት።   የሆነ ሆኖ ሰላምሽ #ይባካን ወይንም አይረጋ የተባለችው ዓለማችን ጭስ ውስጥ ናት። በሃሳብ #ጭስ ውስጥ። ወይንም በዚህ ሂደት ዘላቂ ሰላም ይረጋገጣል ይሁን የፋመ ጦርነት ላይ በሁሉም አቅጣጫ ዓለማችን ተወጥራ ትገኛለች። ጦርነት ከማባራት ይልቅ እራሱን እያራባ፤ እራሱን እያሰፋ የዓለም ህዝብ በጦርነት ስጋት ላይ ይገኛል። ፈጣሪ አምላክ የዓለምን ሰላም መርቆ ያጽናልን። አሜን።   #የዕለቱ መሪ ዕርዕስ።    የኢራኑ ቁንጮ የሃይማኖት መሪ በሥጋ እንደተለዩ የዓለማችን በኽረ መሪ ዜና ሆኗል። ከምን ተነስተው የት እንደደረሱ፤ ፍፃሜውን አካቶ BBC ዘግቦታል። ይህን ዜና በብሥራትነት የሚዩት የመኖራቸውን ያህል፤ ይህን ዜና ሲሰሙ የሚደነግጡ፤ የሚያነቡ፤ የሚበሳጩ፤ እንደ ...

ንጉሥ እስከ ሠራዊቱ የተሰለፈበት #ሚስጢራዊ ክስተት።

ምስል
  ንጉሥ እስከ ሠራዊቱ የተሰለፈበት #ሚስጢራዊ ክስተት።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።       #እፍታ ።    እንዴት አመሻችሁ ማህበረ ቅንነት። የተፎካካሪ፤ የተደማሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የፋና መድረክ የምዕራፍ ፩ የማጠቃለያ ቁጭት ፎቶ ይህን ይመስል ነበር። ስክሪን ላይ ያነሳሁት ነው።   ይህ ቃለ ምልልስ ከተካሄዴ በኋላ በርካታ ኢትዮጵውያን የግል አስተያዬታቸውን በአጭርም፤ በረጅምም፤ በቁጣም፤ በተግሳጽም፤ በክብርብርም - በኩሰትም፤ በቁጭትም - በተስፋ ምልዓትም የኢትዮጵያ የፖለቲካ መንፈስ ጥሩ አድርርጎ አገላብጥ ሲገመግመው ሰነባብቷል። በመጀመሪያ ላይ ይህን ያህል ይሆናል ተብሎ አልነበረም።    የሆነ ሆኖ የብልጽግና ሁነኛ የሚባሉ አክቲቢስቶች፤ ሚዲያወችም ያልጠበቅኩት #አወንታዊ ዕይታ የሰጡትን አዳምጫለሁኝ፤ ጹሁፋንም አንብቤያለሁኝ። ብልፄው ለምን ተደፈረ ያሉም ፊት ለፊት ወጥተው ሲሞግቱ አይቻለሁኝ። ጥሩ ነው። አስደሳችም ነው።    ወጣቶች በራሳቸው የዘመን ፖለቲካ በዚህን ያህል ፍጥነት ግሎባል ንቅናቄ መፍጠር ለቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ምርጫው እኔንም ይመለከተኛል የሚል ጤናማ ዕድምታ ይፈጥራል። አክሰሱ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችም ነገም እኔ እንዲህ ብሆን የሚል ስሜት ሊያድርባቸው ይችላል።    ስለሆነም እኔ ከጠበቅኩት በላይ የተሳትፎ ህብራዊነት በትጋት እና በተከታታይነት ስለየሁ አወንታዊ ስሜት ውስጤ ተመግቧል። በብልጽግና የፖለቲካ ፓርቲ መሪ አካላት እኔን የተሰማኝ ያህል ሊሰማቸው ላይችል ይሆናል። አገር ነገ ለሚሉ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ግን የወጣቶቻችን ሙሉ ተሳትፎ አበረታች ነው።   በሌላ በኩል የለት ዕ...

Par two, ብርድብርድ ያለው የትናንት የፋና የ2018 የምርጫ መድረክ የቤተ - ዳዊት መወደሪያ ምሽት።

  ብርድብርድ ያለው የትናንት የፋና የ2018 የምርጫ መድረክ የቤተ - ዳዊት መወደሪያ ምሽት።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።   #ጠብታ ።   ሴት የፖለቲካ ሊቃናት የፖለቲካ ውክልና አጡ ብዬ ስሞግት ኖሬ፤ ዕድሉ ሲገኝ እንዲህ እና እንዲያ ማለት ስለሚፈትነኝ እንዲህ ካልበዛ በስተቀር እንዳላየሁ አይቼ የማልፋቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ። የሆነ ሆኖ ያን ግዙፍ ተቋም የሚመሩ የፍትህ ሚር ትናት በነበራቸው የብልጽግና ፓርቲ ወካይ የሙግት ቆይታ የብልጽግና አቅም እጅግ #ፈተና ውስጥ ገብቶ ነበር ማለት ይቻላል። እንደ አለፈው ጊዜ በዕለቱ የማያፈናፍኑ ንቁ እና ትጉህ ሞጋቾች ቢኖሩ ምን ይበጃቸው እንደነበር አላውቅም።   ባለፈው ጊዜም ቢሆን ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ በጣም የቅርብ ሚር የሆኑት፤ በወሳኝ የጠቅላይ ሚሩ ልዑካዊ ጉዟቸው የማይለዩ፤ ለግሎባል መሰናዶ ተመራጭ የሆኑት፤ በዘመነ አብይዝም የመጀመሪያው የካቢኔ አወቃቀር ላይ የነበሩት ቁጥር ፩፤ በሲነሪቲ ደረጃ መቅድም የሆኑት ዶር ፍጹም አሰፋም እንኳን ከፋክት፤ ከጭብጥ ይልቅ #ፕርፖጋንዳዊ ሁነቶች ላይ ነበር ያተኮሩት። ይህም ቢሆን ይሻላል ከትናንቱ ብርድ ብርድ ከአለው የፋና የትናንት መድረክ።   እርግጥ ነው በዚህ የሙግት መድረክ ዕቅዳችሁ ምንድን ነው። የዕቅዳችሁ ፖሊሲ በምን ላይ ያተኩራል፤ ለአፈፃጸሙ ምን ያህል መሰናዶ አላችሁ? በፋይናንስ፤ በሰው ኃይል፤ በመንፈስ፤ በኮኦርድኔሽን ወዘተ ጥያቄው ይህ ነው። ቲም ሚር ዶር ፍጹም አሰፋ ግን ባለፋት የመምስት ዓመታት ክንውን ዘገባ አቅራቢ ነበር የሆኑት።   ለነገሩ የብልጽግና ፓርቲ ሁለቱ ምክትል ፕሬዚዳንቶችም ማኒፌስቶ ለቀጣይ፤ ትልም ለቀጣይ፤ ራዕይ ለቀጣይ ሲጠየቁ ማኒፌ...