ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ)፣

 

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ)፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት የበይነ መረብ ጋዜጠኞች ለሆኑት ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት እስማማው እና ዳዊት በጋሻው "ፍትሃዊ" እና "ግልጽ የሆነ" የፍርድ ሂደት እንዲያሠፍኑ ዛሬ ባስተላለፈው መልዕክት ጠየቀ። 
 
አራቱ ጋዜጠኞች በአማራ ክልል በተከሠተው ግጭት ሳቢያ ለሦስት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ መሆናቸውን የገለጠው ተቋሙ፣ ጋዜጠኞቹ የተከሰሱበት የሽብር ወንጀል የሞት ቅጣት ወይም የእድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑን ጠቅሷል። 
 
ተከሳሾቹ ጋዜጠኞች በመጪው ሚያዝያ 23 የክስ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ባለፈው ጥር 28 ቀን ባዋለው ችሎት ማዘዙን ዋዜማ በወቅቱ መዘገቧ አይዘነጋም።
 
ዋዜማ ራዲዮ
February 24, 2026

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።