ፕሮፌሰሩ ዶር ሲሳይ አውግቸው #በእስር እየተንገላቱ ነው።

 

ፕሮፌሰሩ ዶር ሲሳይ አውግቸው #በእስር እየተንገላቱ ነው።
 
እኒህ የኢትዮጵያ ሊቅ፤ በበዛ #ጭምትነት፤ በውስጥ #መረጋጋት፤ በሰላማዊ የአኗኗር ዘይቤ የሚታወቁ ሙሁር ለካቴና ተዳርገው አሳራቸውን ሲዩ ባጅተዋል። አሁን ደግሞ ፍርድ ቤት ወሰነ ከተባለ በኋላ ታቅዶ በሚከወን #ትራጀዲ ሌላ አሳዛኝ ድርጊት መፈጸሙን እየሰማሁ ነው። 
 
ዶር ሲሳይ #በሰባዊ ተግባራት ላይ ተሰማርተው የነበሩ ናቸው። እኔ አበክሬ ስከታተላቸው ነበር። ምርጫ በመጣ ቁጥር እንደበቆሎ ሰርክ የእሳት እራት የሚሆኑት የአጣዬ፤ ሽዋሮቢት፤ ኤፍራታ ለደረሰው መከራ የቅርብ #ረዳት#አጽናኝ #ትጉህ#አይዟችሁ ባይም ነበሩ።
በነገራችን ላይ ኤፍራታ ላይ ሰሞኑን ብዙ ስቃይ አለ። ይህ የሆነበት ሁለት ምክንያት ነው።
 
1) የጭንቀቱ ሙቀት አዲስ አበባን እንዲያሞቅ፤ ለምርጫ የጭንቅ ቀውስ ይታጫል፤ በምርጫ ሰሞን ቀኑ ሲቃረብ ጸጥ ይላል። በሰላም ምርጫው ተካሄደ ይባላል። የሚገርመኝ ብልጽግናን ለመመረጥ የሚያሰጋው ምንም ነገር የለም። 50+ ድምጽ ምንም ሳይጨናነቅ ያገኛል። ይህንን እኔ መዝኜዋለሁኝ። የማይችልባቸው ቦታወች ጥቂቶች ናቸው። ግን አመል ስላለበት መከራ #ያስቀጥላል። 
 
2) የማህበረ #ኦነግ ፍላጎት #ሽዋን #መጠቅለል ስለሆነ ይህንኑ ለማሳካት ታቅዶ የሚከወን ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያን ጠቅልለው እየመሩ ስለምን ይህን እንደሚያስቡ ፈጽሞ አይገባኝም። በውነቱ እንዲገባኝም #አልፈቅድም
 
በአጋጣሚ ዶር ሲሳይ #የስሜን ሽዋ ሰው ናቸው። የእሳቸው ትጋት ከ10 ጊዜ በላይ ለተቃጠለችው አጣዬ እና አካባቢው ማህበረሰብ፤ መጠለያ ላጡት ጊዚያዊ መጠለያ አሰርተው ከመርዳት፤ በተለይ #ለልጆች ሰፊ እንክብካቤ ከማድረግ፤ መኖራቸውን ከተከፋ ወገኖቻቸው ጋር ከመጋራት ውጭ ሌላ ያዬሁት የለም።
 
ለእኒህ ሩህሩህ፤ የመንግሥትን #ኃላፊነት እና #ተጠያቂነትን ሳይጠብቁ በራሳቸው ተነሳሽነት የተጎዱ ወገኖቻችን በማገዝ የግንባር ቀደም ተሰላፊ መሆናቸው #በበጎ ሰው ሊስት በክብር ተቀመጥው፤ ሊመሰገኑ ሲገባ፤ ባለፈም ሊሸለሙ ሲገባ፤ እንዲህ ዓይነት የእስር ችግር እንግልት ሊደርስባቸው አይገባም ነበር።
 
የብልጽግና መንግስት በህወሃት ሊቃናት #ቁልፍ ቦታወችን አስረክቦ፤ ለማህበረ ኦነግም ሜዳውም ፈረሱም ብሎ፤ ንጹሃን የአማራ ሊቃናት ድርብ ችግር፤ እጥፍ መከራ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። እኒህ ቅን፤ በችግር #ደራሽ ሊቀ ሊቃውንት ወንጀላቸው #አማራ መሆናችው ካልሆነ በስተቀር ትጋታቸው በገፍ የሚፈናቀለውን ማህበረሰብ ከመርዳት ውጪ #ሰሃ የለባቸውም።
 
እኔ እንደማስበው በቀለኞች ከነበሩበት እስር ቤት የፈለጉትን ማድረግ ስላልቻሉ፤ በፍርድ ቤት እንዲለቀቁ አድርገው ያቀዱትን #በቀል ለመፈጸም ታስቦ ይሆናል። #ሊሠውሯቸውም ይችላል።
 
ከላይ እስከታች #የህወሃት መዋቅር ነው የቀጠለው። ይህ ግፍ እራሱንም ብልጽግና ተስፋዬ፤ እራዬ፤ ዕቅዴ፤ ግቤ እያለ የሚናገረውን ሳይፈጽም ሊቀር ይችላል። ሰውን ማሰር፤ መሰወር፤ መግደል ይቻላል። እግዚአብሄርን ቁጣ እና እርምጃ ግን አይቻልም። የመዳህኒዓለም ቁጣ የመጣ ዕለት #ወዮ! ነው።
 
ኢትዮጵያ ቅጥ መጠን ባጣ ውጥረት ውስጥ ስለሆነች ብዙ አመክንዮችን አስታግሶ የያዝ በግራ በቀኝ ለተሰለፋባት ተቀናቃኞቿ #እንዳይመቻቸው ለማድረግ፤ ብዙውን አመክንዮ #ጨምት እየተባለ ቢቀጣም፤ ብልጽግና ግን #ይሉኝታ ቢስ ስለሆነ እንሆ ንጹኃንን በተለይ ጭምቱን ማህበረሰብ ከማስከፋት ተቆጥቦ አያውቅም። ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል።
 
ውዶቼ እንዴት አመሻችሁልኝ። በጣም ያሳዘነኝ ዜና ነው።
 
ሥርጉትሻ26/02/2026
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው በዋስ ተለቅቀው እየወጡ ሳለ "በቁጥጥር ስር መዋላቸውን" ጠበቃቸው ተናገሩ - BBC News አማርኛ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።