በአሁኑ ወቅት ዶር ሲሳይ አውግቼው የት ናቸው???
የፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው #የመታፈናቸው ጉዳይ እጅግ አሳስቦኛል።
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
#ይድረስ ስለ ሰው ልጅ የመኖር መብት ግድ የሚላችሁ ንጹሃን ሁሉ።
ታፋኙ ዶር ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ንጹህ በሆነ ሆኔታ ሙሁሩ #የሰባዓዊ #መብት ሁኔታ ግድ የሚላቸው ናቸው። #አዛኝ እና #አጽናኝ የማይደክሙ ናቸው። የሠሩት ቤት የኦነግ አማጽያን ሲያፈርሱት መልሰው አስተባብረው ያስገነቡታል።
እንዲህ ዓይነት #እናት #አንጀት፤ #ሩህሩህ፤ አዛኝ እና አጽናኝ ሰብዕና በእስር ዘመኑን እንዲገፋ መደረጉ አልበቃ ብሎ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠው ተብሎ #አፋኝ አዘጋጅቶ ሌላ ትራጀዲ መሥራት፤ የዲፕሎማሲው መስመር ላቀ፤ አደገ፤ ተመነደገ ለሚል መንግሥት ኢሜጁን እራሱ በራሱ #ያበላሸዋል። ከሁሉም እግዚአብሄር ያዝናል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያለችበት ወከባ ምርጫው፤ የአገራት ርብርቦሽ እና ጥድፊያ፤ ፍጥጫው አገር ውስጡም ውጩም የሰከነ የፖለቲካ መስመር ይጠይቃል። እንዲህ መንፈስን የሚገምስ አሳዛኝ ትራጀዲ የማስተዋል #ፍቀት እንጂ ብልህነት አይደለም።
አሁን ጭንቀቴ የእኔ መሰወሩ በዘለቄታ #እንዳይቀጥል፤ አካላቸውን #እንዳያጎድሉት፤ #አዕምሯቸውን #እንዳያበላሹት ነው። የእያንዳንዱ ያፈኝ ሥነ - ልቦና እንዴት እንደተዋቀረ ይታወቃል። እራስ እግሩ #ጥላቻ፤ እራስ እግሩ #በቀል እና #ቂም የጠጣን መንፈስ ለማስተካከል ተቋም እራሱ የለም። ህወሃት ያበቀለው የክፋ ሃሳብ ድፍድፍ እንዳለ ነው። ከእነ ሙሉ መዋቅሩ። በዚህ ዙሪያ ምንም አልተሰራም።
ጨካኞችን፤ በቀለኞችን፤ #ሃግ የሚል ተቋም የለም። ያሻቸውን ባሻቸው ልክ እስከፈለጉ ድረስ የክፋ ሃሳብ ሠራዊቶች እንዲፈጽሙ ተፈቅዶላቸዋል። ክፋ ሃሳብን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ፰ ዓመት በጣም ብዙ ነው። ዕድሉን አብይዝም አፍሶታል። ይህ ወያኔ ወያኔ የሚሸተው የጭካኔ #ትራጀዲ ጠረን እጅግ አሳሳቢ ነው። የህዝብን መንፈስ ማወክ፤ መረባበሽ ምን ፖለቲካው ትርፍ ሊያስገኝም፤ ሊጠቅም እንደሚችል አላውቅም።
በአሁኑ ወቅት ዶር ሲሳይ አውግቼው የት ናቸው???
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ቸር ያሰማን። አሜን።
ሥርጉትሻ 27/02/2026
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ