ዋግሹም ኃይሉ ከበደ ልጅ ኢዪኤል እንደከተበው!

 

ከአቶ ብሩክ ፔጅ ነው ያገኜሁት። የተገጠመላቸውን እሜቴ ወይዘሮ እምላት ውዴ ልጇን አይታ ከሄደች በኋላ አስባ ላከችልኝ። የዋግሹሞች ጉዳይ ዝንባሌም የውስጥም የሆነ መነሳሳት ስላለኝ። አስባ ላከችልኝ። 
 
ዋግሹም ወሰን ኃይሉ የግራዝማች ፈንታ ኃይሉ ወንድም ናቸው። የግራዝማች ፈንታ ኃይሉ ልጅ እሙኃይ አሰለፈች ፈንታ ትባል ነበር። እሷ ሁለት ወንድ ልጆች ነበሯት። አንዱ ወንድ ልጇ የእኔ ወላጅ አባት ነው። የወንድሜ ሥም እራሱ ኃይሉ ነበር የሚባለው። በእሳቸው ሥም ነበር የሚጠራው። የሆነ ሆኖ ሁለት ዋግሹም ወሰን ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም።
 
እና እሜቴ ወይዘሮ ይህን ታሪክ ስላጫወትኳት ነበር ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰች በኋላ ለጀግናውን የተደረሰላቸው ግጥሙን እና ፎቷቸውን አክላ የላከችልኝ። እኔ ደግሞ በተደጋጋሚ ጊዜ በጸጋዬ #ራዲዮ አቅርቤው ነበር። የወጣላቸው ዓራት ዓይናማ ጀግና ናቸው።
አንድ ነገር ግን ዋግሹም ወሰን ኃይሉ ልጃቸው በህይወት አሉን? ይህ እራሱ ደስ የሚል ዜና ነው።
 
 May be an image of text
 
*******////***********
👑🤴 "ዘውድ ያልጫነው ንጉሥ"🤴
👑
"በማይጨው ጦርነት ቢቆስል አንገቱ፤
እስከ ደም ጠብታ ነው የቃል ትንቢቱ።"
 
"እየተባለ የተቀኘላቸውና በሁለተኛው የጣልያን ጦርነት ላይም አንገታቸውን የቆሰሉትም፣ አንገታቸውን የተቀሉትም፤ታላቁና
ውዱ ባለውለታችን ዋግሹም ኃይሉ ከበደ፤ጣልያን ከእምዬ ምኒልክ ቀጥሎ እጅጉን የሚፈራቸውና የሚሰጋላቸው ታላቅ አርበኛችንና #ሰመዓታችን ናቸው።
 
እምዬ ምኒሊክ አፈር ከድሜ አብልተውና፣በዓለም ፊትም አሳፍረውና አዋርደው ያባረሯቸው፤ የምንግዜም ተሸናፊዎቻችን ጣልያኖቹ፤ያንን ስማቸውን ለማደስና እኛንም ለመበቀል ዳግም ወደኛ እጅጉን ታጥቀው ሲመለሱ፤ዋግ ሹም ኃይሉ ከበደ ነበር ድንገት ከጓዶቻቸው ጋር አድፍጠው የጠበቋቸው።
 
እምዬ አሳፍረው እንዳባረሯቸው ዋግሹምኃይሉ ከበደ ደሞ
በተራቸው እንደ ቅጠል ሊያረግፏቸው አፍጥጠውና ተኮሳትረው ጠበቋቸው።
 
ዋግሹም ኃይሉ ከበደ በጦርነቱ ላይ፣ባለቤታቸው ወሮ "ሸዋነሽ" አብርሀንና፣ልጃቸው"ወሰን ኃይሉንም" ይዘውና አሰልፈው ከነ መላ ቤተሰባቸው ነበር ከተው ጣልያንን ሲያስጨንቁና ሲቆሉት የነበረው።በጦርነቱም እጅግ በጣም ብዙ መሳሪያና የነጣ ወታደር ሊማርኩ ችለዋል።ብቻ ምን አለፋችሁ በ5 ዓመቱ ንጉሡ ባልነበሩበት ዘመን፣ዘውድ ያልጫነው ነገር ግን ጣልያኖች እንደ ንጉሥ የሚያዩትና የሚፈሩት መስፍን ዋግሹም ኃይሉ ከበደ ነበሩ።
 
ዋግሹም ኃይሉ ከጠላት በተተኮሰ ጥይት ተመተው ድንገት ቢያርፉም፤ጣልያኖቹ ግን ካለባቸው ስጋትና ፍርሀት የተነሳ
 
አንገታቸውን ቆርጠው ወደ ሮም በመውሰድ ለንጉሣቸው
ሰተዋል።ጋዜጦቻቸውም የፌት ገፃቸው ላይ በማውጣት
 
ሲያስጨንቃቸው የነበረውንና ዘውድ ያልጫነውን ንጉሥ ዋግሹም ኃይሉ ከበን ይዘንላችሁ መተናል እያሉ ማውጣት ጀመሩ።መላው ጣልያን ሲደሰትና ሲጨፍር ዋለ። በኛ ሰማይ ስር ግን ታላቁነሰ ባለውለታችንን በማጣታችን የተነሳ የሀዘን ሰማይ አጠላብን።
 
እውነቴን ነው የምላችሁ ዋግሹም ኃይሉ ከበደ የከፈሉልንን
የህይወት ሰመአትነትና ውለታ በምንም ተክተን አንከፍለውም።
እስቲ የልጅ ልጃቸውን ዋግሹም ዶ/ር "ሚካኤል ወሰንን"
የአድዋን የድለሸ በዓል አስመልክተው እንኳን አደረሳችሁ
እንዲሉንና እንደ ታላቅ የአርበኛ ልጅነታቸው መልክታቸውንም
እንዲያስተላልፉልን ልጋብዛቸው?ምን ትላላችሁ ታዲያ??
የሳቸው ሀሳብና አስተያየት ምክር አያስፈልገንም ትላላችሁ?
ለኔ ደሞ የቅርብ ቅርብ ዘመዴና ወዳጄም እንደሆኑ በደንብ ታውቃላችሁ መቼም። ሁሌም ምክራቸውንና አስተያየታቸውን እንደተቀበልኩ ነው። ዛሬ ለሁላችንም መልክታቸውን እንዲያስተላልፉ ነው የምጋብዛቸው!!" 
 
ዋግሹም ዶ/ር "ሚካኤል ወሰን ኃይሉ" እባኮትን ስለ አያቶት
እንዲሁም ስለ ድል በዓላችን የተወሰ ነገር ይበሉን ጋሽዬ??
ክብርና ምስጋና ለኛ ሲሉ ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ጀግኖቻችን!
 
ልጅ ኢዪኤል እንደከተበው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።