ዛሬ የምትሞግትለት ነገ አይገኝም። ጣሪያ ላይ ተንጠልጥሎ የራሱን #ኢንፓዬር ሲያንጽ ነው የሚገኜው።
ፍቅር ሲጨንቀው ይጨንቃል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/02/2022
ኢትዮጵያ ውስጥ ጭካኔ #ደልቧል። #ፋፍቷልም። ጨካኞች እንዲጨክኑ ኢትዮጵያ በጨካኝ መንፈስ እንድትታወክ ሊፈቀድ አይገባም። ፈጽሞ። የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት #መለያ #ዓርማ ጭካኔ እንዲሆን በፍጹም ሊፈቀድ አይገባም።
ኢትዮጵያን ከየትኛውም ጥቃት ተባብረን ልናድናት የምንችለው በኢትዮጵያ ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙትን የጭካኔ ሃሳብ አራማጆችን #ሃግ ባይ ንጹህ ተቋም ሲኖር፤ በተጨማሪም፤ ጨካኞች እንዳይደላቸው ሰዋዊ ህጎችን ሥራ ላይ ለመዋል ሲወሰን፤ ለተግባራዊነቱ አብይዝም #ቁርጠኛ ሲሆን ነው።
በቃን! ጭካኔ። በቃ! መጨካከን። ሰው ከማትረፍ፤ ጓድን ከማዳን ይልቅ አሳልፎ መስጠት መንፈሱ ጲላጦሳዊ ነው። #ማዳን ቢያቅት የጭካኔ ማዳበሪያ መሆን #ይሰቀጥጣል። የእኔ ክብሮች የኔወቹ ክፋ ሃሳብ እና ማህበርተኞቹን ቢያንስ #ሃግ እንበላቸው።
ሥርጉትሻ 27/02/2026
ከሥርጉትሻ ቤት የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ መሪ ሊሆን ይችላል፤ ስድብ፤ ዘለፋ፤ ንቀት፤ በፎቶ ላይ ኤክስ ማድረግ፤ ፎቶ መዘቅዘቅ፤ የሰውን ልጅ እንሰሳዊ አድርጎ በፎቶ ሾፕ መስራት፤ ፆታዊ ያልተገቡ ቃላት፤ እያሉን ግን ነውረኛ የሆኑ ቃላት ልንጠቀምባቸው የማይገቡ ለምሳሌ "ጋለሞታ" ወዘተ አይፈቀድም። መራራ ስንብት ይሆናል። ይህ ትውልዱ በትክክለኛ የኢትዮጵያኒዝም ኦርጋኒክ ተፈጥሮ ልክ የሚበጅ ሃሳብ የሚያስተናግድ ፔጅ ነው። ወገንተኝነቱ ለመርህ እና ለፋክት ብቻ።
#ሥርጉትሻ በነጣ አገልጋይ። መልካም ቀን። አሜን።
27/02/2026
ለኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ሰው ልጅ ብልህነት፤ ትጋት፤ ቅን ዕይታ ቢመግባቸውም ከበረሃ ላይ እንደሚዘራ ደገኛ የእህል ዘር ነው የሚያደርጉት። #አይሰሙም። ዋጋ #አይሰጡትም። ሲናዱም ሆነ ሲሸራረፋ ምን ላይ ይሆን #ግድፈቴ ብለው አይመረምሩትም። #መዳንን #ለማዳንም ፈቃደኞች አይደሉም። ስንት በኽረ ጉዳይ እያለ በአንድ ፖለቲከኛ ሰብ ላይ በግራቀኙ የሚጠፋ ጊዜ የጉድ ነው።
ዛሬ የምትሞግትለት ነገ አይገኝም። ጣሪያ ላይ ተንጠልጥሎ የራሱን #ኢንፓዬር ሲያንጽ ነው የሚገኜው። የሆነ መረጃ ኑሮህ ፈልገህ አታገኛቸውም። የሚያሰቡት በዛች በተፈጠሩባት ትንሽዬ ቀበሌ ውስጥ ሆነው ነው። #እና ለራሳቸው ዴሞክራሲን ያልመገቡ ለትውልድ? ሩቅ በጣም ሩቅ ነው። በሌላ በኩል ችግርን እየጨመሩ እንጂ ችግርን እየቀነሱ አይሄዱም። ከቀና መንገድ - ኮረኮንች፤ ከቀላሉ የመፍትሄ ጎዳና #ድጣማ #አቀበት ያሰኛቸዋል። ይህ አገርንም ትውልድንም አያድንም። ፈጽሞ።
ሥርጉትሻ 27/02/2026
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ