የማህበረ አብይ ጉባኤ ... መሪ እና ፕሮቶኮል ሹም።
አንጄትን ቅቤ ያጠጣው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አገላለጽ ነው! „ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፱ ቁጥር ፩) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 31.07.2018 (ከገደማዋቷ ሲዊዘርላንድ) በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰሞናቱ የማህበረ አብይ ጉባኤ የመድረክ አመራር በርካታ ዕይታዎችን አነበብኩኝ። የፕሮተኮል ሹመነትም ተደማሪነትም አለበት። የሆነ ሆኖ ያው በእሱ ዙሪያ እጅግ በርካታ ውዝግቦችን ብራና አስተናግዳለች። እሱን በሚመለከት የተፈለገው ቢባል እኔ በራሴ ውስጥ ነበርኩኝ። የወጣሁት ከእሱ ሰብዕና አልፎ ትዳሩ ላይ ወቀሳ ሲሰነዘር ግን በህግ አምላክ ብያለሁኝ። ጽፌማለሁኝ። በጣም መጠን አልፎ መሄድ አያስፈልግም። ትዳር ላይ የሚወሰድ ምንም ነገር የለም። ትዳር ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው አይደለም። የሰውም የእጅ ሥራ አይደለም የጣና ዘገሊላ ጉዳይ። እንዲያውም የሚስጢሩን ልቅናውን ብናወቀው ሌላ ዘሃ መጎተት ባላስለፈገን ነበር። አገርም በአህቲ መንፈስ ትጸድቅ ነበር። „ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹህ“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ፤ ቢያንስ ይህ የህይወት ቃል አብሶ የተዋህዶ ልጆች ሊያከብሩት ይገባል። ወቃሽ ጸሐፊው የተዋህዶ ልጅ ስለነበሩ። ከዚህ በመለስ አሁን ትልቅ ቦታ ስለተሰጠውም ነው ሊያሰኝ አይችልም 7ኛ መጸሐፌ "ርግብ በር" ላይ መልካም ነገር ስላገኘሁ ሃሳቡን ለማስረጃነት ተጠቅሚያለሁኝ። እኔ ቅንነት ባለበት ቦታ ሁሉ ዳር ደንበር የለኝም። ወደ ጉዳዬ እንብርት ስገባ መቼም ፈታኝ ነው፤ አደባባይ ላይ የተሳታፊን ጥያቄ ማስተናገድ። እኔ አይቼ አላወቅም በሰለጠነው ዓለም። አሁን የሆነው እንደዛ ነበር። ኢትዮጵያ ግን በዛ ሰሞን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ...