ቅጽበት እና ማህበረ ቅጽበቶች ዕዳ እና ዳጦች - የማጥ ሰርጥ።

ብልጫ ድርግም።
„የጽድቄ አምላክ በጠራሁት ጊዜ መለሰልኝ፤
በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፤ ማረኝ ጸሎቴንም ስማ።“
መዝሙር ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ© ሥላሴ 
11.08.2018


ጃዋርን እንመነውን? ሌላ እድል እንስጠውም የሚል ቧልትም አለ። ማለፊያ ነው መሸቢያ። እንዲህ እንደ ሸንብራ ቂጣ ስንገላበጥ በቅጽበት ፖለቲካ ስንተራመስ ትውልድ አሳሩን ያያል። እዳ ድጥ እና ዳጥ፤ ምጥ እና ማጥ! ኢትዮጵያ እኮ አሁን እዬጠፋችን ነው። በፈረስች አገር ነው ሽርጉዱ። ብቻ የሳምንቱ የሚዲያ ጠ/ ሚሮቻችን ደግሞ እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ናቸው። 

ማመንም አለማምንም የራስ ጉዳይ ነው። እኔ ብአዴን አብሶ የአቶ ገዱ መንፈስ ይሄን ያህል በውልቅ የፖለቲካ ቁመና ላይ መሆኑን በፍጹም አላውቅም ነበር። የእውነት በፍጹም።

ጃዋርውያን ሆኖ ጠብ እርግፍ ሲል፤ ያን ያህል ተነጥፎ ደጅ ደጭ ሲል ግርም ይለኛል። እነዚያ የሚዲያ ሽፋን ያላገኙ ተክድነው የተቀመጡ ሊቃናተ - ሊቃውንታት ምን ይታዘቡት ይህን ገማና እላለሁ እኔ ከዚህ ሆኝ። ሰው የራሱ ክብር እኮ አለው። የክብርም ደንበር አለው። ክብር ቀፎ ቀልም የሌለው እስክርቢቶ ማለት አይደልመ። ልክ አለው መጠን።
ለመሆኑ ይህን ያህል ከንቱ ነበርን ብአዴን? ይሄ አማራ መጥላቱን፤ ክርስትናን ማውገዙን አይደለም። ሰብዕናው በራሱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ብልጭ ድርግም ስለሆነ ነው።

እርግጥ ነው እንግዳ መቀበል የተገባ ነው። እሱ የእኔ ባይለንም ሰው ነው። በሰው አምሳል የተፈጠረ ነው። ላያችሁ ፈቀድኩኝ ለፖለቲካዬ ልቅና እና ክብር ስል ሲል የአባት አደሩ ቢደረግለት መልካም ነው። 

ነገ አቶ ንጉሡ ጥላሁንን በ አቶ ደመቀ መኮነን ትክ ም/ ጠ/ ሚር አደርጎ ለሚያሾም የተገባ ነው። ብቻ ብቻ ያ ቆፍጣናው ንጉሦ ጥላሁን ይህን ያህል ግን ከባህርዳር አስነስቶ አቀባባል የሚያስኬድ አንዳችም ነገር አለነበረም። ስለምን አርበኛ ዘመነ ካሴን አቶ ንጉሡ ጥላሁን እዛው ባህርዳር አውሮፕላን ማረፊያ ሄደው አልተቀበሉም፤ ወይንም ዘመን ከቶም ሊተካቸው የማችለውን አቶ ካሳ ከበደን። 

የሆነ ሆኖ አቶ ጀዋር መሃመድ ደፋር ነው። ጥቃት መቀበል አይወድም፤ አለመወድዱ ብቻ ሳይሆን የተጠቃበትን መሰመር መክቶ እኩል ሆኖ ለመውጣት የሚወስደው እርምጃ ያስደስተኛል። አሸንፎ ነው የሚወጣው። ይህን ብቃቱን እወድለታለሁኝ። ደጋግሜም ገልጨዋለሁኝ።

አጀንዳዬ ላደርገው ግን አልሻም። ወቅሼውም አላውቅም። እንዲያውም ትክክለኛ ነገር ሲፈጽም ያነን ነገር ተፃሮ የሚመጣ ሃሳብ እንደ ተለመደው በትርጉም አቃንቼ መልካም ነገር ነው ያደረገው እላለሁኝ።
ከዛ ውጪ እንደ ፈለገ በሚንቦላከባት ሲሰኘው ጭቃ በጭቃ በሚያጨቀዬው፤ ሲሰኛውም በጎርፍ ማዕበል ሊሚያጥለቀልቀው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ልሞግተው ብዬ አላውቅም፤ ደግሞ እናቴ በአራስ ቤቷ አላበደችም።  አቋም ያለው ሰብዕና ነው የሚሞገተው።

ሰብዕናው ግራጫማ ነው። ሲቃ ሚባል ዓይነት። በቅጽበት ብርሃን በቅጽበት ጨለማ፤ በቅጽበት ብርሃን በቅጽበት ጨለማ፤ ብልጭ ድርግም የሚል ሰብዕና ነው ያለው። ጀርመኖች ብሊንግ ብሊንግ የሚሉት ዓይነት። ስለዚህም ነው ለመቃወም ለመደገፍም የጸና የፖለቲካ አቋም ስላሌለው፤ ጭልጥ ብሎ ወደ ድቅድቁ፤ ወደ አርንቋው ሲሄድም፤ ተመልሻለሁ ሲልም ማህል ላይ ሲዋልልም ጉዳዬ አማልለው። 

ብክነት ነው ከእርሱ ሃሳብ ጋር ዳገት ቁልቁለት መባተል። እሱን ለተጠጋ መንፈስ መጥኔ ነው አብሶ ለ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ክብሬ ብለው ሲወድቁ ሲነሱ እያዬሁኝ ስለሆነ …

እግዚአብሄር ዳኑ ሲላቸው ለቁቤ ትውልድ ለማ እና አብይን የመሰለ ጸጋ ሰጥቷቸው ነበር። አይደለም ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ እንዲበቁ አድርጎ ስብዕናቸውን የመቅረጽ አቅሙ ነበራቸው፤ በሴራ ተጠለፉ፤ ታገቱ እንጂ … ይሄን ነው ቄሮ ያለገባው። የ ኢትዮጵያ ህዝብም በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ በዘበጠ አቋም እና፤ አገር ቤት ባለው ሚዲያም በታገተው እውነት ዙሪያ ያለው ነገር የለም። ቢያንስ የዝምታ ቀን ማወጅ ነበረበት

በቃ ዝም ማለት። ወይ ቤት ውሰጥ የመቀመጥ … በዚህ መላ ቅጡ በጠፋበት ዝብርቅ ፖለቲካ ደግሞ ከውጭ አገር የሄዱት ሰፊ መዋለ ንዋይ ፈሶላቸው ዝምንምን ይላሉ አሉ ሚሊዮኖች ደግሞ መጠለያ አልቦሽ … የዕንባ ግጥጥሾ፤ 

መዳኛው የት እንዳለ እንኳን ደፍሮ ወጥቶ ለመሞገት አቅም አጥቷል  የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ። መጥፊያውን እያባበለ እልል እያለ ተቀብሏል የኢትዮጵያ ህዝብ። ነገን ያዬ … 

መሆን የነበረበት ግን ቄሮ አብይን አምጡ ብሎ ተከታታይ የሆኑ ድምፆችን ማሰማት ወይንም ቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ መምታት ነበረበት። ቄሮ እለታዊ የሳሙና አረፋ ሰናዮችን ሳይሆን ዘላቂ ትውልድ የሚገነባበትም መስመር መከተል ነበረበት። እሰኪ ፍቅሩ ሲቀጥል ይታያል …

ምልሰት ሳደርግ እርግጥ ነው ምርር ብዬ ልጥላው አልለውም አቶ ጀዋር መሃመድን። ለምን? እኔም እራሴ አላውቀውም፤ ልጄ ቢሆን፤ ታንሽ ወንድሜ ቢሆን እላለሁኝ። በሌላ በኩል ደግሞ ሃሳቡን ደግፌም አልቆምም ምክንያቱም እሱ እራሱ በቀጣይ ሰከንዶች ምን ሊሆን እንደሚችል ስለማያውቀው። እኔ እንጃ በቀን 6 ጊዜ ቃለ ምልልስ ቢያደርግ 6 ጊዜም ተለዋዋጭ ሃሳብ እና ዕይታ ነው የሚያቀርበው። ለዘርፈ ብዙ የኢትዮጵያ ፓለቲካ እንዲህ ዓይነት ሰብዕና ቀርቶ የአብዩም መንፈስ አልቻለውም።

እንዲያውም አንድ ጊዜ እግዚአብሄርን ባገኘው እንዲህ ዓይነቶችን በሩ ሲባሉ የሚጠፉ፤ ጠፉ ሲባሉ የሚበሩ ሰብዕናዎችን ለምን እንደ ፈጠረ ሁሉ እጠይቀዋለሁ ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ።

ብልጭታው ሳይታይ ድርግምታው፤ ድርግማታው ሳይረጋገጥ ብልጭታ ነው። ይህ አይደለም ለፖለቲካ ህይወት ለተራ ጓደኝነትም፤ ለጉርብትናም እራሱ እጅግ ጋዳ ነው። ወይ ቁጡ፤ ወይ አልቃሻ፤ ወይ ብስጩ ወይ ጨካኝ አንድ ቋሚ ባህሪ ያለው በስንት ጣዕሙ። እንደነዚህ አይነቶች ለውሳኔ አሰጣጥም፤ ለአጋርነትም፤ ለድምጽ አሰጣጥም አሰቸጋሪዎች ናቸው። ከባድ የሆነ በብዙ መልኮች የተሸነሸነ ስብዕና ነው።
  
ይሄ ነው ሰብዕናው ለማለት ባይቻልም ግራጫ ሰብዕና  የሚለውን ስያሜም ለመጀመሪያ ጊዜ የጻፍኩት ከጋዜጠኛ አቶ  ሳዲቅ አህመድ ጋር በዶር አብይ ሰብዕና ጋር ባደረገው ያልተጋባ ውይይት ነበር። እንደዛ ወርውሮ እንደ ማበሻ ጨርቅ ሲጥላቸው፤ ሲጠቅጥቃቸው ግርም ብሎኝ እምመድበው ቦታ ሳጣ ነበር ግራጫማ ሰብዕና ያልኩት።

ፖለቲካዊ ብቃትን በሚመለከትም ሊቅ ነኝ፤ ሙያዬ ነው የሚለው። አዬር የሚመራው ፖለቲካ የለም። ስሜቱ እኮ በቅጽበት ሲገነፍል እና ሲወዛወዝ ላዬው ሰው ማጣቱን ማገናዘብ ይቻላል።

አውሎ ከመራው ፖለቲካ ብቃቱ ደመነፍስ ነው የሚሆነው። በቅድሚያ ሚዲያቸው አቶ ለማ መገርሳ ለማለት እንኳን አይደፍርም ነበር። በሆዋላ ላይ „በኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ሞገድ ሲያል አቶ ለማ መገርሳ ወደ ፊት ሲመጡ ብሄራዊ ጥሪ አስተላለፈ ጸጥ ብለን ሂደቱን እንከታተል አድማውን እናቁም የሚል።

እሱ ነው እንግዲህ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጥሪ መልዕክት የሚያስተላልፈው፤ ለቄሮው ይችላል፤ ሌላውን ማህበረሰብ ግን አይችልም። ቅንጣትም አይችልም። የሆነ ሆኖ ኦህዴድ በደረሰበት ጫና ቆረጣ አካሄዶ ዶር አብይ አህመድን ፊት ለፊት ሲያወጣ አገር ይያዝልኝ አለ። አቋም ማለት ይሄ ነው።  

ኦቦ ለማ መገርሳን በጊዜያዊነት፤ አማራጭ በማጣቱ የደገፈ ፖለቲካዊ አቋም የለማ መንፈስ የፈቀደውን ውሳኔ መቀበል ግድ ይላል፤ ተማርከውም አልተማርከውም ፖለቲካ ሳይንስ ስለሆነ ሎጅኩ ይሄ ነው። ግን ይህም ሆኖ አላዬንም። ዛሬ የተቀበልው እና ሸልማት ያዘጋጀለት አቋም ትናንትም ከጅምሩም የነበረ ነው።

ፖለቲከኛ ማለት ጊዜን ቀድሞ መተንበይ ነው፤ እሱም ባይቻል መርህኛ መሆን ግድ ነው። ሲሞቅና ሲፈላ፤ ሲቀዘቅዝና ሲበርደው እንደ አዬሩ ጠባይ ከሆን ግን ያ ግርድፍ መረጃ ነው … አንተ  በአቅምህ ልክ አንተርትረህ አበጠርህ የምታጣራው።

ፖለቲካ እኮ ስክነት ነው። ፖለቲካ ፍልስፋና ነው። ፓለቲካ ሳይንስ ነው። ፖለቲካ ሎጅክ ነው። ፖለቲካ ፋክት ነው። ዝም ብለህ በገፋህ አውሎ ልክ እምትዘልበት አይደለም። ለነገሩ መሬት ላይ ካልተሠራበት፤ እንደ ገናም መሬት ላይ ሲሰራም የሙያ ክህሎት ያለው፤ ሰብዕናው ሙሉ የሆነ፤ የበለጠ በክህሎት ሰው አብሮ ሠርቶ የሙያ አባት ካልተገኘ በዛ እድሜ እጅግ ከባድ ነው። 

ብዙም እማልፈርድብት በዚህ ምክንያት ነው። የቅርብ የሙያ ብልህ አማካሪ፤ አባት ወይንም እናት አላገኘም። ተፈጥሮውም አሰቸጋሪ ቢሆንም። ጥሩ የሙያ አባት ሲገራ ጠቀሜታው ልዩ ነው። እንደገና ነው የሚፈጥረው ተከተታይ የሆኑ ተግባራትን መሬት ላይ ሠርቶ ቻሌንጆችን ተቋቁሞ፤ መፍትሄ አምንጭቶ፤ ቅራኔ ውስጥ ግብቶ፤ ታሥሮ መከራውን አይቶ ወጥቶ ወርዶ ያገኘው አይደለም ይህ ክብር። ኢሳት በገጸ በረከት ልዑል አደረገው። ሲነጠቅ ደግሞ እልኹ የፈጠረው ግፊት አንጥሮ አውጥቶ የእኔ የሚለው አንደበት ኖረው።

ይህን ማድረጉ፤ ተጠቅጥቆ እንደ እኛ አንገቱን ደፍቶ አልመቀርቱን ነው እኔ እጅግ አድርጌ እምወድለት እና እማከብርለት። ጥቃትን የማይቀበል ሰው እጅግ አድርጌ አውዳለሁኝ። በር ሲዘጋበት በመስኮት፤ መስኮት ሲዛጋም በጣሪያ መክፈቻ አዘጋጅቶ አለመደፈሩን ማሳዬት የሚችል ስብዕና እጅግ አድርጌ አከብራለሁኝ። የማይደፈረውን የሚደፈር …

ሁልጊዜ ሲናገር ልጆችን አስተማራለሁ አገር ቤት ገብቼ ሲል እስማለሁ፤ እሱን መሰል ሰብዕና እሱን መሰል ድርስ ምልስ፤ አምሳያውን ብልጭ ድርግም የሚል ትውልድ ለጠላቴም አልመኘውም እንኳንስ ለምሳሳለት ለነገ ትውልድ።

እሱ እራሱ ሰው አጥቶ አዬር ላይ ታዋቂነት ሲኮፍሰው እንዲህ በክብር ዙፋን ወጥቶ መንበር ላይ ሆኖ ገዢ መሬቱን ሲቆጣጠር፤ ሳይ መሬት እንዲረግጥ ሁኔታዎች የመጡ እለት ወድቆ አይነሳም። ይሰበራል።

 እንኩትኩት ብሎ ነው የሚቀረው። እርሾ ያስፈልጋል መሬት ላይ ለመሥራት። አገልግሎት መሬት ላይ ሲጀመር ነው የሚዘልቀው። 
አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አሳምሮ ያዬበት ወቅት ነው። እግዚአብሄር ይመስገን። አይደለም እትዮጵያ  የአፍሪካ ህዝብ መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አይቷል፤ አይደለም አፍሪካ መሪ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዓለም ተመልክቷል። 

ያ መንፈስ ይቀጥላል ወይ በሙሉ አቅሙ ቢባል በፍጹም። አሁን ሌላ መሪ ሃይል ነው። ምን አልባትም እነ ከይሲው ታስፋዬ ገብሬ የሚመሩት ሊሆንም ይችላል።

የሆነ ሆኖ በዛ በአብይ ቅኝት የተዳሰሰ መንፈስ የእሱ አቅም እኔ ነኝ ያለ ሊሂቅ ያን የልቅና፤ የትህትና የሰዋዊነት መንበሩን ተሻግሮ ተደማጭ ለመሆን ከእንግዲህ ምን ያህልም ሩቅ መሆኑን ዬትኛውም ወገን አባልተኛ ያለሆነው ማለቴ ነው እንረዳለን።

ከዚህ ላይ ከእኔ ጋር የተያያዘ አንድ ምሳሌ ላንሳ፤ እኔ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ ተቀይሮ ሁለት አለቆች ጋር አብሬ መሥራት አልቻልኩም ነበር። የመጀመሪያውም ሆነ ተከታዩ ጋር አብሮ መስራት ከባድ ነው የሆነብኝ፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ ሁሉን ከሰጠው ይሄ ይቀርሃል የማይባል መሪን አዬች ስለዚህ ከ እንግዲህ ጀርባ እና ጀርባ ካልሆነ በስተቀር በምን ስሌት ልብ ለልብ?

ቢያንስ የሚመጥን ነገር ግድ ይላል። ይሄን ደግሞ እናውቃዋለን። እጅግ ነው የሚገርመኝ በሳል የምላቸው የአገሬ ፍሬዎች ሊቀ - ሊቃውንታት በፖለቲካው ዘርፍ ማለቴ ነው ሁሉ የሚሰጡት ዕድምታ ይገርመኛል።

ምክንያቱም የአብይን መንፈስ ደፍሮ እሱ ካለው ሊመረመር ከማይችለው የመንፈስ ቅዱስ ብቃቱ መድርስ ቀርቶ ጫፉ መቅረብ ጭንቅ ነው። ማን ያዳምጣል አሁን ሌላውን። ነፍሳችን እኮ በሳምንት ውስጥ በረዶ ውስጥ ነው የተጨመረው። ውጥቶ እንዲናጋር አጋቾቹ ቢፈቅዱለትም ነፃነቱን ስለተቀማ አይሆንም። ያ ልዩ አቀራርብ ካለ መሉ ነፃነት የሚደፈር አይደለም።   

ያ ቅድስና፤ ያ ቸርነት፤ ያ ርህርህና፤ ያ ቤተሰባዊ ሁሉን በፍቅር የመቀበል አስተምህሮት፤ ያ ምራቁን የዋጣ ሰብዕና መንፈስ እኮ ዕድሚያችን እስከ አለ ድርስ ከበቂ በላይ ሁለመናውን ሰጥቶታል። ሦስት አራት አምስት ዲግሪ ያሰጣል። አጥግቦናል። ከማንም ምንም የመንፈስ ሀተታ እርሃብ የለብንም። አጥግቦናል በቅንነቱ፤ በደግነቱ፤ በብቃቱ፤ በጸጋው፤ በብርታቱ … በጸዳለ በፈካ ገጹ፤ ፍቅርን በገፍ በመለገሱ፤ ይቅርታን በመሆን ማሳዬቱ ደንበር የለሽ ክህሎት።

ዋ አብይ! መቼ ይሆን ነፃ ሆነህ ከቤተሰብህ ጋር የእውነት ሳቅህን የምናዬው? አሁን እኮ ኔት ከሌለበት ቢሮ ነው ቀጣዩን ተግባር እዬነደፈ ታግቶ እዬሠራላቸው ያለው። ስልክም ይፈቅድለታል ብዬ አላስብም። ከደወለም የተሰጠውን ብቻ ነው የሚናገረው። ካነሳም እንዲሁ።

ገርሞኛል ፈንድ ራይዚንጉ የሚያስተባብሩ ተሿሚዎችን ጉዳይ ሳነብ። ይህ መቼም ከጅልነት በላይ ነው። ይልቅ አዲስ ተሿሚዎች የዲአስፖራው ማለቴ ነው ዶር አብይ አህመድን አስፈቱት ከታገተበት፤ ሳይጨርሱት፤ ወይንም አፍዘው አደንዝዘው ተረከቡት ሳይሉን … እዬሆነ ያለው በደመነፍስ አይደለም እጅግ በረቀቀ እጅግም በተደራጀ ሁኔታ ነው፤ 

እንደ ናፈቅን አይተን ሳናምነው ወጥቶ በገባ ቁጥር ፈጣሪን እንደተማጸነው እንዲህ በጎደሎ ቀን የሆነው ሆነ። ለነገሩ ታስቦበት የተደራጀ ነው።

እሰቡት ዶር አብይ አህመድ ጎንደር ሲሄዱ ጀግናው ኮ/ ደመቀ ዘውዱ እንዳይገኙ አደረጉ፤ አሁን ለአቶ ጃዋር አህመድ ከጎንደር ተነስተው እሱ መፍትሄ ሊያሰጥላቸው እዛ ተገኝተዋል ኮ/ ደመቀ ዘውዱ። እራሱ የወልቃይት የጠገዴን ኮሜቴ ከሁለት ነው የሰነጠቁት። አቶ አታላይ ዛፌ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ እና ወጣት ንግሥት ይርጋ።

ይህን የሚመሩት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ናቸው። በዚህ ልክ የጎንደር ጉዳይ የቅድመ ሁኔታው የድርድር አካል ነው ማለት ነው። ይህን ፍሬ ነገረ በሚገባ መመርምር ያስፈልጋል። በሌላ በኩል የጎንደር ህብረት መሪ የቀደሙት ባህርዳር እንደሄዱም ትናንት ከወደ ካናዳ ሹክሹከታ ሱክ ብሎኛል፤  ምን እዬሆነ ነው? ንግዱ ትርምሱ ምንድን ነው?

ወደ ቀደመው ስመለስ አቤቶ ጃዋር መሃመድን ማመን በሚመለከት ያቻለችሁ ቤተ ክርስትያን አስቀርጹለት አብሶ አቶ ንጉሡ ጥላሁን። ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለገብረ ጉንዳሉ ለአቶ ተስፋዬም ገብርአብም ጭምር።

ለኢትዮጵያ ተስፋ ግን አያድርግባት። አይጣልባት። ተረገምን ከሆነ ብቻ ነው ይሄ የሚሆነው። ለነገሩ ከዚህ በላይ መረገም ምን ይምጣ በሦስት ውስጥ ነው ይህ ሁሉ ነጠቃ አዳማ የተከወነው።

 ሥልጣን አልፈልገም ሲል አዳምጨዋለሁኝ። የቄሮ ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጁን ጥናት ላይ እንዳለ አዳምጫለሁኝ በቀጣይ ደግሞ ይጠበቃል። የዛ ጠቅላይ አዛዥነቱን ማንም አይወስደውም። አሁን ብአዴን ይልቅ ለአቶ ተስፋዬ ገብርአብ አዲስ አቀባባል ይሰናዳ። 

ለሌላም ለሌላም ምን አለ አሁን እኮ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው አራጊ ፈጣሪ …  የሆነ ሆኖ ሥልጣን የማይፈልግ ሰው እኮ የሰውን ሰላም አያውክም። የሚበልጠው መንፈስ ሲመጣ ይረጋል። „ሽርሽር በቃህ፤ ሥራህን ቁጭ ብለህ ሥራ እያለ ለዶር አብይ አህመድ ቀጭን ትእዛዝ ሲሰጥ የከረመው አቶ ጃዋር መሃመድ ምነው እሱ አሁን ሽርሽር ላይ ሆነሳ?

የሆነ ሆኖ ነፃነት ለዛ ለብርሃን ጸዳል ለሁለገቡ የኢትዮጵያ ግርማ እና ሞገስ ለቅዱሱ አብይ መንፈስ!
 
ፖለቲካዊ ፍልስፍና በጥላቻ፤ በቂም፤ በቁርሾ ተሰልቆ አይደለም ሊተነተን አቋም ሊያዝብት የሚገባው። ፖለቲካ እኮ መነሻውም መድርሻውም ሰው እና ተፈጥሮ ነው። ሰውን ጠልቶ ተፈጥሮን ጠልቶ ወይንም አግሎ ወይንም ጨቁኖ ፓለቲካ የለም።  ፖለቲካ የሰው እና የተፈጥሮ የአስተዳደር ጥበብ ማለት ነው።

 ጭብጡ ከስሜት ወጥቶ፤ ከራስ ፍላጎት እርቆ፤ ራስን አርቆ እና ገዝቶ ሊመረመመር፤ ሊተነተን ነው የሚገባው። አንድን ስብዕና ስለጠላኸው ወይንም ስለወደድከው አይደለም ፖለቲካው አቋም የምትይዘው። በዚህ ሚዛን አይለካም።

የጭብጡ የመነሻ ምክንያት፤ ምክንያቱ ያመጣውን ለውጥ፤ ወይንም ያ ምክንያት ያስከትላል ተብሎ የሚያመጣው አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ፤ ለተፈጥሮ ያለው ጠቃሚነት ብልህነቱ እና በመሆን መስምር ውስጥ ከውስጥ ጋር ተገናኝቶ አቅም መሆን መቻሉ ነው ሊታይ የሚገባው …

አንድ ለመጨረሻ ሰፊ አምክንዮ ያለውን በተደጋጋሚ አቶ ጃዋር መሃመድ ሲናገር የባጀውን ላንሳ በቀለ ገርባን ጠ/ ሚር ወያኔ ቢያደርግ ካለ ሥር ነቅል ለውጥ ፍንክች አንልም አይደለም ሲል የነበረውን? የወያኔ ሃርነት ትግራይ የውስጥ ድርድር ከሌላ በስተቀር አለ እንዳለ፤ ምንም የተነካ ነገር የለም።

የታሠረ፤ በህግ የተጠዬቀ የለም። አሁን ትግራይን ማዘዝ አይቻልም። ቢቻል ባዶ 6 ያሉ እስረኞችን ማስፈታት ይቻል ነበር ሌላው ቢቀር። አሁን ደግሞ ባህርዳርም ንጉሥም ወሳኝም እኔ ነኝ እያለን ነው።  ከአዲሱ አንጃ ጋር ነኝ እያለን ነው።  

ብጥብጦችን፤ ሁከቶችን፤ ጠ/ ሚር አብይ ህዝብ ከመሰብሰባቸው በፊት የነበረው ሳቦታጅ፤ አብሶ የኤርትራና የኢትዮጵያ ሰላማዊ ግንኙነት እኔ በንጽህና በፍጹም ቅንነት ነበር ያዬሁት፤ ሁሉንም ነገር በቅንነት መቀበል መርሆዬ ስለሆነ።

አሁን ላይ ደግሞ ስርክራኪዎቹ እጅግ ውስብስብ ፈተና ላይ ኢትዮጵያ እንዳለች ይሰማኛል። ደቡብም ቢሆን ይህን ያህል ሺህ ህዝብ ተፈናቅሏል ገናም ያልፈነዳ ጉዳይ አለበት። 

እራሱ የችግሩ ምንጭ እና ግብዕቶቹ በጥልቀት በክብደት አንድ መስመር ላይ ያገናኘናል። ግን የጎዞው አቅጣጫ ወደዬት ነው? የትስ ድረስ ነው? መንስ መሰናዶ አለው። ሁሉ ነገር ተወጠነ በውጥን ቀረ፤ አዲስ ወጣንያን ደግሞ ተስለፋዋል … የ ኢትዮጵያ ሚደያም ያው ድምጡ ጥፍት ብሏል። የተመጠነለትን ብቻ ይዞ ብቅ ነው … ሽባዎች አኮ ነን!

ግን ኦቦ ለማ መገርሳስ ይት ናቸው? አብረው ቤተ መንግሥት ታግተው ወይንስ በነፃነት እዬተንቀሳቀሱ? ጣምራ መንገዶች በጣምራ የጠቆሩ ፈተናዎች፤ የጣምራ መንግሥታት ተልዕኮ እና የጣምራ ኢጎ ዳገቶች የነገ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ደመናማ አድርጎታል።

ግን አንድ ነገር ከቶ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ለአቶ ጃዋር መሃመድ መሬት ላይ ስግደት ቢጤ አደረጉን ይሆን? መቼም ገመናችን ዘንድሮ በርክቷልና … 
የኔዎቹ ቅኖቹ ያቻለችሁ ጸልዩ ያ ተናፋቂ መንፈስ እስረኛ ነው። ይህን አትጠርጥሩት … መጸለይ፤ ድዋ ማድርግ አያስከፍልም … ጸሎት መልካም ነው ቢያንስ መከራችን እምንችልበት ጽናት እና ትእግስት ይኖረናል።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።


የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።