አልደፈርም ያለው "የሹክሽኩት ዕድምታ" በሥርጉተ ዕይታ!
እንዳፋችሁ ያድርግላቸው ያድርግልን።
„ትእዛዙን አናገራለሁ እግዚአብሄር አለኝ፣-
አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፪ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 11.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
እምዬ የአንቺ ቅዱስ መንፈስ እንኳን እንዴት ይርሳቸው?
መነሻዬ። በመጀመርታ ግን ሰንበት እንዴት ይዟችሆዋል ውዶቼ።
https://www.satenaw.com/amharic/archives/62174
ከሚነሶታ እስከ አዲስ አበባ (ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት)
awaze news
የሁለቱ ጹሁፍ መነሻ የጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ጤንነትን በሚለከት ነው። ከዚህ ቀደም ጤና አዳም "ሹክሹከታ" የሚል ዜና አቅርቦ ነበር። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በመርዝ በተበከለ እውሃ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው የሚገልጽ።
ይህን በማስመልከት የቡድኑ ጉባኤ መሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረተ ግልባጩን "ለሽክሹክታ" አድርጎ ምንም የደረሰ ነገር እንደሌላ ነው ማሰተባበያ የሰጠው የሳታናው ብራና ላይ ያገኘሁት መነባንብ ጭብጥ እንደነገረኝ፤ ስም ባይጠቅስም ግን ሁለት ማህበረ ተጓዦች ድንገተኛ ህመም እንደ ነበረባቸው እና የልዩ የህክማና ቡደኑ የሥራ ጫና እንደ ነበረበት ግን አልሸሸገም።
ይህን እንግዲህ በነሲብ ይሄ ነው ያነ ነው ማለት አይቻልም። በሌላ በኩል ግን የተፈጠረ ነገር ቢኖርም ይህን እንዲያስተባብል ጫና ማደረግ ግድ ይላል። ምክንያቱም የጉዞው ሁለመና ስለነበረ ዲያቆን ዳንኤል ክብርት እንደገናም ታዕማኝነቱም የዛን ያህል ስለሆነ ህዝብ እንዲረጋጋ ተጽዕኖ እንዲፈጠር ስለሚፈለግ። ስለዚህ ራሳቸው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ተገደው በአጋቾቻቸው ደውለው እንዲነግሩት ሊደረግ ይችላል።
በሌላ በኩል መለያዬዩቱ ቦሌ ላይ ከሆነም ዲያቆን ዳንኤል ከተለዬ በሆዋላ የተፈጠረም ከሆነ ላያውቅ ይችላል፤ የቅርብ ሰው ነው ስለሚባልም ሊደበቀም ይችላል።
የሆነ ሆኖ በዲያቆን ዳንኤል ክብርትን ማሰተባበያ አልደፈረም ያለው ጤና አዳም ዜናዬ ትክክል ነው እንዲያውም ኢምሬት ህክምና ላይ ነበሩ ብሎ ከመጀመሪያውም በተሻለ ሁኔታ የደረሰውን አዳጋ ዘርዘር አድርጎ አቅርቧለኝ።
https://www.youtube.com/watch?v=ZqjHUW4Fp4Y
Shukshukta (ሹክሹክታ) - ዶ/ር አብይን በመርዝ ሊገድል የነበረው አጃቢ... | Dr Abiy Ahmed
https://www.youtube.com/watch?v=ufK_PZ-vm4E
Shukshukta (ሹክሹክታ) - ሹክሹክታ አልዋሸም! ዶክተር አብይ ኢሚሬትስ ሆስፒታል ነበሩ | Dr Abiy Ahmed | Emirates
አራቱም ንግግሮች እሰጣ ገባቸው ብክለት አልገጠመም፤ ገጥሟል በሚል ነው ሙግቱ። ከብክለቱ ቀጥሎ ያለው ነገር ግን ጭብጡን አልነኩትም። እኔ ደግሞ እገታም አለ ነው የምለው።
አሁም ኢትዮጵያን የሚመራት ሌላ ጁንታ ነው ብዬ ነው የማስበው። የመጠጥ ብከላውንም ገጻቸውን በማዬት ብዙ ነገር ወደ ውስጥ ዘልቆ ገብቶ መመርመር ይቻል። ፈዘዋል እኮ። ያ መንፈሳቸው በጭራሽ የለም። የተወለዱን ያህል ስለምንሳሳላቸው በጣም አቅርበን ብናዬው አራቱም ቪዲዮ ላይ መልዕክት አለው። ውስጣቸውም በሃዘን ተጎድቷል። ታማኝነት ቅርጥፍ ብሎ ተበልቶ ብቻቸውን ሲቀሩ መራራ ነው። ሃሞት። ተተኪው ነግ ለእኔ ቢል መልካም ነው።
የጤና እክል እንደ ገጠማቸው የጠወለገው ገፃቸው ያሳጣል። ነፃነታቸው እኮ የለም። ተቀምተዋል። ስለሆነም ይህ አይሆንም ብዬ አላስብም። ጽአናታቸው እና ሰውን ለማቅርብ ያላቸው ፍላጎት መከልከሉን መታገዱን፤ ማዕቀብ እንደተጣለበት ሁሉ ይታያል። ቀደም ብዬ እንደገጽኩት እኔ ያዬሁት ህልሜ ባዶ ወንበር እና የግማሽ ገጽ ሰው ምስል ደግሞ ለእኔ የሚልክልኝ መልዕክት አለ። እንዲያውም አሁን አሁን ያ ግማሽ ገጽ በዚህ ሴራ ውስጥም በተዘዋዋሪ ይኖርበትን እያልኩኝ ነው። ሂደቱ ዱብ እዳ ነበር። ለውጡ ብቻ ሳይሆን ብሩህ ብቃቱ እጅግ አጓጊ እና መስጫ የሰማይ ታምር ነበር። ቀለበሱት እንጂ።
የገረመኝ አለምአቀፉ ጋዜጠኛ አቶ አለመንህ ዋሴ ቀደም ሲል በፐርሰንት ሊሆንም ላይሆን ይችላል ያለውን ሽሮ 100% ደህና ናቸው ምንም አልደረሰባቸውም እንደ ወትሮው ዘና ብለው እንግዶቻቸውን አስተናግደዋል በሚል ነው የደመደመው። ይህ በውነቱ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ መልካም አይመስለኝም።
የእንግሊዝን ልዑክ፤ የሳውዲንም፤ የአረብ ኢሚሬቴንም እንግዶቻቸው ተቀብለው እንዳነገጋሩ ቪዲዮዎች አሉ። ቪዲዮዎች ግልጽ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋሉ። የደህንነት ችግር ብቻ ሳይሆን እንደ ተጋቱ ጭምር ነው የሚናገረው። በብርቱ ጥበቃ ቁጥጥር ሥር ነው ያሉት። ይሄኢ ለደህንነታቸው ታስቦ አልነበረም። ለደህንነታቸው የታሰብ ጊዜም ሆኖ የፈንጅ ውርዋሮም እኮ ነበር። ወዲያው ወጥተው ነው ስሜታቸውን ኤዲት ሳያደርጉ የገለጹት፤ እንደገናም ተጎጂዎችን ሄደውም የጠዬቁት። በዚህ ሳምንት ውስጥ እኮ ብዙ ምስቅልቅል እያለ አስችሏቸው ዝም ሊሉ አይታሰብም? ፍቅር የሆኑ ሁሉን የተሰጣቸው ያለ ጊዜያቸው የተፈጠሩ ለእኛም የማይገቡ ነበሩ።
ቅደመ ሁኔታው አይታወቀም፤ አዲስ የሽግግር መንግሥት፤ ጠናዬ ተጓድሏል ብሎ ሃላፊነታቸውን እንዲለቁ መገደድ፤ ወይንም በሌላ ሃይል መንፈስን በቅኝ ግዛት የመስጠት ሊሆን ይችላል። እሳቸው እንደምስል ሆነው በትእዛዝ ብቻ ሮቦት መሆን።
አሁን ያለው ሂደት እኮ አንጃው ቀጥሎ እሳቸውን እየተረሱ የሚሄዱ ነገሮችን በመፍጠር ነው። የህዝቡም ማዕበል እጅግ አስፈሪ ስለሆነ። የምዕራቡ ዓለምም ጉዳይ አለ።
ስለሆነም ቅኖች ሆይ! ተግ ብሎ በማስተዋል ከሁሉም አቅታጫ መመርምር ያሰፈልጋል ማንኛውም ያገበኛል የሚል ቅን ዜጋ።
ምክንያቱም ቀጣዩ ጉዞ ምን ሊሆን እንደሚችል አይታወቅም። አደጋ ውስጥ ናት ኢትዮጵያ። ምን አልባትም የማይታወቀው ባልጠረጠርነው መልክ የውጭ መንግሥታት ጣልቃ ገብነትም ሊኖር ይችላል። ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት የብልህነት ሊቀ ዲሞስ ሲኖራት ለዛውም ከከፋ? ማን የበረከተውን? ኢንጂነር ሳይንቲስ ቅጣው እጅጉም ህልፈት እኮ የዚህ ፍርሃት ነው? የራስ ተሰማ ናደው ዘመናዊ አድማ ሴራ አይተኛም፤ አያንቀላፋም፤ ሁልጊዜም እንኩሮው ከዛ ነው የሚነሳው ...
የመጠጥ ውሃ ባከዮች እይህን ሲያቅዱ ይድናሉ፤ ይተርፋሉ ብለው አልነበረም። እግዚአብሄር ደግሞ ይህም እንዲዩ ፈቀደላቸው። ቁሞ ማዬት ሰው ማለትን ይተረጉማዋል። ባይተርፎ ኖሮ ይህን ያህል የሚደያ ጨዋታም አይነርም ነበር የታሰበው ሰው በቦታው ይቀመጥ ነበር፤ የሆነው የታቀደው በታቀደው ነበር የሚሆነው አሁን ግን ሊታረቁ የማይችሉ ፈተናዎች ፊት ለፊት አላዛሯን ኢትዮጵያ ወጥሮ እና አሰጭንቆ ይዟታል።
ችግሩ ደግሞ ህዝቡ አውቆ የመንፈስ ዝግጅት እንዳያደርግ ወዲህ እና ወዲያ በሚወራጩ የሃሳብ ፈሰቶች እዬተዋከ ነው።
የባሰ ችግር ቢመጣ ደህና ሊሆኑ የሚችሉት ትግራይ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ብቻ ናቸው። ያም ቢሆን የትራንስፖርት ከተዛጋ ጣጣው ከባድ ነው። ኤርትራም መንገድ ልክፈት ብትል ካለ ቅድመ ሁኔታ የማይታሰብ ነው። የአዎንታዊነቱን ግብረ ምላሹን የወያኔ ሃርነት ትግራይን አሳምራ ስለመረመረችው። ለነገሩ ይተዋወቃሉ።
እውነት ለመናገር ይህን መጠራቀቅ ኢጎውን አሸንፎ መውጣት የነበረበት ኦህዴድ ነበር። እራሱን ማሸነፍ አቃተው እና የተሰጠውን ሃላፊነት ጎረደው። አሁን ጨዋታው የፖፕላሪቲ የልጆች ጫዋታ ሆኖ ነው ያረፈው። አገር መምራት ሳይሆን ሥምን ማንገሥ፤ የአብይን መንፈስ እዬናዱ የግልን ዝና ማኮፈስ ነው የሆነው።
አላዛሯ ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ናት። እሳቸውን ሲደግፍ የነበረውም ካቢኔ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አይታወቀም። ወይ የውሸት ነበር ወይ ደግሞ ስልብ ሆኗል አብሮ። ራሱ ጋዜጠኞች እኮ በሙሉ የሉም ሚዲያ ላይ። አስተውሉ እንጂ ከልብ ሆናችሁ። ይህ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ኦን ላይን፤ ሪፖርተር የሚሉት ሊኖር በቻለ ነበር። ግን እዬሆነ ያለው ሌላ ነገር ነው። አቅም የፈሰሰበት ነገር ሽልማቱ ለሌላ መንፈስ ሆኗል።
አብይ በመንፈሱ በለውጡ ውስጥ ያሉ የእኔ የሚላቸው ይክዱኛል ብሎ አላሳበም ነበር፤ አሁን ግን እኔ እንደሚገባኝ አብረውት ያሉት እንደ እሱ የታገቱት ብቻ ናቸው።
ጭንቁ የሃይማኖት ጦርነት ቢቀጥል እሰቡት? እና እኔ እምለው ቢያንስ ጋዜጠኞች ጸሐፍት ተዘናጉ እያሉ ከሚሰክቡ ቢያንስ ዝም ማለት ይመረጣል 100% እርግጠኛ ሆኖ ከመናገር። ምክንያቱም የመንፈስ ትጥቅ ስለሚያስፈታ። ለማናቸውም ነገር ዝግጁ ሆኖ መቆዬት ጥሩ ነው። የመረረ ነገር ቢኖር መቋቋም ይቻልል። ይህን ልመዱት እያሉ ነው እነሱ ቲያትር እየሠሩ ያሉት።
በተለመደው ሁኔታ አይደለም ኢትዮጵያ ያለችው። ደስታ እርቋታል፤ ሃዘን እረቦባታል። የት ላይ እንዳለችም እራሷ አላዛሯ ኢትዮጵያ አታውቀውም። ወደዬት እንደምንሄድ አቅጣጫ የለሽ ነው። በሰከንድ አዲስ አባባ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል፤ ቤተ - መንግሥት ውስጥ ምን እዬተሠራ እንደሆነ ሁሉ አይታወቅም።
ድፍን ድንብልብል ያለ ነገር ነው ያለው። ልሙጥ ጉድ። ብሄራዊ ስሜት የሚሠማው ሰራዊት ቢኖረን፤ ደህንነት ቢኖረን ቢያንስ አገር የማዳን ተግባር፤ ህዝብን የማዳን ተግባር የመከወኑን ሃላፊነትን ሪስኪውን ወስዶ የሆነ ነገር ያደርግ ነበር አሁን።
ግን ተበጣጥሰናል፤ ለፈተና እንጂ ለመፍትሄ ስንዱ አይደለንም። ብንሆንማ ኑሮ ከዚህ የተሻለ ጊዜ አይመጣም ነበር። እናውቃለን በአንዲት ቃል ቀርቶ አንዲት ፊደል እንኳን እንደማንግባባ። አንድ መንፈስ የለም። ምን አለን አንድ የሚያደርገን? ብሄራዊ መዝሙር? ሰንደቅዓለማ? ህገ መንግሥት? ፍላጎት? ቋንቋ? ራዕይ? ምንም ነው።
የቅርቡን የአማራ ይህልውናን ተጋድሎ ተመልከቱት፤ ስንት ሰው ነው በግል ኢጎው ወስጥ ከዝኖ የተቀመጠው። ለአማራ ከሆነ ምን ልዩነት ያስፈልጋል? ለኦሮሞ ከሆነ ምን ልዩነት ያስፈልጋል? የሚያሳዝንኙ ቁጥራቸው አናሳ የሆኑት ናቸው? በትላልቆቹ ሊሂቃን መታመስ እነሱም አብረው ይታጨዳሉ።
የሆነ ሆነ አሁን ዋናው ቁም ነገር ስመለስ አብይ ይራሱ ጌታ አይደለም። ሌሎችን በፍቅር ከውስጡ ደመረ እሱ ግን ተቀነሰ። ይሄ እውነት ነው። ቁርጣችሁን እውቁ። እንደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እና እንደ አቶ አለምንህ ዋሴ ቅንነት እና ቸር ማሰብ ከሆነ እንደ አፋቸው ያድርግልን።
ሌላው ቀርቶ እኔን የሚሰማኝ አሁን የሚሰጣቸውን መዳህኒት እንብኝ የማለት ሁሉ መብት የላቸውም። የእንቅልፍ ታብሌት፤ የሚያደንዝዝ፤ እራሳቸውን እንዲረሱ የሚያደርግ ሁሉ መዳህኒት ሊሰጣቸው ይችላል።
አሁን የሚባሉትንም፤ የሚጠጡትንም የሚወሰኑላቸው አጋቾቻቸው ብቻ ናቸው። ና ሲባል መምጣት ሂድ ሲባል መሄድ። ክፍሉን ራሱን እዩት፤ መላው የጣፋ ነገር ነው እዬታዬ ያለው። ጠባቂዎቻቸው እስኪ እንዴት እንደሚቆጣጠሯቸው ተመልከቱት እስኪ። የዓይን ግንኙነት ሁሉ አይፈቅዳለቸውም።
ሌላው አንድ ሹመት ትናንት ሰማሁኝ። ረ/ፕ ነብዩ ባዬን ተመልክቱ በወር ውስጥ ሁለት ሹመት ነው። በጠ/ ሚሩ በቀጥታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር ዋና ዲያሪክተር ሆነው ተሹመው ነበር፤ ትናንት ደግሞ የአዲስ አባባ ባህል እና ቱሪዝም ተጠሪ ሆነው ተሹመዋል። ድብልቅልቅ ያለ ጉድ ነው።
አሁን እኮ የሰው ጉዳይ ነው። የሥልጣንም፤ የሴራም ጉዳይ አይደለም ነፍስ ጭንቅ ላይ ናት። ያን ነው ወደ ውስጣችን አስገብተን ልንመረምረው ይገባል። ምንድነው የሚቀጠለው? ምን እዬሆነ ነው? አንድ ነገር ቢፈጠር ለወር የሚሆን ጥሪት የሌላት አገር 100ሺህ ህዝብ ይዛ ምንድን ነው የምትሆነው? ራውንዳ እኮ ያን ፈተና የተሻገረችው በሴራ ጸጋዋን ጤናውን ተብክሎ ነፃነቱን ተነፍጎ፤ ግራ ቀኝ ተዋክቦ ፤ ታግቶ አይደለም።
በብዙ ጥንቃቄ እና በተጋ ጸሎት አምላኳን ተማጽና ምርቃቷን በጥንቃቄ ጠብቃ ተንከባክባ ነው ዛሬ የአፍሪካ መዲና የሆነችው። እኛ ደግሞ ለአንድ ወንበር 15 ሰው ተሰልፎ ለዛ ይወድቃል ይነሳል። አገራችንም አሳልፈን ቅኝ ግዛት ለማድረግ በር ላይ ነን። ገማናው ይሄው ነው። ብቻ "አብይ ይወገድ" ሌላው ትርፍ ነው …
መሬት የለችም አሁን። መሬቷ የማን ስለመሆኗ የሚታወቅ ነገር የለም። እያንዳንዷ ቅጽበት አመድ ነስንሰን ኤሉሄ ልንል ይጋባል። ቁልጭ ያለ የቤተ መንግሥት መንፈስ ግልበጣ ነው ያለው። ቁልጭ ያለ ስውር ኩዴታ አለ። እንዲህ ለብ ለብ ባለ ጉዞ መጭ ልንለው አይገባም፤ ስለሚተካውም ቢሆን ጋራንቲ የለም፤ የተተኪው ተተኪ ስለሚሆንም ስንት ቀን በጥበቃ? ማን ምንን ይመን? አደብ፤ ተደሞ ፤ ጸሎት በእጅጉ ያስፈልገናል።
ኤርትራ አቋሟ ምንድነው? ግብጽ አቋሟ ምንድን ነው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወዳጅ የሆነችው አረብ ኢምሬት ንጉሣውያን ቤተሰቦች አቋሟቸው ምንድን ነው? እዬሆነ ያለውን በቅርበት ያውቃሉ ብዬ አስባለሁኝ። ቀጣዩስ ምዕራፍ ምን ሊሆን ነው። እንደ ዜጋ ሩጫውን ተግ አድርገን መፈተሽ መመርመር ይገባል።
ስለ ነገ ቀርቶ ስለዚህች ቅጽበታዊ ሁኔታ በግርፉ ሳይሆን ክልብ ሆነን ልንጠቁርለት ልንከስለት ይገባል። አብይማ ከልጅነት እስከ እውቀት ታክቶ የሆነውን ወስጡን አግኝተናዋል። አንድ ነፍስ ነው ያለው። አያሰቃዩት እንጂ ልሙት ብሎ የፈቀደ ሰው ነው። መሪነት ለመሞት መፍቀድ ነው። ለመሆን ኦቦ ለማ መገርሳስ የት ናቸው? ከዬትኛውስ ጎራ ናቸው? በምን ሁኔታስ ይገኛሉ? አቤቱ አምላኬ ምኑን ነው ያመጣህብን? ስለምንስ ፍጹም የተለዬ ሰብዕና ኖራቸው?
ወጣት እያለሁኝ የታላቅ እህቴ ልጅ „መሪ መሆን አልፈልግም“ ይል ነበር። ለምን? ስንለው መሞት ስለማልፈልግ ይል ነበር፤ የ7 ዓመት እያለ ማለት ነው። ድሮም እንደ አናንያን አዛርያን ሚሳኤል እሳት ውስጥ የተጨመረ መከረኛ ነፍስ ነው ስናከለክለው የባጀነው። የሚያጽናናው ቅኑ፤ ጨዋው የኢትዮጵያ ሚሊዮን ልጆች ፍቅራቸው ሰጥተውታል። የመንፈስ ስደተኛ አይደለም አብይ።፡አብይ የ100 ሚሊዮን መንፈስን የፈቀደ ንዑድ ፍጥረት። ዕድለኛ ነው። ይህን አይቷል በዚህ ልጽናና።
ዶር አብይ አህመድ ማመን እስኪያቅት ድረስ ያለጊዜያቸው የተፈጠሩ መሪ ነበሩ። ያለበደላቸው ደግሞ መከራን የሸለምናቸው። ፍዳን ያሸከምናቸው። ቢዘገይም እውነቱ ፍርጥርጥር ብሎ ይወጣል። ልጅ ካወጣም፤ ትውልድ ከተካም ይታያል።
ሌላው ግን ውጭ የሚገኙ የሰብዕዊ መብት ተሟጋቾች ስለምን እንደተለጎሙ አይገባኝም። ፈጥነው ለዚም ተማላ ምስኪን በመልካምነቱ ባይታዋር ለተደረገ ፍጥርት ሊደርሱለት ይገባ ነበር። ግን ሁሉም ለሽ ብሎ ተኝቷል። አዝናለሁኝ።
ጌታ ሆይ! ለዛ ንጽህና አንድ ነገር አድርግ እና ከማዕት ገላግለው እባክህን?
የኔወቹ ኑሩልኝ ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ