የአብይን የቅንነት ሌጋሲ ለማሰቀጠል ብቻ እንትጋ።

የመረጋጋት ስንቅ።
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 11.-8.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።



                 „እኔ ግን በምህረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤
              አንተን በመፍራት ወደ ቅደስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“
                መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፯
 ከሥርጉተ ©ሥላሴ 
11.-8.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

  • ·      መነሻዬ


Ethiopia: [ሰበር ዜና!] ከዶ/ አብይ ስለ ሶማሌ ክልልና የአቡነ መርቆርዮስ ጉብኝት የተሰጠ መግለጫ!

የሆነው ሁሉ ባይሆን መልካም ነበር። ብቻ ይሄ ቪዲዮ አንፃራዊ ነፃነት ያለው ነው። መንፈሱም ጤነኛ ነው። ቀጣዮቹ ጊዘያቶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ባላውቅም ከሰነበትንባቸው ጭጋጋማ ማዕልተ ሌሊቶች የተሻለ ተስፋ ያለው ነው። መሆን ያለበት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖው በተከታታይ ማስቀጠል ነው። የሆነው ሁሉ ለመልካም ቢሆንም አሁንም ሴራ እና ሼር ሊያርፉ ስለማይችሉ የቅኖች መንፈስ የአብይን ሌጋሲ የማስቀጠል ተግባር ላይ መታተር ያስፈልጋል።

ይሄ ቁስል እዬቀራረፉ ግጭትን የሙጥን የማለትን ሂደትን አቆሞ መድንህን የሆነውን የአብይ መንፈስ በቀደመው ሃይሉ እና ብቃቱ ይቀጠል ዘንድ የላዩን ጉዞ ተግ አድርጎ ውስጣዊ የሆነ ድጋፉን በእውነተኝነት እና ስሜት መቀጠል ነው። የሆነው ሁሉ ለበጎ ነው ብለን የሚበልጠው ቀሪ ጊዜ ስለሆነ በማንም እና በምንም ቂም እና ቁርሾ ሳናበቀል በንጹህ ህሊና የአብይን ሌጋሲ ጉልበት እንዲያገኝ አቅም እንዲኖረው ማስቻል ይገባል።

እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ዜጋ ነፍሱን ከአብይ ሌጋሲ ጋር ብቻ ባያያዘ፤ ባስማማ ቁጥር መከራውን ተሻገረን የጥልን ግድግዳ አሸነፍን ቂምን እረተን፤ በቀለን እረስተን ትውልዱን ከቀጣይ ብክነት እንታደገዋለን።


ይህ ያዬሁት ቪዲዮ ሌላም መልዕከት ስለላከለኝ የተሻለ ስሜት ተሰምቶኛል። እርግጥ ታማኝነት ሲጎብጥ ከበደሉ ሁሉ በላይ ነውና ቁስለቱ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ባውቅም ከሁለገብ ፈተና እና እቀባ ልዑል እግዚአብሄር ጠብቆ ለዚህ ለናፈቅን የአብዩ አንደበቱን እንድናዳምጠው ስላደረገልንም የተመሰገነ ይሁን አሜን!


አሁን የተቃጣውን የሴራ ገመድ በካሂለ ሃይሉ በጣጥሶ ልዑል እግዚአብሄር የአብዩን ሌጋሴ ላመስቀጠል ሃይል እና አቅሙ የልዑል እግዚአብሄር ነው እና ይርዳን።

አብሶ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከቀደመው የሴራ ትብትቡ ጋር ተፋቶ ተጸጽቶም ከዚህ ንዑድ መንፈስ ጋር ሆኗ ድርሻውን ይወጣ ዘንድ ላስስበው እሻለሁኝ። የትግራይ ተዋላጆችም ብትሆኑ ቀልዱን፤ ተረቡን ቧሉቱን እና ዘመናዊነቱ ተግ አድርጋችሁ ለልጆቻችሁ እና ለልጅ ልጆቻቸሁ ትንሽ እንደ ሰው እሰቡ። 


ንጹሃን የኦሮሞ የአማራ፤ የጉራጌ፤ የከንባታ፤ የኢትዮ ሱማሌ፤ የሃድያ፤ የኮንሶ፤  የአደሬ፤ የወላይታ፤ የሲዳማ፤ የኩናማ ወዘተ ልጆችም በማስተዋል ሆነ ማግስትን ማሰብ በእጀጉ ያስፈልጋል። ሁሉም በአንድነት ለተስፋው ዘብ መቆም ይኖርበታል።


ከሁሉ ያስደሰተኝ ጅጅጋ የገባው ሠራዊት እንደ ቀደመው ብሄራዊ መንፈስ እንዳለው ሳደምጥ እጅግ ተጽናንቻለሁኝ። ይህ መንፈስ ከቀጠለ የአብይን ሌጋሲ የማስቀጠል እቅም ሁሉ ይኖራል። ሌላው ድንቁ ነገር ሁለቱም ብፁዐን ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ አባታቾም ከልጃቸው ጋር ዓይን ለዓይን በድጋሚ ስለተገናኙ እጅግ ደስ ብሎኛል።

አብይ ካለዘመኑ የተፈጠረ ድንቅ የሰማይ ስጦታ ነው። እንዲህ የፖለቲካ ሊሂቅ ሆኖ መጠን በሌለው ንጽህና የተፈጠረ ሽልማት ነው። እኔ እንግዲህ ጭንቀታም ስለሆንኩ የፍርሃቴም ልክ እና ደንበር ስሌለው እንቅልፍ አልባ ነበርኩኝ። ሃይለኛ ድካምም አለበኝ። ሰውነቴም ዝሏል። በዚኸው ነገሬን ልከውነው። ይብቃኝ።

የሠራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሄር የሴራን አቅም ሰብሮ የ ብዩን ሌጋሴ ያስቀጥልልን።


የኔወቹ ትንፋሼ ተመልሷል በተወሰነ ደረጃ። ለብ ያለ ጥሩ ስሜት ተሰምቶኛል። ትጋታችን እንቀጥል፤ እንበርታ። ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።