ንቅ።
እንኳን ደህና መጡልኝ።
***
„ይህን ጣዖት ማግኘት የሰውነት ጥፋቱ ነው።
ከጥንት ጀምሮ አልነበረምና
ለዘላዓለሙም አይኖርም።“
መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፲፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.01.2019
ከእመዝምታ
- ሲዊዘርላንድ።
የዘመን ማቅ
ዝ - ብ - ር - ቅ - ር - ቅ
ዘመናዊ
መብረቅ
የፍግ
ድቃቅ
ንቅ ----- ነው ------ ንቅ።
የትወልድ ስንጥቅ
ጥ - ቃ - ን - ጥ -
ቅ
የሲኦል ምሩቅ።
ተስፋን
የሚያርቅ*
የተምች መረቅ፣
የልዩነት ልቅልቅ
የቅንባ ዝንቅ
ስ - ል - ቅ - ል -
ቅ
የሲኦል ምሩቅ።
አባይ ውልቅ
የፍዳ
ንቅ
የክህደት እምቅ
ስ - ን - ጥ - ቅ -
ጥ - ቅ
ከሱ ጋራ አንልም ከቶ ዝንቅ!
ይበል
ድቅቅ
ወያኔ
በለቅ
የነጣ ድርቅ።
ነፃነት አውልቅ
ንቅ
---------- ነው ------- ንቅ
ክብርን አማቅቅ
ሞገስን አድቅቅ
ትቢያ! ያ … ልበ - አውልቅ
የሲኦል ምሩቅ።
·
*የሚያርቅ“
… ሲጠብቅ እና ሲላለ
ሁለቱንም ትርጉም ይዞ ነው አባልተኛ የሆነው
ከትህትና ጋር።
·
„አባይ“ ላልቶ ነው የሚነበበው ዋሾ የሚለውን
ትርጉም ይዞ - ከትህትና ጋር።
·
ተፃፈ ሚያዝያ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ሄርሸን ሆቴል ሲዊዘርላንድ
·
ተስፋ መጽሐፍ ላይ ለህትምት የበቃ።
·
እርዕስ የሲኦል ምሩቅ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ