ያተላ፤
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ያተላ
„የተሰራው ሥራ ከሠሪው ጋር ይፈረድበታልና።
መጽሐ ጥበብ ፱
ቁጥር፲“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26.01.2019
ከእመዝማታ ሲዊዘርላንድ።
ያተላ
እኔ አለሁኝ ያለ
እንዲህ የዋለለ።
ዕውነትን አፋጦ
ሃቅን አጠቆረ።
ባንቃሩ ቧርቆ
ያ- መልቲ መንጠቆ።
ዬት አለ ጠንጋራው?
ሕሊና ሸውራራው።
አለሁ ቢል አያምር
የቅርጥምጣሚ ድር።
ሰበራ ሰንጣራ
ጋሬጣ ዘርዛራ።
ለዕውነት የማይራራ
ከፋፋይ ጠንባራ።
ዳጥ እና ደንባራ
ለእናት የማይራራ።
የትውልድ ገራራ
የዘመን ነህራራ።
ፈረፈር ነው ቡላ
ኩረት ነው ገለባ?
ቅራሪ -ያተላያተላያተላያተላ -
በክህደት የተላ።
ገ ነ
ራ ብ
ራ ራ
መርዛማ
... ብ ር ብ ራ
·
ተፃፈ ሚያዝያ፣ 16/2001 ሄርሽን ሆቴል።
·
ተስፋ መጸሐፍ ለህትምት የበቃ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
የኔዎቹ
ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ