የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን!
እንኳን ደህና መጡልኝ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አማኑኤል። አሜን! „ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 30.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ከሰሞናቱ ከተደመጡት ሃዘኖች አንዱ የዶር ነጋሶ ጊዳዳ ህልፈት ነው። አስደንጋጭ ነበር። ድህነትን መውደዳቸውና መፍቀዳቸው፤ ክብር መጸዬፋቸው፤ ሥልጣን በቃኝ ማለታቸው፤ እንደማንኛው ተርታ ዜጋ ሆኖ መኖርን መውደዳቸው፤ ግልጽ በሆነ ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ሄሮድስ መለስ ዜናዊን በድፍረት መሞገታቸው፤ ኢትዮጵያንም የሙጥኝ ብለው በቀዮዋ እስከ ህልፈታቸው መኖራቸው፤ ትዳራቸውን አክብረው መዝለቃቸው፤ „ከንቱ በሆነ ህይወትህ ዘመን ሁሉ ከፀሐይ በታች በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።“ ይቅርታ የኢትዮጵያ ህዝብን ዝቅ ብለው መጠዬቃቸው የሚያስመሰግናቸው ጉዳይ ነው። ልዩም መክሊት ነው የታደሉት ብቻ የሚያገኙት። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ የበቀል ፖለቲካ በመሆኑ በቀል እስኪበቃቸው የከተከታቸው፤ ግን ያነን ተቋቁመው ሁለተኛ ስደትን ሳይመኙ እዛው በአቋማቸው ጸንተው መዝለቃቸው ሌላው ጸጋቸው ነው። ወላጅ አባታቸውም ይህን መሰል ጽናት እንደነበራቸው እና እስር ቤት ሆነው ግን ሃኪም ቤት ተኝተው ጃንሆይ ከእስር እንዳስፈቷቸው ሁሉ ከአንድ ሃይማኖታዊ ቃለ ምልልስ አዳምጬ ነበር። ጽናት የቤተሰብ ነው ለማለት። በተ...