የኮንፌደሬሽን መንፈስ እና የሪፓብሊክ ሩኽ የዛሬ ፍጥጫ።

እንኳን ደህና መጡልኝ
የኮንፈደሬሽን
መንፈስ እና
የሪፕብሊክ ሩኽ የመጀመሪያው ታሪካዊ ስብሰባ ማዕልት።
„ልጄ ሆይ የእግዚአብሔርን ተግሳጽ አትናቅ።“
መጽሐፈ ምሳሌ ፪ ቁጥር ፲፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
                              https://sergute.blogspot.com/2019/04/blog-post_13.html
                                                        

              የነገው አስኳባ የከንቱ ውዳሴ ካባ። 13.04.2019

                                ውዶቼ ወደ ዕለቱ ጉዳይ ከመዝለቃችሁ በፊት ይህችን ወግ አንድ በሏት። 
                                                ፎቶው አሳምሮ ይናገራል። አስኮባ ነበር ተድሮ የዋለው።
                                                  
                                          https://www.youtube.com/watch?v=Ku8288BlRR0

                                    Good job addis ababa - ,ቅድሚያ የኦነግ ወንጀል እና የህዝብ 

                                     ስጋት ላይ እርብርብ ይደረግ ስጋታችን አንድነታችን ነው ።



እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? እንዴት አደረጋችሁ ይሆን የአስኮባው ሰርግ ጉዳይ ዛሬ መልስ ያለ ይመስለኛል። ሰርግ ሲኖር ሰውነት ድቁስቁስ ይላል አይደል ስትራፖ ነገር? ለዛ እኮነው እኔ ትናንት ደክምክም ብሎኝ ሳልችል የቀረሁት። ደቆኝ!

እንዳልኩት ነው የሆነው አስኮባ ነው ገበርዲኑን፤ ሙሉወርዱን ለብሶ ሲንጎራደድ 
የታየው። ይልቅ አማራ ትግራይ ክልል ሠርጉን አልተቀላቀሉም ሲባል አዳምጫለሁኝ። ለነገሩ እራሱ እዬነደደ በግራ በቀኝ ሙጌራ ላይ እዬተቀቀለ በምን ክፍት ቦታ አግኝቶ ብአዴን ወደ ሠርጉ ጎራ ይበል? ለነገሩ እንደ እሱ እኮ ሠርግ ላይ የባጀም የለም? ካባ ተክሊል ሙሉወርድ ጃኖ ሲገዛ ነው የባጀው። እንደ ብአዴን አቀባበል እና አሸኛኘት የባጀበት የለም። 

ርዕሰ መሰተዳደር ለማ መገርሳ ኦሮሞን አንድ መንፈስ አድርጎ ጫና ፈጣሪ ለማድረግ ሲታትሩ ሌት እና ቀን ሲባትሎ እነ ርእሰ መሰተዳደር ገዱ አንዳርጋቸው ደግሞ የፌድራሉን የዲሞክራሲ ስፋት አስጠባቂ ባልድርሻኛ ሆነው፤ ገመና ከዋኝ ሆነው ከፍ እና ዝቅ ሲሉ
ነው የባጀት አሁን እንደ አካፋ አሮጌ ዶማ ተወረወሩ እንጂ ... 

አገር ለመገንባት ትልቅ ተልዕኮ ይዘው የዴሞግራፊ ፍልስፋና እዛው መዲናዋ ላይ ሲተረጉሙ የኦሮሞ ሊሂቃን፤ ባሊህ ባይ፤ ሃይ ባይ አልነበራቸውም፤ ሌላው ቀርቶ 
ቧንቧው የኦዴፓ ሰው አቶ ንጉሡ ጥላሁን ፍቺውን እንኳን ለእናት ድርጅታቸው
ሊያሳውቁ አልደፈሩም … ለነገሩ የልብ ናቸው። ማተባቸውን መበጠስ 
አይጋባቸውምና ለገበሉለት ተልዕኮ።

·       ሬን ያዬ …

ዛሬ በትግራይ ኮንፈደሬሽን እና በኦነግ መንፈስ የሚመራው ሪፕብሊካዊነት የመጀመሪያ የቁጭታ ምክክራቸውን ያካሄዳሉ። ህወሃትን መንገድ መርቶ ደርግንም አብሮ ደልቆ ደቁሶ ለንግሥና ያበቃው የትናንቱ የኢህአፓ ቅርንጫፍ የዛሬው ብአዴን ታሪክ ራሱን ደግሞ „በጣና ኬኛ“ ድምጽ አልባ ጦርነት ልቡን አስረክቦ በጃውርውያውያን እና በዳውዳዊ መንፈስ ለመመራት ከፈቀደበት ዕለት ጀምሮ ፈንገጥ ብሎ የተገኘው ያው በአስኮባው ሠርግና መልስ በታሪካዊው 14.04.2019 ሰንበት ላይ ነው። የመስተፋቅሩ ጉዳይ ባለቅኔዎች ይሂዱበት ... 

የሚገርመው ሌላው ታሪክ ተደግሞም ህወሃት ብቻዬን ይህን ያህል ድል አጎናጸፍኩኝ ሲል እንደተደመጠው አሁንም ኦዴፓም ከሞት አተረፍን እኛው ድሉን አመጣን እያለ ነው>> እነ ቁጭ ይበሉ ብአዴኖች ደግሞ እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶማ የለመደባቸውን የበታችነት ዘመን ድገመኝ ብለው እዬከሰከሱ ይገኛሉ … ጥሟቸዋል። 

እንደዘመኑ በቀዝቃዛ ዝምታ የተዋጠው በግራ ቀኝ ተጠቃሚው፤ ምንም ሳያባክን የድል አጥቢያ አርበኝነቱን ማህተመኛው ደህዴን ደግሞ በዘመነ ህወሃት ብዙም ያልተጎዳ አሁን
 ደግሞ ራሱም እዬተናደ ግን ሐሴት ላይ ውቂ ደብልቂ እያለ የሚገኝ ሲሆን ትናንት ብቻ ሳይሆን ሁሉቱን ሳምንት በሙሉ የልቤ ተብሎ ሠረጋለ ሲቀርብለት፤ ስጋጃ ሲነጠፍለት የሰነባበተ የእግር ሚዜ ነው በኩሸኛ ምት።

በአሁን የሪፕብሊክ እና የኮንፌደሬሽን ስብሰባ ዋና ባለድርሻ ሆኖ በኩሽኛ የፊደል ገበታ አቋሙን አስተካክሎ ይገኛል ብዬ አስባለሁኝ የውስጥ ጌጥ ባለሟል ሆኖ ስለሰነባበተ። ሙሉ ድምጹም ለኩሸኛው ቤተኝነትን በማወደስ ይካነዋል ብዬም አስባለሁኝ። ዓይኑን ጭፍን አድርጎ በአዲስ ወግ የተረከውን ይደግመዋል። የዴሞግራፊ ለውጡም፤ በፌድሬሽን ምክርቤት የነበረው አጤነትም ስለመናዱ ጉዳዩ አይደለም ለደህዴን ጉዳይ። የለት የለቱን ባይም ነው … ልዝ እንጨት ወይ አይነድ ወይ አያነድ … ? በዚህ በለወጥ ጉዳይ እኮ
አዋሳ መሄድ ቀረ እኮ ... 

አቤቶ የኮንፈዴሬሽኑ ተደራዳሪ ህወሃት ዕድለኛ ነው ዛሬ ላይ። በራሱ ተፈትኖ የወደቀ 
የኦዴፓ ድርጅት አገር እዬመራ ስላለ። ለዛውም ኢትዮ አፍሪካን መናህሪያ አልባ አድርጎ አህጉራዊው ድርጅቱ በስጋት ሌላ ቦታ እንዲሄድ ወሳኝ አቋም የያዘው አዴፓ ጋር ሙግቱን መሰረት ለማስያዝ የሚቸግረው የሃቅ እንክብል አያጣም አይዋ ህወሃት። የቀበራት ፈንጅ ሥራዋን ሰርታለት ኦዴፓ ሰተት ብሎ ከወጥመዱ ገብቶለታል ከመሰመሩ።

ስለሆነም በሚያነሳቸው ወቀሳዎች ፋክት አቅርቦ ለሞገት አቅም ይኖረዋል ብዬ አላስብም ኦነጋዊው መንፈስ የተረከበው ኦዴፓ። መቼም ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ከቦታው ከትውልዱ ነቅለህ ዴሞግራፊ ፍልስፍና ዕውን ከማድረግ በላይ ሉላዊ ወንጀል የለም እና።

ይህም ብቻ አይደለም ህወሃት ያሰናዳት ቦንብ ፈንድታ አንዲት አገር ርዕሰ መዲና አልባ የሚያደርገው መግለጫም ምንም የማያወላዳ የውድቀት ከረባት ነው። ይህን የፋክት ጭብጥ አንደበትን የሚያዛጋ ገመና ተሸክሞ ኦዴፓ አሸነፊ እሆናለሁኝ ብሎ ማሰብ 
ያለበት አይመሰለኝም። ኢትዮጵያን ያህል አገር ተረክቦ ኮንደምንዬም ሥር መገኘቱስ?
 ህግ ጥሶ፤ አዲስ ህግ ቀርፆ ከንቲባ መሾሙስ፤ ለወሰን ድርድሩን አንዱን ተደራዳሪ 
ሌላውን ተደራዳሪ የራሱን ድርጅት አድርጎ በ ዓለም የሌለ 8 አባላት ያሉት ኮሚቴ በሥልጣኑ ማቋቋሙስ?

የጌዲኦ ቀራንዮን ሲታከል ትንፋሽን ሰንጎ ይይዛል። የባስኬቶም ማንም ምንም ያላለበት የመከራ ቁልል ነው። አማሮም ፍዳውን እያዬ ነው ከጥቅምት ጀምሮ። የአማራው መከራ ግን ኦዴፓም ህወሃትም ሁለቱም የሚሰማሙበት፤ ማህተም የመቱበት ስለሆነ ከአጀንዳ የሚጣፍ አይደለም። ተረዳድተውም ነው የከወኑትና። ኦዴፓ በወሰዳቸው የማጥቃት እርምጃዎች ሁሉ አማራ ላይ እንጂ ተጋሩ ላይ አልቃጣትም። ያለው ይፈራልና።

እም!የለገጣፎ የግርዴር ውሎም ሌላው የማይደፈር አመክንዮ ነው  … "ስደተኛ መጤ ሰፋሪ" ቃሉ ራሱ ፍርድቤት የሚገተር ጉዳይ ነበር፤ መንግሥትም ህግም ኢትዮጵያ 
ቢኖራት። … በሄሮድስ መለስ ዜናዊ በፎርፌ የተባረረው ኦነግ አቅም ማግኘት እና 
በተሟላ ትጥቅ አገር ማመሱም ነፍሱ ሐሴት ላይ መሆኑ ህወሃት ኦዴፓን የመሞገት አቅሙን ያፋፋለታል። 

ከሁሉ በላይ ያ ሊደፈር የማይችለው አብይወለማ ድጋፍ ሁነኛ ወገንተኛ
የኔ ባይ መንፈስ ባለማግኘቱ ስለተገፋም ዛሬ ላይ የወለሌ ገበታ እያለ ስለሆነ ይህ 
የአቅሙ ክናድ ይሆንለታል ለባለ ኮንፌደሬሽኑ ለህወሃት። ጥንቃቄ አልቦሽ ጉዞ ብቻ
ሳይሆን ስውሩ ገማና ከሌላው ቀድሞ ራስን ነው የሚንደው። እግዚአብሄር ያያል፤ ይፈረዳልም፤ የሰማዩ ቁጣም አለ ... 

ሰሞኑን ሻ/ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የሞገቱበት አመክንዮ እንደ አንድ አብዮት ሊታይ የሚገባው ነው … በዚህም በዚያም ኦዴፓ ሸጉጦ የተሸከመው ገማናው ባመጣው 
ጣጣ ሁላችንም መንፈሳችን ሸፍቷል። ይህ ህወሃትን ለመሰለ ጉድጓድ ድርጅት 
አቅሙን የሚያጎለብትበት መቅኖ ነው። ልዩ ዘመኑም ነው። ህወሃትን እንደገና 
ወደ ስልጣን መጥቶ ህዝብ ይቀበለዋል ብዬ ባላሰብም። 

በራሱ ውስጥም ረመጥ እንደርታ ላይ እዬተንተከ ከመሆኑም በላይ ከስህተቱ ተምሮ ባለፈው አንድ አመት የጎዳውን፤ ያቆሰለውን፤ የዘረፈውን፤ የወረረውን ለመመለስ
የወሰደው ቅንጣቢ እርምጃ ስሌለ በዛው በዛገ መንፈስ መልሶ ወርቅ ሆኖ ለመውጣት
 አቅም አይኖረውም።

ወደ ቀደመው ምልሰት ስናደረግ ስለዚህ ህወሃት አገር እኔ መምራት እችላለሁ ብሎ ሊያቀርብ የሚችለው አቅም ሽሁራር የበላው ቢሆንም በፋክት ግጥሚያ ግን 
ህውሃት ህሊና ላለው፤ በፋክት ለሚያመልክ ሰብዕን ብዙ ጭብጦችን እያቀረበ
ኦዴፓን ማንከረባበስ ብቻ ሳይሆን ጢባ ጢቦሽ ሊጫወትበት ይችላል።

ይልቅ በማነሁለል አባዜ እንደ ሰሞናቱ የኦሮምያ መስተዳደር የክህደት የለበጣ ጉዞ
በዛ የሚማልል ከተገኜ … አንድ መንገድ ሊኖር ወይንም አንድ ዕድል ሊሰጥ ይችል
 ይሆናል … ለጃዋርውያኑ መንፈስ ልቅና … ለኦነጋውያን የህጋዊነት ሌላ ስርትፍኬት። አማራጭምም የለምና ... ማን አለ ቀድሞ ነገር? 

ሌላው ግርም የሚለኝ ይህ የ ኦነግ ብር አንባር ዘመን ኮንኖ የተነሳ አንድ ሊሂቅ የለም ከኦሮሞ ይህን አውግዞ የሚነሳ ...አላዬሁም። ሌላው ልባም ነገር ግን ኦፌኮ አለሁ አይበል። መድረክም እንዲሁ የሰው ዘር ከተጻረረ መንፈስ ጋር አብሮ የሚቆመው
ሲኦል ወይንም ዲያቢሎስ ነውና። አንገታቸውን ቀጥ አድርገው ፕ/ መራራ ጉዲና
 ሲተቹ ይገርመኛል፤ ሰውም ያን ተከትሎ ሲደግፍ ይገርመኛል። ኦፌኮ ከኦነግ ጋር
 አብሮ ለመስራት ተስማምቷል። በዛ ላይ ኢ - ተፈጥሯዊ፤ ኢ - ሰዋዊ የሆነውን 
ም/ ተቃዳሚ ሊቀመንበሩን ይዞ ነው አሁንም ተዋናይ ሆኖ ያለው። አዬ ኢትዮጵያ
 እንዴት አንድ ቅን ንዑድ ልጅ ታጪ?  

ወጥ ወረርሽኝ የበታችነት ስሜት ባይረስ ...


ኦዴፓ የያዘው መንገድ አገር የሚያድን ሳይሆን እጅግ አስፈሪ የጭካኔ መስመር ላይ ሰለሚገኝ መንፈስን ለመፍቀድ ከባድ ነው። መታበዩም፤ ልክ ማጣቱም፤ በዬሰከንዱ የሚቀያይረው የማልያ ዓይነትም እንደ አገር መሪ ነኝ ብሎ ሊያስፎክር የተገኘው
ውጤት እና የቀረውን ለማመጣን የሚያስችል የተባ አምክንዮ ማቅረብ አይቻልም። 
እኔ የኢትዮጵያ መንግሥት ከምለው የኦነግ መንፈስ ገዢ የሆነበት ሙት ዘመን ብለው ይቀለኛል። 

ኦዴፓ የራሱን ወዘተረፈ ወንጀለኞችን እንዳይጠዬቁ በማድረግ ንጹኽን በመከስ፤ በመወንጀል፤ በማሸማቀቅ፤ በማስፈራራት አንደበት በመዝጋት ላይ ነው እዬተጋ
 ያለው። ቄሮን አሰልፎ በመንግሥት ተጠያቂ እንዳይሆን፤ በትጥቅ ትግል ኦነግን
 እያጠተናከረ ነው አቅሙ ሆኖ እንዲወጣ እዬተጋ ነው ያለው። አብሶ የኦሮማማ አምላኪዎች ላልሆኑ የሚከተለው ግልጽም ስውርም መንገድ አስፈሪም ነው።
ሰውኛ ጠረን የለውም። ይህን ፋክት መድፈር ግድ ይላል እንደ ሰው። 

ችግሩ ማን ይተካል የሚለው ነው? ዙሪያ ጥምጥም እኔ አሰብኩት እና ታከተኝ … ተፎካካሪ ከሚበላውም እከሌ የምለው ነው ያጣሁት። ይልቅ ጮሌው ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ትናንት ምርጫ በሚካሄድበት ቀበሌ ስለመገኘታቸው ደግሞ ተደምጧል።

ግን እሳቸው ምን ዓይነት ሰው ናቸው? መቼ ይሆን ይህ የሥልጣን ሱሳቸው የሚገታው? በአንድ በኩል ለውጡ መሰረት እንዲይዝ ነው የምንሠራው ለሥልጣን አይደለም ይሉናል፤ በሌላ በኩል ጥረት የሚያደርጉትን ያወግዛሉ፤ የሥልጣን ነገር ሲመጣ ደግሞ ቀደመው ይጣዳሉ …የካታሊስትነት ባህሪ ነው እኔ ያዬሁት። በውነቱ ያደክማሉ።

ዛሬ በአዲስ አበባ 23ቱም የምርጫ ወረዳዎች ላይ የተሳካ ምርጫ ተከናውኗል::
/ ብርሃኑ ነጋም እንደማንኛውም ተመራጭ በወረዳ 23 ምርጫ ተሳትፈዋል

ስለ ፕ/ብርሃኑ ነጋ መቼም ይህ በጥልቀት ቅኝት ቢደረግበት ሁለማናቸውን የሚያሳይ ይመስለኛል ይህ ሰንበት ላይ የሰሩት ድራማ ደግሞ ሌላው እሳቸው ናቸው የጠ/ሚር አብይ አህመድ ሥልጣን ቢቀጥል እሳቸው ከንቲባ የመሆን ውል ያሠሩ ያስመስላል …

ለዚህም ነው የባልደራስን ንቅናቄ ቀዳሚ ተቃዋሚ ሆነው የወጡት ብዬ አስባለሁኝ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቢወዳደር ይረታኛል ብለው ስላሰቡ … ስለሰጉም … በሌላ በኩል ለኦዴፓ እንቅስቃሴም እውቅና የመሰጠት ነገር ነው። ሌላው የህዝብ ሰቀቃንም ጉዳያቸው አይደለም።    

ግን እንደ ፖለቲካ መሪነታቸው እንደ ተልቀው ወይንም ገዝፈቅ እንደሚታዩበት
 ሰብዕናም ልካቸውን ለማግኘት ጥናት ይፈልጋል … 

Ethiopia:Ethiopis ቄሮ እና ፖሊስ እንቅፋት የሆኑበት የባለአደራው ስብሰባ - ቄሮ በኮኮብ አዳራሽ

የባለአደራው ጋዜጣዊ መግለጫ ክልከላ-(ራስ ሆቴልበድብቅ የተቀረፀ Ethiopia: Ethiopis


ቄሮም የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ስብሰባ ለማወክ እንደተነሳው ፕ/ ብርሃኑ 
ነጋ በተገኙበት በዚህ ቦታ ተገኝቶ ህወከት አለመፍጠሩ በመንግሥት ደረጃ ያለ 
የተከደነ ስምምነት እንዳለ ምልክት ይሰጣል።ግን ፕ/ ብርሃኑ ነጋ ከማን ጋር ይሆን 
እዬተፎካካሩ ያሉት? መቼስ ነው ይህን መሰል ድርጊታቸውን አቁመው በሰከነ
 የፖለቲካ ፍላጎት ርጋ የሚሉት? በመከራው ሳትገኝ? ልጆቹ አደባባይ ሲረሸኑ፤ ጦለይ በቀል ሲበላቸው?   

እኔ በዚህ እርምጃ የተመለከትኩ ወሳኝ ነገር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በቅንጅት ጊዜ 
የነበራቸው ሚና እና የወሰዱት እርምጃ እራሳቸውን የወቀሱበት ጉዳይ እንዳላቸው
 ነው። ያን እድል በወሳኝ የመሪነት አቅም ለድል ሳይበቃ መረራ ስንብት ማስደረጉ የተከፈለው መስዋዕትነት፤ መልሶም በቁጭት ለማምጣት ግንቦት 7 መስርተውም ካለምንም ውጤት በበዛ መስዋትነት ከንቱ ሆኖ መቀረት የጸጸታቸው ይመስለኛል።

ግን ተሳሳትኩ ብሎ ለመናገር አይደፈርም። ብዙ መንፈስ ተንዷል እና። ሃላፊነት እና ተጠያቂነት ላይ ወገቤ ነው … የሁሉም ሊቃናት ችግር ነው ይሄ … እራስን በመወቅስ ረገድ። በዬትኛውም አገር የፖለቲካ ውድድር ምራኝ ብሎ የመረጠህን ህዝዝብ ከመረጠህ በኋዋላ ልግባ አልግባ ተብሎ አይጠዬቅም። የድርጅት እውቀት ማነሰ ወይንም የመርህ አፈጸጻም ስስነት ነው። ከመረጠህ ቀጥ ብለህ መግባት ነው። በቃ። ያ ትልቁ ግዙፍ ግድፈት ነበር በዘመነ ቅንጅት ... 

ብቻ ጥሩ አጋጣሚ ነው እሳቸውን ሲሞግቱ ለነበሩ መንፈሶች ድል አነባብረውላቸዋል። አሁንም አኮ ያው የህወሃት ህግ መንግሥት ነው። መሪዎችም ኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ናቸው። ነፍሳቸው በዛ የተቃኜ .. 

የመብራቱ ብልጭ ድርግምም እኮ የዛው አይዲኦሎጂ ጣጣ ምንጣጣ ነው>> ግን ስንት ዓመት ሲኖር ነው የአዲደስ አባባ ተመራጭ ለተወዳዳሪነት የሚታጨው? በዚህም መስመር ቢኬድ ከመርህ ጋር ግጭት ይፈጥራል። ይህም ከመርህ አንጻር ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት ትልቅ መሪ ሞጋች ጉዳይ ነው፤ ልጣስ ካለ ብዙ ነገር ስለሚናድ … ከዚህ ጋር ለህግ የበላይነት እንታገላለን ዶግማም አፈር ድሜ ነው የሚግጠው ...ሁልጊዜ መወደቅ የማይታክተው መንፈስ ... አጀብ ነው ...   

ወደ ቀደመው ጉዳዬ ምልሰት ሳደርግ የራሱ ማንነት ያልተፈቀደለት፤ የራሱ ጠባቂ የሌለው የእንጀራ ልጁ የአዲስ አባባ ነዋሪ ደግሞ አንድ ጤነኛ ተቆርቋሪ መንፈስ ቢኖረው እሱም ሰብሰባውን እንዳያካሂድ ተገድቧል። የሚገረመው  ለእሱ ደህንነት ተቆርቁሬ ነው ያለው የአንድ አገር መንግሥት አዛዦቹን ከቦታው ድረስ ልኮ ስብሰባው እንዲቀር በፈለገው 
ጊዜ ደግሞ አስደርጓል። በዚህ ውስጥ ዴሞክራሲ? ፌዝ ነው። ወይንም የልግጫ ርግጫ … ወይንም የፍጥጫ ልጥጫ …  እኔ ከኦነግ የምጠብቀው የነፃነት ፍርፋሪ የለም። 

·       ን …

አሁን ማነው ኢትዮጵያን እዬመራት ያለው? ማነው አገረ ገዢው? ተደራዳሪውስ ማነው? ከማንስ ጋር ነው ድርድር የሚደረገው? ሾላ በድፍን ነው ነገርዬው …

እኔ እንደማስበው የአሁኑ የኢህአዴግ ስብሰባ ኮንፈዴሬሽን ትግራይ በ አንድ ረድፍ፤ በሁለተኛው ረድፍ ብህአዴን ደህዴን ድርድር በተመልካችን የሚያደርጉት ሲሆን ተደራዳሪው አጤው ከቄሮ ነገሥታት ጋር ይሆናል ማለት ነው። አዲስ አባባ ድረስ ገስግሶ ስብሰባ የሚያግት አቅም? ወቼ ጉድ እንዴት ተቀለደ? ውይይቱም፤ ተቃውሞውም፤ ድጋፉም ከዚህ አንፃር ነው የማዬው እኔ።

ሰብሳቢው አቶ ጃዋር መሃመድ በመንፈስ ጉብ ብለው ከዙፋኑ ላይ፤ ጸሐፊው ደግሞ
 አቶ ንጉሡ ጥላሁን በዚህ ዓውድ ኮንፌደሬሽን ትግራይ ነፍስ እና ሪፕብሊክ ሩኽ ቄሮ አብረው ቁጭ ብለው ይወያያሉ ማለት ነው። ሌላው ደህዴን እና ብአዴን ደግሞ ለጭብጨባ ወይም ስጋጃ ለማቀበል ... ወይንም ለችርስ ... ቀድሞ መረጃውም የሚሰጠው ለአቶ ጃዋር መሃመድ ይሆናል ማለት ነው። የፕሬስ ሰክሬታርያቱ እስካሉለት ድረስ ... ምን ሲገደው። 

አገር ምድሩ ኦሮማማ ድልነት ነው የሚነገረን። ሊሂቃኑ በሌቲቢ የሚስታውሱን ይኽንኑ ነው። የ ሮሞ ሊሂቃን በዬለቱ ርችት በርችት ላይ ነፍሳቸው ጥፍት ብሏል። ስለዚህ እነሱ ሪፕብሊካቸውን እዬገነቡ ስለሆነ መደነቅ አይገባም። ሌላው ከኮንፌዴሬሽኑ ከትግራይ በስተቀር ለሪፕብሊኩ ምሰረታ አስፈላጊውን ቁስ፤ የመንፈስ አቅም በማዋጣት በመደገፍ ሰጥ ለጥ ብሎ ሲያሟላ ነው የባጀው። 

መቼም በዚህ የነፃነት ተጋድሎ ዘመን አንድ ነገር ኮሽ ሲል ላጥ እያሉ ከሚገቡት ከሚወጡት፤ ወይንም ከሚከስሙት ዘንድ ያልሆኑ በንጽህና ስለነፃነት በጽናት የተጉት 
ሁሉ አቅማቸውን ሁሉ ለአጤ ዳውድ ኢብሳ እርክክብ እንደፈጸሙ ልብ ሳይሉት አይቀርም እኔም አለሁበት። ቅንነት አቁማዳ ሆኖ ነው የተሰፋው ዘንድሮ ነው። ክህደትም ዙፋን ደፍቶ የነገሠው። 

የሚገረመው አሁንም ይህን መንፈስ አትንኩት የሚሉት ነገር ነው እኔ የማይገባኝ። የዘላለም ጸጸቱን ከቻሉት ይቀጥሉበት። ኢትዮጵያዊ ጠረን እዬከሰለ ስለመሆኑ
 ማሰብ ያለባቸው ይመሰለኛል። አቅም ስታፈስ፤ አቅም ስትመግብ ለእኔ ይቅር
 ለእሱ ይሁን ስትል ከግለሰብ ባለፈ አገር የሚባለውን ትልቅ ነገር ማሰብ ይገባል።

እንደዚህ ዘመን መራራ ጊዜ የለም። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሁሉንም ትጥቁን አስፈትተው በመዳፋቸው ውስጥ ካስገቡ በኋዋላ ነው አሁን ያለው ትዕይንት እያዬን ያለነው። 

እኔ አራሱ ም/ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን ፓሲብ ሆነው ነው ያዬኋዋቸው።
ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ የህዝብን አኗኗር ስብጥር ለመቀዬር ያን ሁሉ ተግባር
 አፍንጫቸው ላይ ሲሟላ ለመሆኑ የት ነበሩ? አዲስ አባባ ላይ አንድ የቄሮ ሃይል
 ከሌላ ቦታ መጥቶ አንደበት ሊዘጋ ይህን ያህል ስልጣን ሲሰጠው የሳቸው ም/ጠ/
ሚርነት የት ላይ ነው?

እራሱ ፕሬዚዳንቷ የትላይ ናቸው ያሉት? የተመድ ከፍተኛ ሃላፊ ለነበረ አንድ ነፍስ
 ይህን መሰል ዓለምን የሚያናጋ ጉዳይ እዬገጠመ በዝምታ መቀጠል ምን የሚሉት
 ፈሊጥ ነው? ዲሞግራፊ እኮ በዓለም የተወገዘ ፍልስፍና ነው። ለመሆኑ ፕሬዚዳንቷ
 የጌዴኦ እናት ሶቃቃ አዳምጠው ምን አሉን?

የበቀለ ትእዛዛትስ ከተባባሩት መንግሥታት ምሰረታ፤ ከቀይ መሰቀል ምስረታ፤ ከአፍሪካ ህብረት ምስረታ፤ ከአውሮፓ ህብረት ምስረታ፤ ከአምንሲት ኢንተርናሽናል ምሰረታ፤ ከሰባዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ዓላማ፤ ከሃይማኖት ተቋማት ዶግማ እና ነገ ስለሚፈጥረው ቀጣይ የዘር ጭፍጭፍጫ በምን ተለይቶ ይሆን ዝምታቸው 
የክብርት ፕ/ ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ጉዳይ እንደ አንድ የሰብዕዊ መብት ተሟጋችነታቸው እንደ እናትነታቸውም እንደ መሪነታቸውም?

ችግር ሲደርስ በችልታ ታይቶ ችግሩ ካለቀ በኋላ ድንኳን በመጣሉ ጉዳይ የአንድ አገር ፖሊሲ ሆኖ በተከተታይ እዬታዬ ነው … ይህን እንደ አንድ አገር ፕሬዚዳንትንት እንዴት ታይቶ ነው ረጭ የተባለው?

ክብርት የፌድራሏ ከፍተኛ የፍትህ አናት ወ/ሮ ማዕዛ አሸናፊስ? በዚህ መስመር ሰብዕዊነትን ፍለጋ ስማስን አንድ ሰው አጣሁኝ። እና ዛሬም ነገም ከበደኝ
ማረፊያ ጥግ የሚሆን ነገር የለንም። በዚህ ማህል ኩዴታ ቢመጣ፤ በዚህ ማህል 
የውጭ አገር ወረራ ቢከሰት ምን እና ምን ሊኮን እንደሚቻል አላውቅም። 
ተዝረከረከ …

እኔ ምን ይሁን ምን የአሁኑ ጉባኤ እንደ አለፈው ጊዜ አላስጨነቀኝም። ስለምን
 ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ስለሆነ። ትናንት ኢትዮጵያ ሙሴ እንድታገኝ ታገልን። 
ዛሬ ሙሴው በዓመት ውስጥ በነፍስ ወከፍ፤ እንደ አገር መሪነትም መታመን፤ የቃል
 ጥበቃ፤ ቢያንስ ርህርህና፤ ቢያንስ የማድመጥ አቅም፤ ቢያንስ ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶች በእኩልነት የማዬት አቅም፤ ሚዲያዎችን ዜጎች እኩል በመንፈስ የማዬት ዝንባሌ የለም። አንዱ የክት ነው ሌላው የዘወትር፤ አንዱ የሚታደን ሌላው 
የቤተመነግሥት ሰው ነው። 

አብሶ በአማራ ላይ በስልት የሚሰሯቸው ነገሮች፤ የስሜን የፖለቲካ መስመርን 
ለማስመጥ የሚሄዱበት መንገድ ስልታዊነት ዱዳ ነው ያደረገኝ ስለሳቸው 
በአዎንታዊነት ለማሰብ።  

አትኩሮት እና ቀረቤታቸው ለማን እንደሆነ ሳስበው ክህሎታዊ ዕሴቱ ጥጉ ያጠርብኛል። ቁጭ ብዬ የደከሙባቸውን፤ እንቅልፍ አልባ የጣሩባቸውን ድካሞች በምልሰት አስብና
 እና የዛ ድካም መቋጫ ሳስበው ማመጣጠን ያቅተኛል።

ያው እኔም ፈተና ላይ ነው የባጀሁት ለማለት ነው እኔኔ እኔ እዬሞገተኝ። የመወሰን
አቅም፤ የማድመጥ አቅም የማስተካካል አቅም አለዬሁም። አዝናለሁኝ። ደከመ
 ደለ ባልኩት ሁሉ ከግንቦት 2010 ጀምሮ ስለሞገትኩኝ እዬደገፍኩም ጸጸት 
የለብኝም። አሁን ግን ተስፋዬ ተጨልጧል። 

ለጠ/ሚር አብይ አህመድ እርእሰ መዲና አልባ ለማድረግ ድርጅታቸው መሰራቱ ከምንም ነገር ሊወዳደር የማይችል ነው። ዴሞግራፊ ጉዳይም፤ ሰብዕዊ እርዳት እንዳይደረግ መታገዱ፤ የፌስ ቡክ ቡድንን አገር ቤት ጠርተው ያደረጉት መሰሪ ነገር መራራ ነው …
   
ቅብጥ እና ቅልጥ ፈስስ እና ሙልቅቅ ያደረግናቸው ሙሴያችን ነፍሳቸውን የሰጡበት መንፈስ ከድሮው ከዘመነ ህወሃት አማራ ጠል ትርክት የተሻለ ነው የምለው የለኝም እኔ በግሌ። ምክንያቱም  አንድ መሪ የሁሉም እናት ነው። የሁሉም ጉዳይ ያገባዋል። ያዬሁት የክት እና የዘወትር ነው። የቤተኝነቱ መሥፈርት በሚገባ ዓመቱን ሁሉ መደበኛ ሥራዬ ስለነበር አጥንቼዋለሁኝ። የሚፈለገው ደም የማን ስለመሆኑ አስረጂ አልሻም።

ስለዚህ ፈጣሪ የወደደው ይሁን ነው የምለው … የሚያጓጓኝም የምመሰጥበትም ሁኔታ አይኖርም። ድራማውን ለማዬት ግን ትኬቱን ቆርጫለሁኝ … እናንተስ ቅኖቹ? ትኬት አገኛችሁን? 

ይልቅ ትጥቁን የፈታው ዲያስፖራ ከድሪቶ ፓለቲካ የወጣ ነፍስ ያለው የተሰፋ
 ድርጅት ይፈጠርና ቢያንስ ፋክት ነገሮች ላይ አተኩሮ እንደለመደብን የሎቢ
ተግባሩን አህዱ ማለት ይበጃል። ሞት ላይ ሆኖ ሠርግና መልሱ የራውንዳ ትዕዛዛትን የገለበጡ በቀላውያን ባሉበት እጅን አጣምሮ መቀመጥ የሚበጅ አይሆንም …

ሌላው ግን የፖለቲካ ድርጅት ሊሂቃን አምኖ በእነሱ ምክንያት ማህበራዊ ኑሮን 
ከማወከም ከዚህ ዘመን በላይ መምህር ስሌለ ለራሳችን ሰላም ምንም ቀዳዳ ሳንስገባ ከግዙፉ ስህተታችን ተምረን ፈቀዳቸውን ፈጻሚ ሳንሆን አንድነታችን
 ማጠናከር ያለብን ይመስለኛል። እነሱ አሁንም እዬተረተሩን ነውና። 

እነሱ ከሞቀው ባልስ ባሰኛቸው ቁጥር አብረን ሚዜ የምንሆንበት ምክንያት የለም። ለራሳችን የውስጥ ሰላም መፍትሄዉ እኛ እንጂ የኢጎ ባለቁልሎች አይደሉምና። እነሱ ለተሰለፉት የሥልጣን የሥም እና የዝና መሰላል ሲተጉ፤ እኛ ራሳችን እያነደድን ስደት ከበላው ወንድም እና እህት ጋር ተቃርኖ ገብተን እምንታመሰብት መንገድ ሊኖር 
ከእንግዲህ አይገባም … ልብ እንግዛ … ሃሳብ፤ ዓላማ፤ ራዕይ ለሌለው ነፍስ ነፍስ አይገበረም፤ የውስጥ ሰላምም አይሸለም። ይኸው ዛሬ እኮ ይሻላል የሚባል ነገር ለማገኝት አልተቻለም …
  
ያው አሁን ደግሞ አዲስ ትወና ዲያስፖራ ላይ እንደሚኖር ስለማውቅ ነው ይህን
 የምለው። እኛ የራሳችን ህሊና በሰው ሳይሆን በፈጣሪ ተሰጥቶናል። መፍቀድ 
ያለብን ፈጣሪ በሰጠን ልክ ራሳችን ሁነን ለመኖር መቁረጥ ነው። ዕቃ እንጂ
 ህሊና ለሰው አይወረሰም።

የፈለገ ወጀብ ይኑር እውነትን አምኖ ለዛ መትጋት ይገባል። እውነት ሲኖር ብቻ ነው
አቅም ሊዋጣ የሚገባው፤ እውነት ከሌላ ማንም ይሁን ማንም ሊደገፍም አቅም
 ሊዋጣለት አይገባም። ለግድፈተኛ ጃኖ ማልበስ፤ ተክሊል ማቀዳጀት ድርሳን ማድረስ አይገባም። ስለመልካም ተግባሩ ተመስግኖ ስለ ድክመቱ ግን ሊገለጽለት፤ አቋም ሊወሰደበት፤ አቅም ሊነፈገው ይገባል። 

እኛ ዘመናችን ሁሉ የሰጠነው ኦነግን ያህል የኢትዮጵያ ጠላት ጉለሌ ተቀምጦ
ንጹሃንን እንዲያርድበት፤ ቤተመቅደሳችን እንዲያቃጥልበት አገራችን መናህሪያ
አልባ እንዲያደርጋት አይደለም፤ አልነበረም። ህዝባችን ጭንቅ ውስጥ ነው። ህዝባችን ፍርሃት ውስጥ ነው። ህዝባችን ስጋት ላይ ነው።  

በሌላ በኩል ሃሳብ አልቦሹ፤ ራዕይአልቦሹን የሌለው ያልነበረው በባዶ ሜዳ በተንከባለለ ቁጥር ለእሱ ድርና ማግ መሆንም አይገባም። ከሌለው ሃሳብ ቦታውን መልቀቅ ነው
እንጂ እንደ እርጎ ዝንብ በደመቀው ሁሉ ጥልቅ ባለቁጥር እኛ አብረን ዱብ ዱብ የምንለበት ምክንያት የለም። ኢትዮጵያ ከሃሳብ በላይ ናትና። ለሁሉም ነገር ህሊናን መንፈስን አረጋግቶ ማሰናዳት ይገባል። 



ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።