ፈሪነት …

 

ፈሪነት …

 

ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ሕይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራር።

„ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔረ

ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“

(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20)

 


ቢያንስ የሃሳብ አቅም አምጦ መውለድ ይቻል ነበር። በተነው የተበተነ ለመሰብሰብ አሁንም ለብታ የለም። ሃሳብ ይፈራል። ሞጋች ይፈራል። ሃሳብ ሞጋች የሚፈራው ገዢው ብቻ አይደለም። በትብትብ ውስጥ ያለው፤ ያልነፃው፤ ያልደነገለው፤ ያልቆረጠው ሰብዕና ሁሉ ነው ሞጋች ሃሳብ የሚፈራው መድረኩ ያለው ደግሞ እሱ ነው።

እንደ ድሪቱ ቢጣፍ፤ ቢደረት ችግሩ አፍጥጦ እዬገሰገሰ ነው። እዬዋጠ ነው። በዝምታ ውስጥ መክኖ መቅረትን የመሰለ መከራ የለም። መከራ። አወን መከራ። አገር እንደ ዋዛ? ሃይማኖት እንደ ዋዛ? የሰው ልጅ እንደ ዋዛ? ተፈጥሮ እንደ ዋዛ? ታሪክ እንደ ዋዘ? ትውፊት እንደ ዋዛ? ትሩፋት እንደ ዋዛ? ማግሥት እንደ ዋዛ? ትናንት እንደ ዋዛ? ዛሬም እንደ ዋዛ? የወዘኞች ዘመን? ሁላችንም ዋዘኞች ነን። ከዋዠኝነት የዳኑ ብጹዓን ናቸው እላለሁኝ። እኔው።

እራሱ የኃይል አሰላልፉ ዝንቅ፤ ቅልቅል፤ ያለዬለት፤ አሳቻ፤ አሳሳችም ነው። እንደ እኔ ሌላው ይታዬው ይሆን አይታዬው አላውቅም። እኔ ግን እማዬው ተዛነፍ ነገር ነው። ሚዛን የሚአስጠብቁ፤ የሚያስክኑ፤ ስንፈላ እና ስንበርድ ሙቀቱን አስተካክሎ ሊመሩ፤ ሊያስተዳድሩ የሚችል ቅዱስ መንፈስ ያስፍለገናል። ያልባለቀ ንጹህ ሰብዕና ያስፈልገናል። እንጸልይ። እንጹም። እንስገድ። አንደበታችን እንረም። እራሳችን እንቅጣ። ትዕዛዝ አይደለም። ትህትናዊ ማሳሰቢያ እንጂ። ኢትዮጵያ ታሳዝነኛለች።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

16.04.2021

ኦ! ኢትዮጵያ ሆይ ቀንሽ መቼ ይመጣ ይሆን? አሳዘንሽኝ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።