ኢትዮጵያውያን አብይ ሠራሸ አይደለንም።

 

 እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። 

·       ኢትዮጵያውያን አብይ ሠራሸ አይደለንም።

 

ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ሕይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራር።

„ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔረ

ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“

(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20)




የፈጠረን እግዚአብሔር ነው።

አገራችን ኢትዮጵያን የሰጠን አምላካችን ነው።

እኛንም አገራችንም የፈጠረ አምላክ አለልን።

ተስፋ እግዚአብሔር ነው።

ተስፋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ ይገባል።

ኃያል አምላክ አለን። ተመስገን።


ማህጸን አለኝ ሳይሉን ይቀራሉን ዶር አብይ አህመድ አሊ?

 

እኔ እንማስበው ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የነገሥታቱን ታሪክ፤ የፀሐፍትን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ እኔ ሠራሁት እያሉን ነው ያሉት። ከውስጥ ሆናችሁ ስታዩት። ኢትዮጵያንም እኔ ሠራኋት አይቀሬ ነው። እሱ ብቻ አይደለም አይድነቃችሁ የአብይዝም ትውልድ እንዳለ በህሊናቸው ዳንቴል ውስጥ ያምናሉ። እኛንም ጠፍጥፈው፤ አንቦልቡለው እንደ ቀረጹን ነው የሚያስቡት።

 

ለዚህ ነው ጋልበው ጋልበው እርገቱ ዲያስፖራው የሚሆነው። ሎቢስት ቅጠሩልኝ እኮ ከሰሞኑ ተደምጧል። ያን ጊዜ 100 ቀን ሳይሞላቸው ነበር ስሜን አሜሪካ ለመውጣት የተጣደፉት። ለምን ተጣደፉ ብሎ የጠዬቀ የለም? እሳቸው ያጎደሉት ነገር የለም። የጎደልነው እኛ ነን። ከሥር ሳይሆን ተንሳፈን የምንገኝ።

 

በሳቸው የኢማጅኔሽ ዓለም ነው ሁላችንም ታቁረን ያለነው። ግጭቱ ይህ ነው። ጦርነቱ ይህ ነው። ቆይተው ማህጸንም አለኝ ሊሉን ይችላሉ። ጾታቸው ስርንቅ ፍላጎትን ያከማቸ ነው። ለዚህ ነው አሳቻ ናቸው እምለው። ዘመኑን ለማንበብ ከሳቸው የሰብዕና አወቃቀር መነሳት ይጠይቃል። ከዛ ቀጥሎ የገዳን አስተምኽሮ። ይህን ዕድሜ ለሊቃውንቱ ለዬኔታ ፕ/ሃብታሙ ተገኜ ዘመኑን ገልጠውታል። ለዚህም ነው የመገለጥ ዘመን የምለው።

 

ግን ሠራንበትን? ግን ተጠቀምንበትን? ግን ማንፌስቷችን እንዲሆን ፈቀድንለት? በማወቅ ውስጥ ነው ማስበል የሚገኜው። በማወቅ ውስጥ ነው መብት እና ግዴታን ማወቅ የሚቻለው። በስተቅር መኖርን ሥርዓተ አልበኝነት ይመራዋል። መኖርን ሥራዓተ አልበኝነት ከመራው መራር ነው ግብረ ምላሹ።

 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ችግሩ ለመገለጡ ዘመን እኛ እንመጥነዋለን ወይ ነው? እሚፎካከር መፎካከር ከሚችል አመክንዮ ወይንም ጭብጥ ጋር ነው። እኛ እኮ ያለነው 2013 ላይ ነው? አይደል? እሳቸው ያሉት ደግሞ 50በ60 ላይ ናቸው። ይህን አገናኝቶ፤ አፋትጎ፤ ወይንም ልጎ፤ ወይንም ጠርቦ መልክ ማሰያዝ ይገባል።

 

ማመጣጠን፤ ማቻቻል ቢያንስ አቻዊ የሆነ የጭብጥ አቅም፤ ክህሎት ፈጥሮ በሥርዓት መስተዳደር። ቢያንስ ለዛሬ 20/30/ ዓመት ለሚፈጠሩ በሃሳብም ለሌሉ ግን ማግሥት ለሚያመጣቸው እሸት ትውልድ ራቅ ያለ ሃሳብ ሊኖር ይገባል። ይህን የተወጡት የኔታ ፕ/ ሃብታሙ ተገኜ ትውልዳዊ ድርሻቸውን ተወጥተዋል። እኛስ?

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

16.04.2021

የሐናን ልመና የሰማ አምላክ የእኛንም ጸሎት ሰምቶ የጨመተ ሙሴ ይስጠን።

አሜን። 

ጸሎት ድል ነው!

ድዋም ድል ነው!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።