ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።
· ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።
ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ሕይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራር።
„ኃጣን ግን ዝም ብለው በጨለማ
ይቀመጣሉ፤ ሰው በኃይሉ አይበረታም“
(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 2 ቁጥር 9)
ኢትዮጵያዊነትን ያከበረ፤ ያጸደቀ፤ ያሰበለ ለካቴና
ሲሰጥ ኢትዮጵያ የት ነሽ ብሎ መጠዬቅ ይገባል። አወን ኢትዮጵያ ካቴና ላይ ናት። ለምን „በገዳ መደመር“ ስላልተካተተች። ይህን
አሻም ያሉ ካቴና ላይ ናቸው። ወይንም በረጅም ገመድ በቁም እስር። እሺ ያሉ ደግሞ በከራባት እና በገበርዲን ሰርግ እና መልስ ላይ።
ኬክም አለበት።
ኢትዮጵያም ሙሉ ወርዱ ቀርቶባት ማቅ ለብሳ ትንፋሽ
ባገኜች ምንኛ ዕድለኛ በሆነች ነበር። ህወሃት መራሹ ኢህዴግ የከታተፋት ኢትዮጵያ እንኳን አሁን የለችም። ድፍን ነገር።
አቶ እስክንድር ነጋ ሲታሰር እኮ ነገሩ አብቅቷል።
እ። ከዛ በፊት ኢንጂነር ስመኜው በቀለም ሲገደሉ የኢትዮጵያ ሉዕላዊነት ተረሽኗል። ነገረ አባይ እኮ ረግረግ ውስጥ የገባው ለዛ
አሉታዊ ዴሞግራፊ የኮፒ ራይት ሽሚያ ላይ ሲዳካ ነበር። ግን ልብ መሸመቻ ይኖር ይሆን? እህ። ማፈላለጉ ይገባል ብዬ ነው።
ገዳ አባይ የእኔ ነው አለ። ሊቃውንታቱ የፈለሰሙት፤
የመሩት፤ ያስተዳደሩት በእኔ ጠረን ነው ሲል ነበር አብይዝም ታላቁን ምስክር በአደባባይ በእርስ መዲናዋ ደመ ከልብ ያደረገው። የሄሮድስ
መለስ ዜናዊን ፈጣራም በአደባባይ ነው የተዘረፈው። መስዋዕትነቱን እንደምን እንደ ተቀረደደ እራሱ ዘመን ይገልጠዋል። ዘመን ያብራራዋል።
ተከድኖ፤ ተከርችሞ፤ የሚቀር ምንም ነገር የለም እና።
ነገረ
ኢትዮጵያ በሉት፤ ነገረ አፍሪካ ቀንድ፤ ነገረ መካከለኛው አፍሪካ መከራ ዕዳ ከሜዳ ነው የሆነው። ለምን? ሁሉም ነገር ገዳ ሰራሽ፤
አብይ ሠራሽ ሆኖ በአሉታዊ ዴሞግራፊ ነቀላ እና ተከላ ይካሄድበት ዘንድ ግድ ነበርና። ይህን ከልብ ሆኖ፤ በማስተዋል ሆኖ ማዬት
ይገባል። ቅጠሎች እጽዋቶች ሳይቀር እራሱ ዴሞግራፊ በሥርዓት ተካሂዶባቸዋል። ወይ ነደዋል ፈልሰዋል። የንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ
ቤተ - መንግሥት ሥር ነቀል ዴሞግራፊ ተካሂዶበታል። „ሶፍ ኡመር ዋሻ ምን ያመጣኛል ከደጄ እያለልኝ እናንተም መጥታችሁ እዩልኝ„
ሲሉ ምን አቅደው ምን እንደ ከወኑ ያሳያል።
https://sergute.blogspot.com/2019/04/blog-post_23.html
የጠ/ሚር አብይ አህመድ
ሦስተኛው
… ው
መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ።
https://sergute.blogspot.com/2019/04/blog-post_24.html
2019 ኤፕሪል 24, ረቡዕ
« ይህ አገር የወረስነው ሳይሆን የተዋስነው ነው። » (አቶ ዮናስ ደስታ)
https://sergute.blogspot.com/2019/04/blog-post_21.html
2019 ኤፕሪል 21, እሑድ
የአቶ ዮናስ ደስታ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ስለመነፈግ
የኢትዮጵያ
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር በቀላጤ ነበር የተባረሩት። ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራንፕ ልጅ ጋርም ሲዮዋቸው ነደዱ።
በዬትኛውም የቅርስ ጥበቃ ዕውነት ውስጥ አቶ ዮናስ ደስታን ስንብትም ጋር አዋዶ ማዬት ይገባል። ዕድሜ ጠገብ ጥሪት መንቀል በደረጀ
ሁኔታ ከውነውበታል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ሳያውቅ ነበር ቤተ - መንግሥቱ የታደሰው። ይህን የሞገትኩበት ሊንክ ለጥፌያለሁኝ። ኢትዮጵያ
እንድትፈርስ የታወጀባት መጋቢት 18/2010 ነበር። እሳቸው በግርባው ብአዴን ይሁንታ ለሞቱ ሞቱን የፈቀደ ዕለት። ከዛች የይሁንታ
ቅጽበት ጀምሮ ኢትዮጵያ ለገዳ አድራለች።
·
ከቤዛዊት የደካ ፋሲል ግንብ ምን
ጠቀራዊ ህልፈት ተዘጋጅቶልህ ይሆን?፡
አሁን ሰሜን ላይ ዙረዋል ከቤዛዊት ቤተ - መንግሥት
- እስከ ፋሲል ግንብ ጎርጎራም ጣናም በዴርቶ ጋዳ ምናብ ያርሱታል። የባህርዳሩ ኦፕሬሽን 90 ደቂቃ በኢንተቤ ነበር። መጽሐፉን
ያነበባችሁ ታውቁታላችሁ። እያንዳንዱ የልበ ወለድ መጽሐፍ ትወና ኢትዮጵያ እንደ ጥንቸል ሙከራ ተደርጎባታል በፒኮኩ ንጉሥ አጤ አብይ
አህመድ።
እሳቸው ሁሉንም ናቸው አጤ ዮኋንስ፤ አጤ ሚኒሊክ፤ አጤ ቴወድሮስ፤ አጤ ኃይለሥላሴ፤ አቶ መለስ ዜናዊንም ወዘተ
እኔ ነኝ ባይ ናቸው። ከዛም የቀደሙትን። ይህ የፓርክ ነገር እኮ እኔ ቅዱስ ላሊበላ ነኝ ነው አይደል? ኬኒያ ስሄድ ዝናብ ወረደ
ልክ እንደ ጃንሆይ „እኔ ቅዱስ መንፈስ ነኝም“ አለበት። አጤ ዝናቡም ሆነዋል፤ አጤ መንኮራኩርም ናቸው።
ከውስጥ ተደሞ ያለው ጭምት ፖለቲካ ቢኖር ኖሮ እዬፈረሱ
መሳቅ ባልሆነ የእኛ ነገር። እዬተናዱ ማውካካት ሆነ የእኛ ነገር። አሻራችን ገድለው እሳቸው አሻራ ሆነው ለመውጣት ነው እዬታገሉ
ያሉት። ተሳክቶላቸዋልም።
በኢትዮጵያ ማብቂያ ላይ ሉባዊ አብይዝምን አደላድሎ
መትከል ነው እዬተጉበትም ነው። አሳቻ /// አሳሳች //// አምታች /// ተማችም። ያልተደበበደበ ነፍስ የለም። ያልወለቀ ቀደምት
ነገር የለም። ያልረገጡት ሥነ ልቦና የለም። ያላቃሉት ሩህ ታሪክ የለም።የኔታዋ ቅድስት ተዋህዶ ሳይቀር አባዘቷት። የዕድምታ ባለሙያም
ሳይቸግራት ጤፍ ብድር ሆነባት። ተምች ወረደባት።
እግዚኦ! በሉ
ቅኖች ሁሉ!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
16.04.2021
ጎዳናዬ ለሥር ነቀል ለወጥ መታገል ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ