« ይህ አገር የወረስነው ሳይሆን የተዋስነው ነው። » (አቶ ዮናስ ደስታ)
እንኳን ደህና
መጡልኝ
የጠ/ሚር
አብይ አህመድ
ሦስተኛው … ው
መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ።
„ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤
ከሥርጉተ©ሥላሴ።
Seregute©Selassie
24.04.2019
ከእመ ብዙኃን ሲዊዚሻ።
የማግሥት ባለውለታ!
·
ከፍል አራት ማጠቃለያ።
እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ክፍል
ሦስትን በእንዲህ ነበር የከወንኩት ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ናት በሁሉም ዘርፍ። እና የቅንጦት ጥያቄዎችን ተግ ማድረግ ይጠይቃል። አማራጭ
ሳትይዝ አማራጭ ይፍረስ፤ ይናድ እያሉ ቅድመ ሁኔታ በመፍጠር መንፈስ ከመበተን መቆጠብ ይገባል። ሰላምን ማደፍረስም የተገባ አይደለም።
አቅም ያለው ነፍስ ያለው ድርጅት ዲያስፖራ ላይ
ያቋቁም። በቅኝ የማይያዝ ራሱን የቻለ ራዕይ ያለው። የሌለውን አለ እያለ ኮማን ነፍስ ይዘራል ብሎ ከሚጠብቅ። ያላበቃ፤
ያልደቀቀ ነገር የለም። ስልብ ነው ያለው ሁሉ … ም።
·
ስለ ነገረ
ዮናስ ጥሞና እና ጽናቱ ማጠቃለያ።
የአንድ ሰው ከቦታ መነሳት ለምን ብሎ መጠዬቅ
ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ለዛ ነፍስ ኢትዮጵያ ሁለመናዋን ገብራ ነው ያበቃችው። አብሶ ሥልጣን መበቀያ ሲሆን ደግሞ ይመራል።
በተገኘው ገጠመኝ ሁሉ የቀለምህን እንጥፍጣፊ እዬፈለግህ
ስተሰካካ የህብረ ብሄር እናት የሆነችው አላዛሯ ኢትዮጵያ አንክሳ ትታዬናለች። የ27 ዓመት የነፃነት ተጋድሎ ለዚህ ነበር እንዲህ
የወለሌ ገባታ ሆኖ ቀረ እንጂ።
ከሁሉ በላይ ቅርስ እና ውርስ ላይ ያለው የታቀደ
የመናድ፤ የማንደደ፤ የማንቋሸሽ፤ የመሰለብ፤ የመበወዝ ተግባር ማንነት አደጋ ላይ ስለመወድቁ ይተረጉምልናል።
አሁን እኔ በፋሲል ግንብ ጉዳይ ከጎንደር የአማራ
ተጋድሎ ወዲህ ነፍሴ እረፍት የላትም፤ የሰሞነኛው የስሜን ተራራ ሳስብ ጎርጎራውን የስስንዮስን ሥነ- ምንግሥታዊ መሰረትም አሰብኩት በጸሎት። ጥንታዊ አብያተ ቤተክርስትያንም አሉ …
ልብ ብሎ ሁኔታውን ማዳመጥ በእጅጉ ይገባል። እኔ
ግራኝ መሀመድ ወይንም ዩዲት ዘመን አዬር እንደመጣብን ነው የሚሰማኝ። በኮሃራም ተፈቅዶለት በሎጅስቲክ እዬተደገፈ ስቅዝ ብሎ አዬሩ
በሽብር ተይዟል። ወደዬት ነን ማለት ይገባል? የአቶ ዮናስ ደስታን ከሥራም ከዜግነትም መነቀል እማዬው ከዚህ አንጻር ነው … አዲስ
ጉልቻ የጠ/ሚር ጽ/ቤት ስለምን ፈለገ … አብሶ በዚህ የቅርስ እና የውርስ ቢሮ? እሺ አቤት ወዴት የሚል ነፍስን ማፋፋትንስ ስለምን
ተወደደ?
·
የወልዮሽ ፈንጣጣ
…
ኢትዮጵያን ይመራሉ የሚባሉ ዕድሉን ያገኙ ወገኖች
የወል ችግር አለባቸው። በዬትም ሁኔታ እና በዬትኛውም ሰዓት። ሲያሻቸው የሰውም የእንሰሳም የህክምና ባለሙያ፤ የሰማይም የምድርም ማህንዲስ፤ ከከርስ በታችን
ከከርሰ ምድር ላይ ያሉ ማዕድናት ኤክስፐርት፤ የምርምር የጥናት ሳይንቲስት፤ የጠፈር ተመራራማሪነት፤ የታሪክ ባለሙያ፤ የቢዝነስ
ማናጀር፤ የፍትህ ሚነስተርነት፤ የዳኞች ጉባኤ ሰብሳቢ፤ የሃይማኖት ተቋማት እጬጌ፤ የዩንቨርስቲ ፈላስፋዎች፤ የወታዳራዊ ሠራዊት
ሊቀ ሊቃውንት፤ ወዘተ ወዘተ
ወዘተ ፈጣሪ ሆነው ቁጭ ይላሉ።
በድርጅታቸውም ውስጥ 500 የጉባኤ አባላት ቢኖር
በአዘቦቱ ቀን አቶ „ሀ“ ጉባኤ ሆነው ቁጭ፤ 200 የማዕካላዊ ኮሜቴ አባላት ቢኖራቸው እሳቸው አቶ „ሀ“ ማዕከላዊ ኮሜቴ ሆነው ቁጭ፤ የሲብክስ ማህበራትንም መዘውር እኔ
ነኝ ይላሉ ያው „አቶ ሀ“፤ የሃይማኖት ተቋማትም እሳቸው ናቸው ሸሁም ፓትርያርኩም ያው እሳቸው ናቸው የመፍትሄ ቁንጮ „አቶ ሀ“።
እሳቸው ስል እኔ ዶር አብይ አህመድን ማለቴ አይደለም
የሶሻሊዝም በረከት ተቋዳሽ
ነፍስ
የሆነው ሁሉ መስረታዊ ችግር ይኸው ነው። ጠቅልሎ መወጥ። ሰው አቅም አይበረክትም በዚህ ዕሳቤ። ብቅ ሲል መንቀል ነው።
ለነገሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድም ቢሆኑ እኔ በፍጹም
ሁኔታ ባልጠበቅኩት ሁኔታ በእኔ ይሁንባችሁ „እኔ አሻግራችሁአለሁ“ እንጂ
ድርጅቴ ኢህአዴግ ያሻግራችኋዋል
አላሉነም። መንግሥቴ ኢህአዴግ ያሻግራችኋዋል አላሉም። እሳቸው መርከብም፤ ካፒቴንም፤ ቤንዚንም፤
ሹፌርም፤ ቴክኒከርም፤ አስተናጋጅም፤ አስተነባሪም፤
የአደጋ ጊዜ ተጠሪም፤ አቅራቢም፤ ሰጪም ነሽም እሳቸው ናቸው።
የፍልስፍና ይሁን የአገላለጽ ብቻ እራሱ ንግግሩ
የጽንሰሃሳብ ወደል ግድፈት አለበት
‚እኔ አሻግራችሁአለሁ‘። እንዴት ብሎ የሞገተ የፖለቲካ
ሊሂቅም አልተፈጠረም።
ስለምን እያንዳንዱም መሰረትኩት፤ አቋቋሙኩት በሚለው ድርጅት ያለው መንፈስ ይኸው አጤነት ስለሆነ።
የፖለቲካ መሥራች ሊቃናት አያዳምጡም፤ እንደገናም
ሁሉንም ቦታ ተክቼ ልስራ
ይላሉ … ከዛም ጥልቅ ነው፤ ከዛም ዶል ነው። መጠቅለል ነው ነፍሳቸውን አቅል
የሚነሳው። የማይበረክቱትም ለዚህ ነው። ሳይከፈል፤ አንጃ ሳይፈጠርበት የጸደቀ
የለም፤ መፍረስ፤ መናድ፤ መቀርፈፍ ...
ይህ ነው ኮ/መንግሥቱ ሃይለማርያምን ዘመንን የገደለ
እነ ኮ/ ጎሹ ወልዴን የመሰለ የሉላዊው ዓለም የብቃት ልዑል ያሳጣ፤ ስንት ምድር ልትገልጣቸው የማትችላቸውን ከፍተኛ መኮነንኖችን
ሆነ ሊቃናት አሳጥቶ እርኛ አልባ፤ መመኪያ አልባ፤ አማራጭ
አልባ ኢትዮጵያንም እንዲህ ከሚፈርሱ አገሮች ተርታ ያሰለፈው …
ማድመጥ ምን ያቅታል? ስህተትን መቀበልስ ማንን ይገድላል? ስለምን ድርጅቱን
ሳያማክሩ እድሳት ይጀመራሉ እሳቸው እራሳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ?
እሳቸው ፈራጅም፤ ዳኛም፤ አቃቢ ህግም፤ ተከላካይም፤ ከሳሽም ሆነው ይችሉታልን?
እኔ የጤናቸው
አልመስለኝ እያለ ሁሉ ነው አሁን አሁን የማዳምጠው ማህጸን ሰንጣቂ ሰብዕና።
እንዲህ በቃ ውሃ በቀጠነ ከሁሉም ጋር በመጋጨት
እንዴት ኢትዮጵያን ያህል አገር
መምራት ይቻላል? ባንድ ብጣቂ ወረቀት የአንድ አገር አንጡራ ሃብት መወርወር
ኧረ ቀስ አድርገው ይያዙት …
እኔስ ፈራሁላቸው የውነት … አትድፈሩኝ እንኳንስ
ለሳቸው ለኮነሬል መንግሥቱ ሃይለማርያም፤ ለሄሮዶስ መለስ ዜናዊም አልሆነም። ሌላው ቀርቶ ለአባ ጳውሎስም አልሆነም። ጎንደሮች „ልክን
ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ …
በዚህ ሂደት ውስጥ እርግጡን ባላውቅም የተወለዱበት
ደልዳላዋ ቀዳማዊት እምቤት
ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ከሰሞናቱ እንደተረዳሁት ሳይጃስትሪስት ናቸው። ይመስለኛል ኮከባቸው።
የዚህ ኮከብ ባለቤቶች ሴቶች ከሆኑ እናትነት በጥልቀት፤
ሚስትነት በጥልቀት፤ ፍቅር
እና ሰላም ፈላጊነት በጥልቀት፤ ቅንነትን በጥልቀት፤ ንጽህና ርህርህና በተፈጥሮው ልክ በምላት፤ መስጠት
መለገሥ፤ አዎንታዊነት፤ እውነት ከነሙሉ ጸጋው የሚታይባቸው በመሆኑ ባለቤታቸውን እናታዊ፤ ፍቅራዊ፤ ሚስታዊ እውነታዊ በሆነ ሁኔታ
ቀስ
እያደረጉ ሊገሯቸው የሚገባ ይመስለኛል። ሳይጃስትሪስት ሴቶች ሰብዕዊ አማካሪዎችም
ናቸው። ልዮ እና አሪስም ግጥማቸው ስለሆኑ የሰመረ
ጋብቻውን ለዚህ መሰል መደማመጥም መዋል የሚገባ ይመስለኛል።
የጠ/ሚር አብይ አህመድ መንገዱ አላመረኝም …
ሊንዳ ጉንዳ ሳይጃትሪስቶችን የዚህ ኮከብ ባለቤቶችን ንጹሃን ነው የምትላቸው … ንጹህ ናቸው፤ ቂም የሚባል አያውቁም፤
ግልጽ እና ቀጥተኛ ናቸው፤ እኔም ተስፋዬ ያደረግኳቸው ከዚህ አንጻር ነው፤ እንዲያውም በአደባባይ ከሚሰሩት የሚታይ በጎ ነገር ይልቅ
ሳይጃትሪስቶች ክድን ብሎ የሚከወነው መልካም ነገር ዝልቅ ነው … ስለዚህም ስለ ሰባዊነት ባለቤት ቢሆኑለት አበክሬ ላሳገነዝባቸው
እውዳለሁኝ።
በሲነሪትም የሚቀድመኝ ሰው አለ ብለው መቀበል ይኖርባቸዋል ጠ/ሚር
አብይ አህመድ፤ ኢትዮጵያ እኮ ስንት
እንቁ የመንፈስ ዲታ ሊቀ ሊቃውንት
አገር ናት። ተዘርዘሮም ተነግሮም ተብራርቶም በማያልቅ ሁኔታ ኢትዮጵያ
በመንፈሳቸው የለሙ የዳበሩ
የላቁ ልጆች እናት ናት። አቶ ዮናስ ደስታ ለውጭ
ጉዳይ ሚኒሰተር የሚመጡን ሰው ናቸው። ይህን ደፍሬ ነው የምናገረው። እንኳንስ
ለዚህም ቦታ አትመጥንም ተብለው ሊነሱ ቀርቶ።
መሬት ቢይዙ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጥሩ ነው።
አዬር መንገድ በፈቃዳቸው ቦርዱን አቋቋሙ፤ በባንኩም የተወሰደው እርምጃ እንዲሁ ነው፤ የንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክን ቤተ- መንግሥት
ለማድስ ሲነሱ መንግሥት ሥልጣኑን የሰጠውን አካል ሳያሳውቁ፤ ሳያማክሩ በራሳቸው ተነሳሽነት ነው።
·
ጥሞና በተደሞ።
የሚኒሊክ ቤተ መንግሥት እድሳት ቀድሞ ነገር ይህ እኮ አገራዊ ጉባኤ ተጥርቶ ሊመከርበት፤
ሊዘከርበት፤ ውሳኔ ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነበር። ራሱ ካቢኔው
በአጀንዳ ተሰብስቦ ሊወያይበት የሚገባ ጉዳይ ነው ኢትዮጵያ እራሷ
የምትገለጥበት
የጥቁር ህዝቦች
የድል ማማ የሆነ የታሪክ አውራ ጉዳይ እኮ ነው ይህ ጉዳይ።
ያ ቤተመንግሥት እኮ ውጫሌን፤ ዶጋሌን፤ አድዋን፤ መቅደላን፤ ካራማራን፤
ባድመን በመንፈሱ ያያዘ ነው። በዚህ የተጋድሎ ሂደት የአገር ውርስ እና ቅርስ የሆኑ መዋለ
መንፈስ፤ መዋለ ንዋይ፤ መዋለ ጊዜ ፈሰቦታል።
ሃብትነቱ የህዝብ የዜጋው ነው።
ስለሆነም በአንድ በሌላም ያሉ የኢትዮጵያ ጉልላቶች
የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ በተደሞ፤ በአርምሞ ሊመክሩበት ይገባ ነበር። ላደለውማ
ከመጀመሩ በፊት ሁሉም በዬሃይማኖቱ ቢያንስ የሦስት ቀን ሱባኤ መያዝ ነበረበት። ጸሎትም ሱባኤም
ያስፈልጋዋል ይህን መሰል ጉዳይ
ሲጀመር። ስለምንስ ይጣደፋል። የአገር ነፃነት ተወራራሽነት የተበጀበት ጭንቅላታዊ ጉዳይ ነው ይህ መንፈስ።
ቀድሞ ነገር መብትም የለውም እኮ አሁን ያለው ፓርላማ
ራሱ። ስለዚህ ቅቡልነቱ
በህዝብ ፊርማ የተረጋገጠ መንፈስ
እስኪመጣ ድርስ ሃሳቡን እያበሰሉ፤ እያሹ፤ እዬሾከሾኩ፤ እዬፈተጉ በጥናት ላይ የተመረኮዙ ሙግቶችን እያቀረቡ ማብሰል
ይገባ ነበር።
የንጉሦች ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክ ቤተመንግሥት እኮ
የኢትዮጵያ ሰማይ እና ምድር
ህገ መንግሥትም ነው። የጋህዱ ዓለም እና የሰማያዊው አለም መናህሪያ ነው።
መገናኛ። የመንፈስም
የጋህዱም ዓለም መገናኛ ድልድይ ነው የሚኒሊክ ቤተ
መንግሥት ነው።
ይህ ጉዳይ እኮ የአንቀጽ 17 ወሳኝ ውሳኔ የሚመለከት
ሚስጢር ያለበት እጬጌ ጉዳይ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን
የአፍሪካ፤ የጥቁር ህዝቦች የታሪክ መርከብ
የሆነው ታላቅ እጬጌ ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ህሊናዊ ንድፍ ብቻ እድሳቱ ሆነ ብልጽግናው ሊተዳደር፤ ሊሻሻል እንደገና ሊበጅ
አይገባም። ከዚህ ጋር
የኦሮሞ ፖለቲካ እና የንጉሦች ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ ጉዳይም እንዲህ በቀላል እንዳሻህ ተብሎ ይለፍ ሊሰጠው አይገባም።
ድንግልና ስለሚጠይቅ።
ታሪክ አጋጣሚውን ቢሰጥም አጋጣሚው ግን በወልዮሽ
ቀለም ሊመከርበት ሊዘከርበት ይሁንታ ሊያገኝ ይገባል። አንድ ኮንደምንዬም የድንጋይ ድርድር ላይ ጦርነት የሚከፍት ድርጅት እንደ
አንድ ተማላ ጎጆ ይህን መሰል እርምጃ ለመወስድ በንጽጽር ሲታይ አይመጣጠንም።
በተጨማሪም ምንም እንኳን አኖሌ አጀንዳዬ ሆና
ባታውቅም ለትውልዱ ግን እዛ ያነን ሠርተህ አሁን ደግሞ ለዚህ አዎንታዊ፤ ቅናዊ በጓዊ ዕሳቤ ቢሆንም እንኳን ህዝብ ቀጥል ብሎ ታማኝነቱን
እንዲሰጥበት ሁኔታው መማመቻቸት ይገባ ነበር … ቢያንስ ባልስልጣን መስሪያ ቤቱ ይሁንታው ሊጠዬቅ ሊፈርምበት ይገባ ነበር።
በእያንዳንዱ ሙያ
ባለሙያ ኢትዮጵያ የምታስተምረው፤ የምታስመርቀው እኮ ለግብር ይውጣ አይደለም። ወይንም ዲፕሎማው፤ ዲግሪው ፍሬም ተስርቶለት የግድግዳ
ጌጥ እንዲሆንም አልነበረም። የትውፊት እና የትሩፋት ሙያው ሊቀ ሊቃውንታት በዘርፉ
የከበረ ተመክሮ ያላቸውም አሉበት። የሙያ ኤትኪስም
ርግጥግጥ ነው ያለው …
በዚህ ማን አለብኝ እርምጃ …
ሲመሰረትም ብዙ አገራዊ መዋለ መንፈስ ፈሶበታል፤
ሂደቱ በራሱ ራሱን የቻለ
አምክንዮ አለው፤ ጠቅላላ ይዘቱ የሚስጢር ቋት ነው። ልባችን ያለበት ጉዳይ ነው። ህሊናችን ያለበት ጉዳይ ነው። መንፈሳችን ሃዲድ የሠራበት ጉዳይ ነው።
ባለድርሻ የመንግሥት አካላትን ጨምሮ የባህል፤ የቅርስ፤ የታሪክ፤ የህግ፤ የሃይማኖት፤
የቋንቋ ሙሁራን፤ የጥብበ ሰዎች
ሁሉ ተገኝተው መክረው ዘክረው ሊወስኑት የሚገባ ጉዳይ ነበር።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዬ ዕለቱ ፕሮጀክታቸውን
ለማዬት እንደሚጓጉት ሁሉ
ሁሉም ዜጋ ስለመብቱ እና ስለ ግዴታው ጉጉት ያለበት መሆኑን እንደ መሪ ቢቀበሉት የሚሻል ይሆናል። እዬገፉት
ስለሆነ ዜግነትን። ጥሰት እዬፈጸሙም ነው።
በአንድ ቀንጣ መንፈስ፤ በአንድ በጎ ፈቃደኛ ተነሳሽነት
ወይንም በአንድ ተጽዕኖ ፈጣሪ
ነፍስ ብቻ ይህን መሰል ሁለገብ፤ ሁልአቀፍ፤ ህብራዊ ጉዳይ ሊፈትል የሚገባው ጉዳይ አይደለም። አልነበረም።
ቅርስ ትውፊት ነው። ቅርስ ታሪክ ነው። ቅርስ
ነፍስ ነው። ቅርስ ህልውና ነው። ቅርስ
ትናንት ነው። ቅርስ ነገ ነው። ቅርስ ከነገ ወዲያ ነው። ቅርስ ጊዜ ነው። ቅርስ ትውልድ
ነው። ቅርስ ማንነት አለው፤ ቅርስ ብሄራዊ ዜግነት ያለው ነው። ቅርስ አለምአቀፋዊ
ዜግነት ያለው ነው። ቅርስ ሰው ነው።
ስለዚህ ለዚህ ሁለገብ አቅሙ ሁለገብ ክህሎት
ያለው የብዙሃን የሃሳብ ቅምረትን ይጠይቃል። እርጋታ አንሰው እርምጃው ...
ጥድፊያን ቤተ መንግሥት አብረው አልተፈጠሩም ... የቤተ መንግሥት ሰው
አደብ የነፍሱ መገለጫ ነው። እንግሊዞች ለቤተ መንግሥት ቅርሶቻቸው ቀናኢ ናቸው። ከእነሱ መማር በ እጅጉ ያስፈልጋል። አገር እኮ በመንግሥት ሥርዓት ነው የሚፈጠረው እንጂ አገር በመሄድ አይደለም የሚበጀው ... መሄድ እርሾ የለውም።
ይህን መሰል ጉዳይ ተደሞን፤ ርጋትን፤ ምራቅ መዋጥን
ይጠይቃል። ይህን አለመፍቀድ
ለዚህ አለመሰናዳት ትርፉ ኪሳራ ነው። ዛሬ እሳቸው ስልጣን ላይ ስላሉ ሊያደርጉ የፈቀዱትን ያድርጉት
ግን እሳቸው ቋሚ ስላልሆኑ ነገ ደግሞ ሌላው እንደሚሆን ያደርገዋል። ህዝብ መክሮበት ቢሆን ግን ዘላለማዊ የመንፈስ ፊርማ ይሆን
ነበር።
ሃሳቡ፤ ትልሙ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ሆኖ ግን ይሁንታው የህዝብ ቢሆን ከዚህ
ደረጃ የሚያደርስ አልነበረም። ያልነበት ዘመንም ግሎባል ስለመሆኑ ልብ
ሊባል ይገባል። ለነገሩ እሱንም እገድባለሁ ብለው ታጥቀው ተነስተዋል።
ነገ ስለሚሆነው ማናችንም አናውቅም። መሠረት ላለው
የህዝብ አንጡራ ሃብት
መሰረት ያለው እርጋት በጽኑ ያስፈልጋል። ያን
ቤተ መንግሥት ያህል የመንፈስ
እምቅ ጥሪት የእነ ተሎ ተሎ ቤት በሆነ መንፈስ … ግልቢያ ብቻ ሆነ።
ስክነት ያሰከንል፤ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ባለድርሻ አካላትን በገፉ
በገፈተሩ ቁጥር መከራን በራስ ላይ መቆለል ነው። ትርፍ ሳይሆን ኪሳራም ነው። እኔ እንደማስበው
ጠ/ሚር አብይ አህመድ በዚህ እርምጃቸው
ከሰሩ እንጂ አላተረፉም።
አያጀግናቸውም።
አሁን እኔ እድሳቱ አያጓጓኝም። የፈለገ ዘመኖ ቢሰራ ሚሊዮን ዶላር ቢያስፍስ፤ ምክንያቱም ታማኝነት ከፈቃደኝነት ሲነሳ ብቻ ነው ለእኔ እርባና የሚኖረው።
በህግ ጥሰት የተጀመረ ፕሮጀክት ነው ለእኔ። ባለሥልጣን
መ/ቤቱ ሳያውቀው ከሆነ ፎርጅድ ነው ለእኔ። ገና
ታድሶ ሳያበቃ በመንፈስ ደረጃ ኤክስፓዬርድ አድርጓል።
ይህም ሆኖ ስህተትን አርሞ ወደ ትክክለኛው መስመር
መምጣት ሲገባ ጭራሽ
ባለሥልጣኑን ከሥራ ማባረር በሌላ አገር ቢሆን ፍርድቤት የሚገትር ነበር።
ለነገሩ አቃቢ ህጉ ራሱ ኦዴፓ አይደለምን?
ለማንስ አቤት ይባላል? ራስ እግሩ
እሱ በእሱ።
·
ትምክህት
ፈጣሪ ብቻ ነው።
የሳቸው በዬሦስት ወሩ ነቀል ተከል ሹመት ቀርቶ
በረጉ፤ በሰከኑ አገሮች ያለው ሥልጣን እንኳን ይህን ያህል አያስመካም። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በተመሳሳይ
ሙቀት ነበር
ሁለቱንም የመመረጥ ዕድል በርጋታ አሳልፈው ሥልጣናቸውን
ለተተኪያቸው ያስረከብቱ፤ ስለዚህም እንደተከበሩ ይገኛሉ። ሙቀትም ቅዝቃዜም
ግድ
የማይላት ሲዊዝሻ እንኳን እኒህን መሪ በልዩ ሁኔታ በተለያዬ ጊዜ ከነቤተሰባቸው ትዘክራቸዋለች - ዛሬም።
እኔ ደፍሬ እና እርግጠኛ ሆኜ የቅኔው ልዑል ብላቴ
ጌታ ጸጋዬ ገ/መድህን ማለት ኢትዮጵያዊነትም አፍሪካዊነትም ነው የምለው የውስጡ ድንግልና ነው። ዘመን
ቢቀያዬር ዘመን ቢለውጥ ያ የሚያበራ የሰከነው ብሄራዊ አቅሙ ይበልጽጋል፤
ይፈልቃል፤ ያጸደያል እንጂ አይከሰምም ...
ምክንያቱም ማግስትን የቀረጸበት እርጋታው ዘመን
አሻጋሪ በመሆኑ። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ግን የሚከተሉት ፈለግ
የሚሄዱበት መንገድ መልካም አይደለም።
ችኩልነት በዛው። ጥድፊያ ቀያሹ ሆነ፤ ማድመጥ ጋዳው ሆነ፤ ንዴትን
አበሰረ፤
ቁጣ ሰፈነበት፤ እኔ
እንደማስበው የድሮው ሰብዕናቸው ነው የሚሻላቸው …
ለገሃዱ ዓለምም ለመንፈሳዊ ዓለምም … ያ ምቹ
ነበር። ፈለጋቸውን እዬሳቱ በሄዱ
ቁጥር ከህዝብ ፍቅር ጋር ስለሚጋጩ የበለጠ ብስጩ እዬሆኑ ሰብዕናቸውን ፈታኝ
ለሆኑ አደጋዎች ሁሉ
ይጋለጣሉ … የመካሪ ያለህ ትላለች ነፍሴ …
በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ ያላቸው ጠናና አቋም
ምን ሊያስከትል እንደሚችል አላስቡበትም፤ በአዲስ አበባ ላይም የወሰዱት እርምጃ ራሳቸውን ነው እዬናደ ያለው። በዚህ ማህል የቆሞስ
እኒጂነር ሰመኘው ደመ ከልብነት አለ፤ ታምቆ ተሸፍኖ ውሾን
ያነሳ ተብሎ የተቀመጠ ፈንጅ አለ። ጊዜ ይጠበቃል። ጦር የሚሰብቁት አትኩሮታቸው
ምን ላይ እንደሆን? በማን ላይ ጥርስ እንደነከሱ? ማንን ለማግለል እዬተጠደፉ
እንዳሉ ጠረኑ ለሳቸው ግምኛ ነው።
ይህም ሆኖ አሁን ደግሞ ይህን አክለዋል ነገ እና
እሳቸውን ያያ … በዚህ ዘመን መከራ ለመቀበል መቁረጥ፤ መወሰን ቢያስከበር፤ ጀግና ቢያደርግ እንጂ የሚያወርድ፤ ቅስም የሚሰበር፤
የሚሰቀጥጥ አይሆንም። ለራሳቸው ነው የቀረባቸው።
ክብራቸውን፤ ግርማቸውን፤ ሞገሳቸውን ቀስ እያደረጉ
እዬሸኙት ስለሆነ እኛም
በሳቸው ላይ ያለን ተስፋ ቀስ እያለ እንሸኘዋለን … ውል የለብን … ውለታም
አንሻ፤ ቅርጥምጣሚ የውዳሴ
ከንቱ ራህብተኞችም አይደለንም …
ጌጥነት እንዲህ ግንጥል ጌጥነት መሆኑን ስናስተውል
ንጽህናችን፤ ቅንነታችን አቤት
ማለቱ አይቀርም ለአንድዬ … ሌላ አቅም ባይኖርንም ማለት። እሳቸው ሁላችንም
ምንም አታደርጉኝም አይነት
ስለሆነ ጉዞ የጀመሩት። ቅንጣት ነፍስ ብዙ ናት ወቅት
እና ጊዜ ከጠበቀች ንጽህናውም ከኖራት … እግዚአብሄር ለቅኖች ቀናተኛ አምላክም
ነው።
እኛ … ቀድሞም እውነት ነው ያሰደገፈን፤ ከጎን
ያስቆመን ዛሬም እውነትን ተመርኩዘን
ነው እምንናገረው … ወደ እውነት ሲመጡ ይደገፋሉ ከአውነት እዬራቁ ሲሄዱ ደግሞ ልባችንም ይሸፍታል
… እንዲህ ማስከፋቱን ሲያነባብሩት ሸጋ ነው፤ ስለምን ብትሉ መቁረጥን ሲለሚሸልም። መወሰንን ሰለሚያጎናጽፍ … የቁርጡ ቀን ሲመጣ
መገንባት እንጂ ማፈረስ ቀላሉ መንገድ ነው። ጸሎት ሃይል አለው። ጸሎት የልብ ንጽህና ብቻ ነው የሚሻው።
የሚገርመው አቶ ዮናስ ደስታ በጠ/ሚር አብይ አህመድ
አክቲቢዝም ላይ የጎላ
ድርሻ እንደነበራቸው ነው እኔ እማስበው፤ ስለምን ብትሉኝ በዛ ቤተሰባዊ በሆነ
„ከእርምጃ ወደ ሩጫ“ ፕሮጀክት
ላይ የነበረው ሥልጡን፤ ውብ፤ የተሟላ ጤናማ
መንፈስ ውስጥ የታደመ ነፍስ አብሮ እያለ ቀርቶ እኛን በሩቅ ያለነው ኢህአዴግ
የሚባል
ጨካኝ ግንባርን ያሰረሳን እውነት ስለነበረው እኒህ ነፍስ በሳቸው ጉዳይ
ላይ በተገኙበት ቦታ እና አጋጣሚ ሁሉ ነፍሳቸውን ከነፍሳቸው
ጤናማ በሆነ ሁኔታ ያሰተሳሰሩ የአዎንታዊ አርበኛ ይሆናሉ ብዬ ነው የማስበው።
ለነገሩ እሳቸው መሆናቸው አለመሆናቸውን አላውቅም
ጠ/ሚር አብይ አህመድ
ሰሜን አሜሪካ በነበሩበት ጊዜ አንድ ከፍተኛ ሃላፊነት ያለው ለሌላ ተግባር ስሜን
አሜሪካ የነበረ ነፍስ ሰፊ
የሆነ አዎንታዊ አብያዊ አክቲቢዝም ሲፈጽም እንደነበረ መረጃው ነበረኝ። አስከ ኮሎንቦስ ኦሃዩ ድርስ ሃዲድ ዘርግቶ ሲተጋ ነበር።
አሁን
ሳስበው ስሜቴ እንደሚነገርኝ ከሆነ አቶ ዮናስ ደስታ ይሆኑ እላለሁኝ ግን እርግጠኛ አይደለሁም። እስኪ አጣርቼ እነግራችሁ
አለሁኝ ለቅኖቹ …
ዛሬ የሚሰማኝ እሳቤ የምገልጠው እንደ አንድ የቀድሞ
ደጋፊ ዜጋ ልባችን ለመጥረግ መንፈሳቸውን ለመጥረግ፤ ህሊናቸውን ለመጥረግ
እውነት ቢሆኑ እላለሁኝ … ሌላማ ለማንም ሳይሆን ለራሳቸው፤ ለቤተሰባቸው ጠቃሚው መንገድ ይኸው ስለሆነ።
ለአላዛሯ ኢትዮጵያማ ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም
ያልፋል።
መዶሻ ፋፍሪካውንስ እንዴት ነው ቻይናዎች ቤተመንግሥት ውስጥ ግንባታውን
ተረክበውት ይሆን? ቀጣዩስ ማን ይሆን አምስታ … ስድስት … ሰባታ የመዶሻ
ባለ እጣ ፈንታ … መለማመጃው፤ የሙከራ ጣቢያው ማን እንደሆነ ይገባናል፤
·
ስለቀደመው ….
Ethiopia
- Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ
ይህን እኔ አዳምጬ የዛሬ ዓመት እንዲህ ብዬ ጽፌ ነበር …
„እዮር ሰማይ ላይ ብቻ ሳይሆን በዚህ ቅዱስ መንፈስ ውስጥ አየሁ። ተመስገን።“
እኔ ይህን ስጽፍ የቀደመኝ አስተያዬት የአቶ መሀመድ ጀማል ይህን ብለው ነበር
አሁን ሳስበው አቶ ጀማል ያሉት ትክክል ነበር ማለት ነው። ሰብዕዊነት ድረቀት ገብቶታልና።
„ችግሩ ከስልጣን በፊትና ቡኋዋላ ያለው ወሬ እየተለያየ ተቸገርን“ እውነት ብናገር
አቶ መሀመድ ያሉት ትክክል ነበር ማለት ይቻላል።
Ethiopia - Dr abiy ሚኒስትር ከመሆንህ በላይ ሰዉ ነህ!
Published
on Feb 17, 2018
ዛሬ ላይ
አንዲት ቃል ስለሳቸው ተቃውሞ ማሰማትም ሆነ የሳቸውን እርምጃ መኮነን አያቻልም። ሁሉንም አሰሱንም፤ ግፋፎውንም፤ ስንዴውንም
እንክርዳዱንም ተቀበሉ
ባይ ናቸው።
ጦርነት ከእስክንድር
ንቅናቄ ጋር ለመግባት የቆረጡ፤ ለምን ተጠዬቅኩ ብለው አቶ ዮናስን ከሥልጣን ያነሱ፤ አንድ የፖለቲካ ድርጅት የሚፈጠረው
ለሥልጣን ነው „ነገ መንግሥት እንሆናለን መሆናችንም አይቀርም“ ሲል አብን ያን ያህል በንቀት እና በማዳዳጥ መሳቂያ እና
መሰላቂያ በአደባባይ ያደረጉት እውን „ሚኒስተር ከመሆነህ በላይ ሰው ነህን“ ተቀብሎ ይሆን ከውስጡ መንፋሳቸውን ያሰኛል?
ሁሉ ሰው
ከሆነ ከላይ እስከታች የራሳቸውን ዘሮች እዬፈለጉ ስለምን ቦታ ይሰጣሉ? የራሳቸው ደሞች ስንት የህግ ጥሰት ሲፈጽሙ ስለምን
ከህግ በላይ እንዲሆኑ ይሻሉ?
ሌላው ላይ ደግሞ ስለምን ጫና ያበዛሉ? እሳቸው መሆን ያልቻሉትን ነው ለእኛ ይህን የሚሉት።
ትዝብቴ ሰፊ
ነው … ሂልተን ሆቴል ስለ አብን ከተናገሩ በኋዋላ በአንድም በሌላም
በአብን ላይ ያለው ጣምራ ዘመቻ ራሱ የላከልን መልክት አለ። የወሎ ማህበር፤
የባህርዳሩ ግጭት፤ የወሎ እና የስሜን ሽዋ ሰቆቃ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ነው እኔ
የማዬው።
Ethiopia: Dr Abiy ahmed speech at Gonder
abiy News
Published on Mar 16, 2018
Abiy
ahmed speech at Gonder part 2
Published on Nov 4, 2017
ይህ ስለ ሰው ፍልስፍና ረቂቅ የሆነ ቅዱስ መንፈስ እንዲረብበት የተደረገ
ገለጻ ነበረበት። ሰው ጸሐይ ነው እስከማለት የደረሰ። ግን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው እንደ ጸሐይ ይታያልን ? በስጋት
እዬተናጠ/ በሽብር እዬተቀቀለ አንድ ቀንጣ አረጋጊ መንፈስ አጥቶ ነፍስ ይናውዛል … አይዞህ ባይ የለውም
ኢትዮጵያዊው ሰው።
·
« ይህ አገር የወረስነው ሳይሆን የተዋስነው ነው። » (አቶ ዮናስ ደስታ)
Tech Science TV Program
Episode 39
Published on May 24, 2016
Ministry of Science and
Technogy(MOST), Leadership and Motivation Program
Published on May 12, 2016
በዚህ
ስብሰባ ላይ ዛሬ በዘመነ አብይ ንግሥና በአንድ ቀላጤ የተባረሩት አቶ
ዮናስ ደስታን እንዲህ ሲሉ ነበር የገለፆዋቸው ጠ/ሚር
አብይ አህመድ።
„አምሰተኛው ተናጋሪ አቶ ዮናስ ይህ አገር የወርስናው ሳይሆን የተዋስነው ነው
ብሎናል። አቶ ዮናስ በውርስና በውሰት መካከል በሚያስደንቅ ብቃት ነው
የገለጸው።“
ይህን ያሉት
ጠ/ሚር አብይ አህመድ የአገር ሙሴ ሲሆኑ ደግሞ ድንቅ ብቃት
ያሉትን ዜግነቱን ነጥቀው፤ ሞራሉን ድቅቅ አድርገው፤ ሥነ -
ልቦናውን በመቀስ
እንዳሻቸው ሸንሽነው ቀዳደው የሥራ ሃላፊነቱን በግለት መንፈስ ንጠው እና
ነስተው የአቶ ዮናስን የማንነት
ሰብዕና ከሰውነት ሰርዘውታል።
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ተነሱ
17 April 2019
በዚህ „ከርምጃ ወደ ሩጫ“ ህልዋዊ ጉባኤ ላይ አቶ ዮናስ ደስታ እንዲህ ብለዋል ስለ አገራቸው
ኢትዮጵያ ያላቸውን ረቂቅ ጽኑ ጥልቅ ንጥረ ነገር ወይንም መንፈስ በዚህ
ውስጥ ውዶቼ ታገኙታላችሁ። ይህንኑ ብጡል መንፈስ ዛሬ
ለጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደ ጣውንት የሚታይ፤ በጥርጣሪ የሚታይ ነው።
ነገ
በህይወታቸው ላይ ምን እንደሚደርስ ሁሉ አናውቅም። እንደ ቆሞስ ስመኛው
በቀለ ደመ ከልብ ወይንም አካል ጉደለት … አናውቀውም
አሁን ያለው የኢትዮጵያ
መንፈስ ጠረኑ እጅግ አስፈሪ ነው። ባለቤት አልባ መንፈሶች እልፍ ናቸው …
·
የዘመን
ጀግና የልቡን ተናግሮ ከመሸበት አዳሪው ሊሂቅ አቶ ዮናስ ደስታ እንዲህ
ይሉናል …
„የሥልጣኔ ምንጭ
ነን ሲባል ብዙ ሰው መነሻው ምንድን ነው ወይንም ያን አርጉዩመንት በምንድን ነው የሚያው
ሲባል የተለያዬ መልስ ሊኖረው ይችላል የሚለውን ነገር የሦስት ሺህ ዘመን ታሪክ አለን እሱም ትክክል ነው፤ ግን እሱም ብቻ ስለሆነም
አይደለም የሰው ዘር እስከዛሬ ባለው ያው የሳይንስ ሰው ስለሆናችሁ በሳይንስ ቋንቋ ስንነጋገር የመጀመሪያው ስልጣኔ ሊሆን የሚችለው
የሰው ልጅ ከአካባቢው ፊድ ለማድረግ የተጠቀማበቸው ስቶን ቱሎች ናቸው። አንዳንድ ሰዎች
ኮት ሲያደርጉት በአለማችን ላይ ሞስት ፓፕልሽድ
ስቶን ይሏታል ያቺ ስቶን ቱል ጎላ የሚባል ኢትዮጵያ በደቡብ አካባቢ የተገኘች ድንጋይ ስትሆን ሁለት ነጥብ ስድስት አንድ ሚሊዮን አመት ዕድሜ ያላት ከዛች የድንጋይ መሳሪያ በፊት የተገኜ ቴክኖሎጂ ስለሌለ
እንግዲህ አሁን ቴክኖሊጂ ውድድሩ ስአስማርት ፎን የተለያዬ የተለያዬ የተለያዬ
ነገር አለ በዬቀኑ እዬተቀያየር ነው ያለው መነሻው ግን የእኛ ነው ስንል እስካሁን ሳይንሳ ኢብዴንስ እኛው ጋ ስላለን ነው ስለዚህ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ስለሆነ
እዬሠራችሁ ያላችሁት መነሻው አገር
ላይ እንዳለችሁ ማንሳት ፈልጌ ነው።“
Tech Science TV
Program Episode 39
ተውጠው የቀሩ ፊደሎች ከኖሩ ይቅርታ እጠይቃለሁ ግን ራሳችሁም ማደመጥ ትችላላችሁ። ይህ አቅም ስለምን ተፈራ ? ይህን በህሊናው የጸነሰ ለዛም
የሚተጋ ከልቡ የተቀበለ መንፈስ ስለምን ተፈራ ? ስትሉ የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ለሚሉት ጋሬጣ ነው፤ አጀንዳ አልባም ያደርጋቸዋል፤ የበታችነት በሽታቸውንም ይቀሰቅሰዋል። ነገር ግን የትውልዱ መዳኛ ይህ መሰል ለራስ
ታሪክ፤ ለራስ ብቃት ታማኝ መሆን ነበረበት እርግጥ ጉዞው ኢትዮጵያን የተስፋ ምድር ለማድረግ ከሆነ ሩጫው …
Published on May 24, 2016
Tech Science TV
Program Episode 39
Ethiopia - Dr
Abiy ይህ አገር የወረስነዉ ሳይሆን የተዋስነዉ ነዉ!
„ይህ አገር የተዋስነው ሳይሆን የወረስነው ነው ብለናል።“ ይላሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ይህን ይዘው የተለያዩ ሚዲያዎች ጠ/ሚር
አብይ አህመድ ለዚህ ቦታ ሲሾሙ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ንብረት አድረገው ሲሰሩበት አዳምጫለሁኝ። ይህ ግድፈት ነው። አገላለጹ
የተነገረው በብሄራዊ ጉባኤ ነው። ስለዚህ አገላለጹ ባለቤት አለው። ፖስት ያደረገውም ዩቱብ ግድፈት ነው የፈጸመው።
Tech Science TV Program Episode 39
TechinEthiopia
እዚህ ላይ ደግሞ ከ40 ደቂቃ ጀምሮ ያለውን ስታዳምጡት ሃብትነቱ የአቶ
ዮናስ ደስታ ስለሆኑ እሳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እራሱ ይገልጡታል። ያን ነፍስ የነበረውን
ጉባኤ ሲያጠቃልሉ ስለ እያንዳንዱ
ተናገሪ ሲናገሩ ስለ አቶ ዮናስ ደስታም በድንቅነት ገልጠውታል።
ነገር ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲሾሙ ሌሎች ሚዲያዎች ሃይለ ስንኙ
ወይንም ፍልስፍናው መነሻ አድርገው ሌሎችም ሲቀባበሉት አዳምጫለሁኝ። የዚህ ሃይለ ስንኝ ፍልስፍና ባለቤት ግን አቶ ዮናስ ደስታ
ናቸው። እንደ ባለቅኔነታቸው፤ እንደ ፕለይ ጸሐፊነታቸው፤ እንደ ሥነ - ጹሑፍ አራሚነታቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ « ይህ
አገር የወረሰነው ሳይሆን የተዋሰነው ነው ብለናል » ማለት በፍጹም አልነበረባቸውም፤ ሚዲያዎችም የሳቸው
አድርገው ስለተናገሩት ነው ወደ እሳቸው ያስጠጉት።
አንድ ቃል ወይንም ስንኝ ወይንም ሐረግ የሁሉም የሚሆነው ተመካክሮ
በጸደቀ ሰነድ
እንጂ እራሳቸው ምስክርነት ሰጥተው „አምሰተኛው ተናጋሪ አቶ ዮናስ ይህ አገር የወርስነው ሳይሆን የተዋስነው ነው ብሎናል። አቶ ዮናስ በውርስና በትውስት መካከል በሚያስደንቅ ብቃት ነው የገለጸው።“ ያሉትን ገልብጠው ይህ አገር የወረስነው ሳይሆን
የተዋስነው ብለናል“ የራሳቸው ሃብት አድርገው ማቅረባቸው ወደል
ግድፈት ነው። ብሎናል እና ብለናል የትርጉም ልዩነት አላቸው። ብሎናል ሌላ ሰውን አምልካች ሲሆን ብለናል ግን እኔም ብያለሁ ነው ...
„ኢትዮጵያዊነት
ሱሴ ነው የአቶ ለማ መገርሳ ነው፤ ቅንጅት መንፈስ ነው የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዲቅሳ ነው፤ የቡዳ ፖለቲካ የፕ/
መራራ ጉዲና ነው፤ ቃል ይተክላል ቃል ይነቅላል የጠ/ሚር አብይ አህመድ ነው፤ የሚታይ ነገር ለማሳዬት መጀመሪያ የማይታይ ነገር
ይሰራል የፕ/ ብርሃኑ ነጋ ነው፤ በቃ! አንድ ካናዳ የሚኖር የነፃነት እርበኛ ወጣት ሉላዊን ዓለም ያነቃነቀ ሞቶ ነበር“
ስለዚህ መሪ
ቃሎች፤ መሪ አባባሎች፤ መሪ አነጋገሮች የባለቤታቸው ናቸው። እሳቸውን ያህል አራት ዓይናማ
ተናጋሪ ከሌላ ትውስት የሚያስኬዳቸው ስለሌለ በዬትኛውም
ስብሰባ ላይ አባባሉን ከወደዱት፤ አገላለጹ ከማረካቸው „አቶ ዮናስ
እንዳለው
ይህ አገር የወረስነው ሳይሆን የተወስነው ነው።“ ይህም ማለት ብለው በራሳቸው
የግንዛቤ ልክ ማብራራት ይገባ ነበር።
ልክ እኛ የጠ/ሚር
አብይ አህመድ
“መደመር“ ማለት ብለን በጥቅስ ውስጥም አስገብተን እንደምንጽፈው፤
ተናጋሪዎችም ሲናገሩ እንደ ጠ/ሚር አብይ መደመር ብለው ነው የሚነሱት።
በንግግርም
የሳቸውን አገላለጽ ሥረ መሰረቱን የባለቤቱን አፍላቂ ህሊና ሳንጫን፤
ሳንዘርፍ፤ ሳናኮማትር፤ ሳንጨማምቅ፤ ኩፍትርትር ሳናደርግ
ከነተፈጥሮ
እንደምናቀርበው በዛ ልክ እሳቸውም የአቶ ዮናስ ደስታን ፍልስፍና ማቅረብ
ነበረባቸው።
ለዚህ ግን
አቶ ዮናስ ጠ/ሚር አብይን አልከሰሱም፤ አልወቀሱም … በትእግስት አልፈውታል፤ ለነገሩ „ንጉሥ አይከሰሰ ሰማይ አይታረስ“ ነውና
… ይህም ሆኖ …
በቀለጤ ደብዳቤ ተሰረዙ ከለውጡም ከዜግነትም … ስለ ንጉሦች ንጉሥ አጤ
ሚኒሊክ ቤተመንግሥት ሁላችንም
ባለድርሻ ስለሆነ ያገባናል። ይህ መታወቅ አለበት።
ስለ ኢትዮጵያዊ ዜግነቴ ሰጭም ነሽም የለምና።
የሆነ ሆኖ
ሙስናን አጥብቀው የሚጸዬፉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በአባባል
በአገላለጽ
በፓተንትም ላይ ተመሳሳይ አቋም እንዲኖራቸው ምርጫዬ ነው …
የአፍ ወለምታውም ስለሚደጋገም። በሃቅም
ዙሪያ እንዲሁ፤
ከዚህ ጽንሰት ስነሳ ግን ያን ያህል ያነን ጉልህ ስንኝ መንፈሱን ወርሰው የራሳቸው
ለማድረግ ያሰቡት፤ ያን
አገላለጽ ራሳቸውን አክለው የተናገሩት የገለጹበት መንገድ
ዛሬ ላይ ሳስበው በሳቸው እና በአቶ ዮናስ አቅም የቆዬ ቂምም ባይሆን የመንፈስ
ፉክክር እንዳለባቸው
ጠቁሞኛል።
እኔ እንደማስበው ያላመከሯቸውም ከዚህም የተነሳ ነው፤
ጥያቄው ሲነሳ ለእርምጃ የተጣደፉትም በዚኸው ምክንያት። ይህ ሁሉንም ነገን የሚጠብቀው መከራ ይሆናል። ምክንያቱም እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ስለሚወለድ ሞገደኛ መክሊት በተፈጠረ
ቁጥር ቤተመንግሥትን የሚነካ ከሆነ መዳጡ አይቀሬ ነው ዱላውም
ፋሱም። አስፈሪ ነው ነገርዬው …
ከሁሉም
ይልቃሉ ተብለው እኮ ነበር ጠ/ሚር የሆኑት … ለዛውም በሚሊዮን
ድጋፍ ተንቆጥቁጠው፤ ያልተሰጣቸው ሥም አለን? አሜኑ ሲባሉ እኮ
የረጉ፣ የጸኑ፣
አስተውሎት የተፈቀደላቸው፤ የተቀቡ፤ የተመረቁ፤ ለእውነት ያደሩ፤ ለሁሉም እኩል
ፍትህ የሆኑ፤ የተባረኩ ማለት
ነበር እሳቸው አላውቁበትም እንጂ።
ከዚህ በላይ
ልዕልና የለም። ስለዚህ እያደቡ የሚያጠቁት ነገር ፈጣሪ ስለማይወደው
ቅጣት እንዳይመጣ በልክ ቢይዙት መልካም ነው እንላለን
ከዚህ ከጭምቷ መንደር። የቁጣ መለኪያም መገደቢያም ወሰንም የለውም እዮር...
ውዶቼ
ተመሳሳይ ሊንኮችን በተደጋጋሚ አቅረቤአለሁኝ እንደ ጭብጡ ሁኔታ በርጋታ እንድታዩት ነው። ሙግቱ ደግሞ ከኢትዮ አፍሪካዊው
ከእጬጌ ጋር ስለሆነ ነው።
ስላቅ አይደለም ኢትዮ አፍሪካዊ ስል አቅሙ ክህሎቱ አላቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ችግሩ መንትዮሽ ፋላጎት ስላለ ሁለት
እግርን በተመሳሳይ ወቅት ሁለት ዛፍ ለመውጣት የማስቡ ሂደት ነው ግጭቱም፤ ፍጭቱም ስበቃውም … በዚህው ይከውን …
ለመበርከት ማበርከት!
ለማበርከት መበርከት!
(ከአቶ ያሬድ አስራት ቲተር ገጽ ላይ የተወሰደ።)
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ