"ተረኝነት" ያደከመኝ አኞ ፖለቲካ ....

 

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።

 ተረኝነት ያደከመኝ አኞ ፖለቲካ .. 

ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ሕይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራር።

„ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔረ

ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“

(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20)



ልብ - ኩላሊት - ሳንባ - ጉበት - አንጀት -

ብቻቸውን ሆነው ሰውን መፍጠር ይችላሉን?

ሰው ውህድ ነው። ኢትዮጵያም እንደዛው ናት። ተገጣጥማ አልተሠራችም። ተብትና አልተሰበሰበችም። ሂደቱ በጥበብ፤ በፈቃደ እግዚአብሄር በፈቃደ አለህ የተከወነ ነው። ይህን ሂደት ጥሶ፤ ይህን ሂደት ረግጦ ይህን የዘመና የሂደት ትረፉት ጨፍልቆ ኢትዮጵያን ልክ የጉልት ድንች የሚያደርግ ክፉ ሃሳብ፤ ክፉ ድርጊት በምድሪቱ ሰፍኗል።

ከዚህ ክፉ ከሚመራው መንጦላዊት ሥርዓት ደግነት፤ መልካምነት ርህርህና አይወለደም። ታስታውሱ ከሆነ ደግነት ተሰደደ ብዬ ጽፌ ነበር። ደግነት ሲሰደድ ሰዋዊነትም፤ ተፈጥሯዊነትም ይሰደዳል። በደግነት የምትታወቀው እናት አገር ኢትዮጵያ እሱንም አሳጥተው አስፈሪ አደረጉት ሁለመናው።

መከራው ተቃሎ „ተረኝነት“ ይባላል። እህ! „ተረኝነት?“ እም! „ተረኝነት“ ኦ! „ተረኝነት“ የሚሆነው ነገር ሁሉ ተራ ነውን? የሚሆነው ነገር በደዴ የሚከውን ነውን? የሚፈፀመው ሰቆቃ „ተረኝነት“ ይገልጸዋልን? ኢትዮጵያ እኮ በስውርም በግልጥም በባዕድ መንፈስ እጅ ወድቃለች። ሱባኤ፤ ድዋ፤ ንግግር፤ ውይይት፤ ምክክር ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔርን ይጠይቃል።

አልሰከንም። አልረጋነም። በውስጣችን ያለው ክፉ ነገር ተሸክሞ ፈተናውን የመሸከም፤ መፍትሄ የማመንጨት አቅም እንደምን አምጠን መውለድ ይቻለናል? እራሱ በችግሩ ደረጃ እንኳን አልተስማመነም እንኳስ በመፍትሄው። እንግሊዞች ችግርን ማወቅ 50% መፍትሄ እንደማግኔት ነው ይላሉ።

ቢያንስ በችግር መሰማማት አልቻለንም። የኢትዮጵያ ችግርን አሁን ያለውን ለማወቅ የናዚን አነሳስ እና ሂደቱን በጥሞና ማጥናት ይጠይቃል። አሉታዊ ዲሞግራፊ ሰታቀድ ኢትዮጵያ ወደ ዬት እዬሄደች እንደሆን የፖለቲካ ሳይንቲስ ሊቀ  -ሊቃውንት አያስፈልገውም ነበር። ያ የዴሞግራፊ ነገር የአንድ ሰሞን የጤዛ ውሎ ሆኖ ነው የቀረው። ፖለቲካው ሰክኖ ከዛ ቢነሳ ቢያንስ ችግሩን መቅረፍ ባይቻልም ወጥ ጉልበታም የሃሳብ አቅም መፍጠር ይቻል ነበር።

ሃሳብ አሸናፊ የሚሆነው በልኩ አቅምን በ አቅም መመከት ሲቻል ነው። አገር ውስጥ አይቻል ውጭ ግን ይቻል ነበር። ከቅምጥ ፍላጎት፤ ከስውር ፍላጎት መውጣት ቢቻል። ከግለሰብ ሰብዕና የግንባታ ፉክክር ይልቅ ያ ሰብዕና የፈጠረች እናት አገር ትቀድም ነበር። ሌላው ቢቀር ማለቴ ነው።

ለዚህ ነው አቅም ባክኖ ምርኮኝነቱ በሁሉም መስክ የሆነው። ችግሩን ማውቅ ነው ተስፋን ማቅረብ የሚችለው የነበረው። ችግሩን በናቅነው፤ በራቅነው፤ በገፋነው ቁጥር ችግር ጠንሳሹ አካል አቅሙን እያጎለበተ፤ ትንፋሹን እዬሰበሰበ የወደደውን ይፈጽማል። የሆነው ያ ነው።

ችግራችን ተራ የተለመደ ተኖ እንዲበትን ተደርጎ ታዬ። አሁን እንኳን የችግሩን ደረጃ ለመቀበል፤ ከዛ ለመነሳት የፖለቲካ አቅም አላይም። አንድ ነፍስ ብቻ የኔታ ጎዳና ያቆብ በጥቅምት ወር የማዬው ነገር „ከተረኝነት በላይ ነው“ ሲሉ አድምጫለሁኝ። የፖለቲካ አቅሙ በዛ ልክ መምጣት ይገባ ነበር። ሊያሰባስብ የሚችለው ሞቶም ይህ ነበር። የታዬው እኮ ምልክት ሳይሆን ድርጊት ነበር።

ዘመኑ ፋሺዝም ስለመሆኑ ከአቅም በላይ ዕውነቶች አሉ። በልኩ ቢታወቅ፤ በልኩ አቅም ቢሰባሰብ፤ በልኩ መደማመጥ ቢቻል ኖሮ አሁን ሁሉም ነገር ከአቅም በላይ ባልሆነ ነበር። ሦስት አመት? በያንዳንዱ ቀን ያለው ሰዓት፤ ሰከንድ ሲሰላ ገዢ መሬት ላይ ያለ፤ ሙሉ ስልጣን ያለው አካል ምን ሊፈጽም እንደሚችል ማወቅ ይገባ ነበር። ማሰብ ይገባ ነበር። የድቀቱ ናዳ ያ ነው ችግሩን አቃሉ ወይንም ችግሩን ጋርዶ ማዬት። የውስጥ ሸሚዝ ፍላጎት እስካለ ድረስ ወደፊትም የከፋ ነገር ነው የሚገጥመው። መነሻም መድረሻም ኢትዮጵያን ማዳን መሆን ካልቻለ እያለቁ መሄድ ግድ ይሆናል።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

16.04.2021

ጎዳናዬ ለሥር ነቀል ለወጥ መታገል ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።