በወጣቶቹ ህልፈት እና እስራት ፖለቲካን ሃራም ያሉ ወገኖች ከውስጣቸው እንዳዘኑ ተረዳሁኝ።

 

በወጣቶቹ ህልፈት እና እስራት ፖለቲካን ሃራም ያሉ ወገኖች ከውስጣቸው እንዳዘኑ ተረዳሁኝ። በተለይ ዘማርያን ሳይለንት ማጆሪቲ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቼ። በዜናሽ እንደነገረችኝ በህይወቴ ሙሉ ወንድ ልጅ እንዲህ ሲያለቅስ አይቼ አላውቅም ሁሉ አለችኝ። አስከሬን ሊሰጥ ሲገባም መታገቱ አብዝተው ለጠቅላይ ሚር አብይ አስተዳደር ይሻሻል እያሉ #ተስፋን #የሚዘግኑ ወገኖች አሁን ላይ እያዘኑባቸው ነው። የብላቴ ሎሬት ፀጋዬ "የወንድልጅ እንባው በሆዱም" እንደቀረበት ከሰጡኝ መረጃ ተረዳሁ።
 
የማያውቁት ሁሉ አለቀሱለት፤ ሃዘንተኛውንም መለዬት አይቻልም ነበር ሲሉ ነበር የገለፁልኝ እነ በዜናሽ ተመስገን። ሥንኝም ቋጥረዋል። የፈለገው ሁሉ የሚደረግለት ወጣት ነበር አሉ። ሰፊ ቤተሰብ እንዳለሁም ሰማሁኝ። እኔ በልጅነትም ዛሬም ቁጥብ ስለሆንኩኝ ምንም አላውቅም። የትውልድ ሐረግ መረጃም አልጠይቅም። 
 May be an image of 2 people and people smiling
 
"እሳቱ ነደደ ጨሰ በዬቤቱ
እንዴት ሆነሽ ይሆን የናሆም እናቱ
እንዴት ሆነህ ይሆን የናሆም አባቱ
እንዴት ሆነሽ ይሆን የናሆም እህቱ።"
 
ከበዜናሽ ተመስገን። 
 
 May be an image of 1 person
ግን ጠቅላይ ሚር አብይ ይህ የህዝብ ሃዘን ዋጋ አያወጣም ብለው ይሆን? ስለምን ሬሳቸው ማዕቀብ ተጣለበት? ምን ያደርግለወታል? ዕውነቴን ነው። ከእምዬ ሚኒሊክ ቢማሩ ምን አለ? ኧረ ልብ ይስጠወ። አሜን።
 May be an image of 1 person, smiling and text
ውዶቼ እንዴት አደራችሁ? እንደምን አረፈዳችሁ? እንደምን ዋላችሁ? ሰላም እደሩልኝ። አሜን።
ሥርጉትሻ አገልጋይ 2024/04/24 በሦስት አራት ስንብት ይሁን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።