የጠቅላይ ሚር አብይ ላንቃወች ፈቃድ ተፈጽሞ ውቧን ማንጠግቦሽን አዲስዓለም ጌታነህ አሰራችሁን? አበስኩ።
የጠቅላይ ሚር አብይ ላንቃወች ፈቃድ ተፈጽሞ ውቧን ማንጠግቦሽን አሰራችሁን? አበስኩ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ዶር አብይ መላቅጡ ጥፍት ብሎወታል። የፓርክ ሥራው አለቀን??? የፕሮጀክት ማናጀር፤ የኢቤንት አስተዋዋቂነቱ ክው አለን? አሁን ደግሞ ጥበብን አያሳዬኝ ብለው ጥበብ ለካቴና ዳረንጎት እዬዳረጉ ነው። መጥኔ። ኧረ አላማረበወትም። ግን መቼ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሚተነፈሰውን አዬር ስ ለካቴና የሚዳርጉት። የቀረ የለም። አማራ ሚስተወትን ይዘው ይቀልዳሉ። "ሲወዱ እስከ ንፍጥ ልጋጉ" ይባላል። አማራን ያነጋገረ፤ ከአማራ ጋር ቡናየጠጣ ካቴና። የአቶ በቀለ ገርባ ማኒፌስቶ በተግባር እዬፈፀሙ ነው።
መቼም ማለፍ አይቀር። ሁላችንም ተጓዥ ነን። ግን ሞትን አስበውት ያውቃሉን??? የሚገርመኝ የተያዘ የተረዘዘው የሚያስረግደወ መሆኑን ነው። ግን ባለቤተወ ብቅ ይሉ ይሆን ወደ ባዕታቸው??? #እሬሳ #ያገቱ፤ #ያሳገቱ፤ #ቢያንስ ፈጣሪን ፍሩ ሁለታችሁም። ከመካከለኛው መቶ ክ/ ዘመን ጀምሮ አሰቃቂ፤ መራራ የሆኑ ሁነቶች ሁሉ ቤተ ሙከራዋ ኢትዮጵያ ላይ ፈፀሙ። አሁን ቀይ ሽብር ዘመን ላይ ይገኛሉ። ነገ ደግሞ የካራማራውን መከራ ናፍቆተኛ ስለሆኑ ይደግሙታል። መጥኔ።
ምን አምጪ ተብላ ነው ደመግቡዋ አርቲስት በእስር እምትንገላታው? የጠሚ አብይ አንደበቶች ያ ያቃለሉት፤ ያጣጣሉት፤ እንደማይረባ ጉዳይ ያዩት አመክንዮ እሬሳ ማገት፤ እሬሳን መበቀል፤ እሬሳን ማስጨነቅ፤ በገፍ ወጭ ወራጅን በሙሉ ለካቴና ማብቃት አልበቃ ብሎ አርቲስቶች የባህሬ መግለጫ አናባቢ መሳሪያ ባልተፈጠረበት ዓለም እምታገኙትን ሰው ሁሉ ሳንሱር ማድረግ ነበረባችሁ ዓይነት ይመስላል የደማሟ አርቲስት እስር።
"መንግሥት ነን እንባላለን" ተግባር ላይ ግን ወገቤን። እኔ
እንደማስበው አናርኪዝም ይመስለኛል 4ኪሎ እያወጋ ያለው።
ማስተዋል የነጠፈበት፤ ፈርኃ አላህ፤ ፈራ እግዚአብሄር የመነበት ዘመን እንዲህም፤ እንደዛም ያደርገዋል። አታጨናንቋት ቀንበጧን።
ማፍቀርም፤ መወደድም፤ የሰው ልጅ ተቀባይነትምሲታደሉት ብቻ ነው። የናንተውስ ግልምት ያደርጋል። አማራ ሲቢላይዜሽን ጠልታችሁ? አማራን ወዳጅ አንይ ብላችሁ? የአማራን ቱሩፋት እናስኬት ላይ ግን ሽሚያ ላይ ናችሁ ለመሰልቀጥ።
ጥበብን አታንገላቷት። ጥበብ ቀልቧ ካረፈበት አበባ ትቅሰም። ጥበብ ትጉህ ናት። የጉሮሮ አጥንት ሁናችሁ አሳሯን አታብሉት። ብትሞካክሩትም አልቻላችሁበት። ማና ቃና የለሽነታችሁ አደባባይ እዬሠፈረው ነው። ማስጨነቅ፤ ማሰር፤ ማገት፤ ማፈን ሥራ ሆኖ ትኩራሩበታላችሁ። መጥኔ ለልዕልት ኢትዮጵያ።
ሥርጉትሻ 2024/04/26
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ