አዲስ ፈተና ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ።

 

አዲስ ፈተና ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 4 peopleMay be an image of 4 people and tree
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በዚህ የጠለፋ እና የእገታ ክስተት ውሳኔያቸው ምን ሊሆን እንደሚችል እጠብቃለሁኝ። በእገታ፦ ከእጃችሁ የገቡት አርበኛ ኮነሬል አሰግድን እንደምን እንደሚይዟቸው አያለሁኝ። የቀደምቶችን ታሪክ ውስጥ የእኔ አሻራ አለበት ብለው በብዙ ሁኔታ አዳዲስ ሁነቶችን አያለሁ።
 
ለምሳሌ ከሥሙ ጀምሮ ጨፍላቂ የሆነው ዓድዋድዋ "#ዜሮ ዜሮ" በዚህ ላይ ጽፌበታለሁ ተዚህ ቀደም። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ምን እና ምን እንደሆነ፤ የህወኃት እና የእርስወ መንግሥት ጦርነት የአገልግል የውሎገብ የጦር ዘመቻወት ከአንገተወት ላይ ስካርፕ እንደ ህወሃት ጣል አድርገው ብዙ በጣም ብዙ ነገሮችን ማንሳት እችላለሁኝ።
 
እምዬ ሚኒሊክ ከእጃቸው የገቡትን የጣሊያን መኮንኖች እንደምን እንደያዟቸው ያውቃሉ። ያውም #በምርኮ። ከንጉሦች ንጉሥ ከእምዬ ሚኒሊክ እስኪ ይማሩ። ይህ #ጠለፋ ነው። ይህ እገታ ነው። ፊትለፊት ተጋጥማችሁ በተመዘገብ የድል ስኬት የተገኜ ዕድል አይደለም። #ምርኮም ወይንም #እጅ #መስጠትም አይደለም። ይህን ተቆራርጦ ከተለቀቀው ቃለ ምልልስ ደጋግሜ ሳዳምጥ ያገኜሁት ግንዛቤ ነው። ዕድሉ #አጤ ስልክ ያመጣው ጣጣ ነው።
 
የሆነ ሆኖ መሪነት በቀል አይደለም። መሪነት #ቂመኝነት አይደለም። መሪነት የአማራን ህዝብ እና ቱሩፋቶችን መሪወቹን፤ #ተምሳሌወችን #ማቃለል#ማጣጣል አይደለም። መሪነት በእጅ የገባን ዕድል በቅጡ መያዝ ነው። ማንገላታት፤ ዱላ፤ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመዋል መጣር፦ #ማዋረድ የሚገባ አይደለም። የሰው ልጅ ፈጣሪ ቤተ መቅደሱ አድርጎ የፈጠረው ክቡር ፍጥረት ነው። ዕምነት ሃይማኖት ክብርን ሲቀበሉ ፍጥረቱን አክብሮ መነሳት ነው። ሰውን ማዕከል ማድረግ። 
 
ሚዲያወቸወት ህጉን እንዲከተሉ ቢያደርጉ ጥሩ ነው። በስተቀር ቢዘግቱ ይሻላል። ይህን ያህል የሚዲያ ህግ ትልልፍ። የገረመኝ የቅብብሎሻቸው ጥድፊያ ነው። #ኢንሳም ሚዲያ ላይ እንደአለ አውቃለሁ። ይህ ሁሉ ለትውልድም ለታሪክም አይጠቅምም። ለመሪነትም አይበጅም። መሪነት ለእኔ በሰባዐዊነትና በተፈጥሯዊነት ፍልስፍና ልቆ እና ተሽሎ መገኜት ነው። ሰባዐዊነት፤ ተፈጥሯዊነት ነው አገርንም ትውልድንም የሚያድነው። 
 
ከፋኝ ያሉ ዜጎች ጫካ ሊመቻቸው አይደለም ዱር ገደል የሚማስኑት። እኔ ያሳዝነኛል። ጫካውንም ስለማውቀው። ዛሬም??? ወደ ሥልጣን ሲመጡም ዘለግ ባለው ፁሁፌ ግንቦት 5/2010 ዓም እኔም ዜጋ ከሆንኩማ ብዬ ጽፌለወት ነበር። ለመሪነት ሳይታሰቡም እንዲሁ አበክሬ የአደኩበት በዓቴ ላይ እንዳይደገም አሳስቤ ነበር። መከፋትን ተከትሎ ሰው ያበጀው የዕንባ ጎርፍ ኢትዮጵያ ሊበቃት ይገባል። 
 
ከፋኝ ያሉት ፋኖወች #መተንፈስ ስላልቻሉ ነው። የአማራ ልጅ ትጥቅ ፈቶ ትዳር አልባ ይሆናል። አይታሰብም። የሆነ ሆኖ ጫካ ከባዱ የሕይወት የፈተና ክፍል ነው። #ውሳኔውም ከባድ ነው። የወጣት አርበኛ ናሆሰናይ አስከሬን አለመስጠት #የማህፀን #ርግማን ነው የሚያስከትለው። ለዛውም ሴት ጆች ያሉት። ሴት እህቶች ያሉት፤ ሴት ሚስት ያለው፤ ሴት የሥራ ባልደረባ ላለው። 
 
አሁንም ኮነሬል አሰገድን በውጊያ፤ በደፈጣ ሳይሆን #በጠለፋ #በእገታ ከእጃችሁ ገብተዋል። እኔ የጦርነት አቀንቃኝ አይደለሁም። የሰው ልጅን ጭንቅላት ውሻ ይዞ ሲመጣ በዓይኔ ልጅ ሆኜ ስላዬሁ ሃራም ብዬዋለሁ። በጦርነት ቀጠና ስለአደኩም አይናፍቀኝም። እንደዛ A+ የነበረ ጭንቅላት ምን ሆኖ እንደቀረ ኑሬበታለሁ። ከደጁ የሚያጠቃ ሲመጣ ግን ምን ይደረግ? ሁሉም ነገር በጣም በዛ እና እዚህ ተደረሰ።
 
የሆነ ሆኖ የዓለም ዓቀፍ ህግጋት ተጥሶ የእስረኛ መብት እንዳይጣስ ነው እምጽፈው። ለእርስወ ፈተና ነው። እንዴት ይህን ችግር ይፈቱት ይሆን? #በቀል #መርዝ ነው። #ቂም #ድዌ። 
 
በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴም ቢጨመሩበት ደስ ይለኛል። ክብርቷ የእምዬ ሚኒሊክን አስተምህሮ ይገፋታል ብዬ አላስብም። እኔ ኮነሬሉ እንዳይንገላቱ ነው አደራዬ በአጽህኖት የሚገልፀው። 
 
ለትውልድ የሚተጋ ከሆነ አንከር የሆኑ ሰብዕናወች ልዩ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል። የአሳምነው ትውልድ በላፒስ ማጥፋት አልተቻለምና። ያ እንዳይደገም። ብርቱ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ክስተት ነው። በዛ ላይ የጥበብ ሰው ናቸው። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/07/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።