የምዕራፍ ፲፮ መግቢያ።
የምዕራፍ ፲፮ መግቢያ።
እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? ሰላም ሰነበታችሁ ወይ? ቤተሰብ፤ ኑሮ፤ ትምህርት፤ ትዳር፤ የፍቅር ጉዞም ከነበረ በምን ሁኔታ ተስተናገደ። በቅድሚያ ጥሞና ላይ መቆየቴን ያላወቁ የተከበሩ የማህበረ - ቅንነት ታዳሚወች ጥፍት ስል በጓዳ መጥተው ጠይቀውኛል። እጅግ በጣም አመሰግናለሁኝ። የማይገኝ ልዩ #ስጦታም ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። በሌላ በኩል ረጅም ጊዜ የጥሞና ወቅት የወሰድኩት ይሄኛው ምዕራፍ ፲፭ ጨርሼ ለምዕራፍ ፲፮ መሸጋገሪያ ጊዜ ረዘም ያለ ይመስለኛል። የጸጋይ ራዲዮ በራዲዮ ሎራም ጠቅላላ ቲሙ የበጋ እረፍት ላይ ነው ሰኞ በ14/08/2025 ቲሙ ከእረፍት መልስ ሥራውን ይጀምራል። የሆኖ ሆኖ ምክንያቴ …… በስሱ …… ግን #ለብም #ድብም ሳይል እንዲህ ልቀጥለው ………
1) #ያው ሁላችሁም እንደምታውቁት እኔ ፌስቡክ የጀመርኩት በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሥልጣን ዘመን ነው። ከዛ በፊት የደጉ ሳተናው፤ የደጉ ዘሃበሽ ቋሚ አምደኛ ነበርኩኝ። በሌላ በኩል የራሴ የጸጋየ ድህረ ገጽም እንዲሁም የፀጋየ ራዲዮ ለሙሉ ፲፯ ዓመታት የተጋሁበት ዘርፍ ነው። የግል ብሎግም አለኝ። ግራቀኝ ዩቱብ ቻናልም አለኝ። በፌስቡክ ግን ዘገምተኛ ነበርኩኝ። ስጀምረው በምዕራፍ ከፋፍየ ነበር። ለምን? አትኩሮቴን አቅጣጫ ለማስያዝ ስለፈለግሁኝ። አንዱን ምዕራፍ ስጨርስ ቀጣዩን ከመጀመሬ በፊት ጥሞና አደርጋለሁኝ። ግራቀኙን ፖለቲከኞች ማድመጥ ይገባል። ግሎባሉን ዓለምም እንዲሁ።
2) #ምዕራፍ ፲፭ እጅግ ረጃጅም ጹሁፎች የተስተናገዱበት ስለሆነ ለአንባብያንም በቂ እረፍት መስጠት ስለሚገባም ነው።
3) #የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጸሐፊም ተናጋሪም ስለአላጣ ድህነቱ ያለ ማድመጥ ላይ ስለሆነ የማድመጫ በቂ ጊዜ መኖርን ባህል መለማመድ ስለሚኖርብንም ነው።
4) እኔ ሁልጊዜ ከተጎዳ ወገን ስለምቆም ከበድ የሚሉ ነገሮችንም ስለምሠራ አንባብያን ውስጣቸው እንዳይጎዳብኝ እረፍት ልስጣቸው በማለት እንጂ፤ ሙሉ ቤቱ ጹሁፍ ነው። በቀን በጣም ብዙ በርካታ ጹሁፎችን ፖስት ማድረግ እችላለሁኝ። ይህን ጸጋ በሙላት የሰጠኝ አማኑኤል ይመስገን። አሜን።
5) #ከእረፍት ስመለስ በቀጥታ ወደ ተለመደው ተግባሬ ገብቼ አንባቢወቼን ከማጨናንቅም እያዋዛሁ መጀመሩ ልማዴ ነው። ባዮግራፊ መለጠፌ፤ ፕሮፋይሌን መቀየሬ ፌስቡኬን ማኔጅ የማደርግበት አንዱ ቋሚ ባህሌ ነው። ከተከበራችሁት የፌስቡኬ ታዳሚወች ውስጥም ፎቶ የሚያስደስታችሁ እንዳላችሁ ስለማውቅም ይህንንም እከውናለሁ። ፍላጎታቸው መከበር ስላለበት ዛሬ በቀጣይ ልከውን ያሰብኩትም ይኽንኑ ነው። የእመቤታችን ተናፋቂ ግን አጭር ሱባኤ ዋዜማ ላይ ስለምንገኝ ረብ ብሎ መሰንበት ስለሚገባንም። ፖለቲካ ተጠናቆ አያውቅምና። ስለሆነም መጣደፍ - አያስፈልግም። በስክነት በአስተውሎት መራመድ ያለንበት የዕድሜ ጣራም ተፈጥሯዊ ሁነት ስለሆነም። እኔ ወጣት አይደለሁም።
6) #ወቃሽ እንጂ #ተወቃሽነትን ፈጽሞ ዕውቅና የማይሰጠው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚሻው ቁምነገር ቢኖር #በአስተውሎት #መራመድን ነው። ይህ መንገድ ውስጤን ይመራ ዘንድ በመፍቀዴም ነው የጥሞና ጊዜየ ዘለግ ያለው።
7) #በቀጣዩ ምዕራፍ ፲፮ በፖለቲካ ወገኖቻችን ከእስር ይለቀቁ ዘንድ እምተጋበት መስኬ ይሆናል። በህፃናት መብት ጥሰት፤ በሴቶች መደፈር፤ መታገት ላይ አትኩሮት ይኖረኛል። ከየትኛውም ወገን ከገዢው ብልጥግና፤ ከተፎካካሪወች፤ ከተደማሪወች፤ #ከተጠማኞች አጓጉል ላይ ካሉት ይሁን ከተቀዋሚወችም ቢሆን ሊሞገት የሚገባው ጉዳይ ወይንም አመክንዮ ሲኖርም ተከብሮ የጉዳዩ ባለቤት ይሞገታል።
ስምንት) የሥነ - ግጥም፤ የሥነ - ጹሁፍ አምድም ደመቅ ብሎ በምዕራፍ ፲፮ ይሠራበታል። በዕለታዊ ተግባር እየተጠመድን በወሳኙ መክሊታችን ላይ የበዛ መዘናጋት ስላለ።
9) #ትውልድ፤ አገር፤ ብሄራዊ ሰንደቅ፤ ብሄራዊ ማንነት፤ ትውፊት፤ ታሪክ፤ ትውልዳዊ ድርሻ፤ አደራ፤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት በሚመለከት የምዕራፍ ፲፮ ቤተኛ ይሆናሉ።
10) #በቤታችን ህግ መተላለፍ፤ ዘለፋ፤ ያልተገቡ የቃላት አቲካራወች፤ የሰውን ልጅ አቃሎ የማየት ስንፍና በጽኑ ይታገል ዘንድ ምዕራፍ ፲፮ ተፈቅዶለታል። እዚህ ቤት የኢትዮጵያ ቀደምት የሞራል ዕሴቶች ይከበሩ ዘንድ የፈቃድ ዘበኞች እንዳለን ሊታወቅ ስለሚገባ ተግባር ላይ ይውላል።
11) በነፃነት የተወለደ ሰብዕና። በነፃነት አገር ተወልዶ ያደገ ሰብዕና የነፃነትን ጥምር ሥነ - ምግባር ፍሬ ነገርን #ሁኖበት፦ ኑሮበትም ሊያሳይ ይገባል። ስለሆነም የአንዱን ነፃነት ሌላኛው ሊጫነው ፈጽሞ #አይገባም። የኢትዮጵያን መንግሥት መሪ የሆነው የብልጽግና የፖለቲካ ድርጅት ይሁን፤ ከእሱ ፖሊሲ የወጡ ወይንም ያፈነገጡ፤ ወይንም አያስፈልገንም ያሉ ሞጋቾች፥ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ አክቲቢስቶች፤ ጋዜጠኞች፤ የጥበብ ሰወች በግልም ይሁን በጋራ የሚታገሉ ሰብዕናወች፤ በተፎካካሪ ወይንም በተቃዋሚ፤ በተደማሪ ወይንም በተጠማኝ፤ በሙሉ የብልጽግና ደጋፊነት ወይንም በከፊል ሞጋችነት የተሰለፋ ወገኖቻችን ሁሉ እኩል #ነፃነት ስላላቸው #ነፃነታቸውን #የመጫን መብት ማናችንም እንደሌለን #ከውስጣችን ልንቀበለው የሚገባ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ምዕራፍ ፲፮፮ ያተኩራል። መከባበርን አንግሶ ማስቀጠል ከእያንዳንዳችን በግል ከሁላችንም በጋራ የሚጠበቅ ትውልዳዊ ድርሻችን ሊሆን ስለሚገባ።
12) #የፖለቲካ ሞጋቾች አክሰሱ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች መንፈስ ሊጠነቀቁ ይገባል። ይህን ከቤታቸው ጀምሮ በጥንቃቄ፤ በአስተውሎት ሊሠራበት የሚገባ በኽረ ጉዳይ ነው። ልጆቻችን እራሳችን እያጠፋን ትውልድ በተስፋ እንገነባለን የማይታረቅ ፋንታዚ ወይንም መሻት ስለሚሆን።
13) #ሁሉንም ሳደምጠው የደረስኩበት ማጠቃለያ ፈላስፊት ኢትዮጵያ፤ ሳይንቲስቷ ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም እንደሆነም ነው። ኢትዮጵያን ማክበር፤ መውደድ፤ መናፈቅ ማለት የገባን አይመስለኝም። በአገራችን ጥልቅ፤ ረቂቅ ጸጋ እና በረከት ልክ የየግላችን ስሜት ገርተን ተሳትፏችን #ሐዋርያ በማድረግ እረገድ ሁላችንም ደካማ መሆናችን በሚገባ ገብቶኛል። ኢትዮጵያን ስታስብ ቢያንስ ካቴና ላይ ስለአሉ ወገንህ ክብሪት ለማቀበል አለመሻማትን መርኽ ማድረግ እንደምን ይከብዳል? መተሳሰብም፤ መተዛዘንም እኮ የአገረ ኢትዮጵያ ውርስ እና ቅርስ ነው። "ልብ አምላክ ዳዊት ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።" ይላል።
እንደምን ለተጎዳው ህዝባችን ተጋሁ የሚል አንድ ሰው ጉዳት ለመቀነስ አስታራቂ የመሆን አቅሙ ቢያንሰው ካቴና ላይ ያለን ወገን አጥብቀህ ያዝልኝ እንደምን ይባላል? የእኛ ዘመን ፖለቲከኝነት እና የቀደምቶች መሪወች የህሊና ዊዝደም ፈጽሞ አይገናኝም። አቻ መሆን ባይቻል የሚቀራረብ ርህርህና ስለምን ድርቅ እንዲመታው በገዛ እጃችን ለምን እንፈቅዳለን? በሁሉም መከራ ውስጥ ድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች፤ እህቶች፤ ሚስቶች፤ ፍቅረኞች ዕንባን በውስጣችን ዕውቅና ልንሰጠው ይገባል። ቢያንስ ሁሉም እናት አለውና።
ክብረቶቼ ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/08/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ኢትዮጵያዊውን #አክብሮትን አክብረን እንገኝ። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ