ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አይበገሬው! የቁም ነገር አባት።

  አይበገሬው! የቁም ነገር አባት።    «አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።» አሜን።   "Kenya Mourns as Trailblazing Leader Raila Odinga Dies at 80 – LCCTV Uganda" https://lcctvuganda.com/kenya-mourns-as-trailblazing.../   አይበገሬው! አፍሪካዊ ፖለቲከኛ የጽናት መሠረትን ጥለው ታግለው የማያሸንፋት ሞት ወሰዳቸው። ይህን የመሰለ የሰላማዊ ትግል አብነት ለኬንያ ቀጣይ ትውልድ ተቋሙ ይሆን ዘንድ እመኝለታለሁኝ። ለእማማ አፍሪካም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊቃናት ይህን ከመሰለ የአይበገሬነት ተምሳሌት ምን ይማሩ ይሆን?   ጥንካሬ፤ ብርታት፤ የተዛባ ሥርአትን በፍርድ ሂደት ውስጥ አስገብቶ መርታት እጹብ ድንቅ ትንግርት ነው። ይህ አርያነት ለመላ አፍሪካ ትምህርት ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው። የማይታየው ረቂቅ አይበገሬው መንፈስ የኬንያ ወጣቶች ስለመብታቸው በሚያደርጉት ደፋር ሰላማዊ ተጋድሎ በዘመናችን ተመልክተናል።    የኬኒያ ወጣቶች አብነታቸውን መራራ ሞት ቢቀማቸውም መሠረቱ ስለተገነባ ሃዘናቸውን ማመጣጠን ይችላሉ። በመጨረሻም ለመላ የኬኒያ ህዝብ፤ ለዲሞክራሲ ለሚታገሉ የነፃነት ፋናወች፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እመኛለሁኝ። ክቡር ሆይ ያባከኑት ቅንጣት ጊዜ የለም። ዕድለኛም ነወት የድካመወን ሰብል አይተዋል። በሰላም ይረፋ። አሜን።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 16.10.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።   “Nairobi, Kenya — October 15, 2025 — A subdued yet searing sorrow has spread across Kenya and beyond today with the news that Raila...

ቸር #አውለኝ ብቻ ሳይሆን፤

 ቸር #አውለኝ ብቻ ሳይሆን፤ ቸር #አሳስበኝ ፤ ቸር #አናግረኝ ፤ #ቸሮችን #አገናኜኝ ማለት የሚጠቅም ይመስለኛል። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ሥርጉትሻ 2025/10/13

#የዳነ #ሃሳብ #ቀድሞ ራስን #ያድናል፤ #ትውልድን #ያድናል፤ #አገር #ያድናል #ቅዱስ #ነውና!

ምስል
  #የዳነ #ሃሳብ #ቀድሞ ራስን #ያድናል ፤ #ትውልድን #ያድናል ፤ #አገር #ያድናል #ቅዱስ #ነውና ! #የዳነ ~ሃሳብ ለእኔ ሰማዕትም ነው። #የዳነ ~ ሃሳብ ብዙ ይፈተናል።   #የዳነ ~ ሃሳብ በወጀብ፤ በብዙ ጦሮ፤ በብዙ ማዕበል ይፈተናል። ግን ህውከቱን ጸጥ አድርጎ ብስጩውን አየር ሳይቀር #ፈውሶ ያሸንፋል።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ምዕራፍ ፲፯     #በር ።   የሥርጉትሻ ቤተ - ቅንነት ውድ ቤተኞች እንደምን አላችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ በጣም ደህ ነኝ። ዕለተ ሰንበትን #ከዳነ ~ ሃሳብ ፍልስፍናዬ ጋር እንወያይ ዘንድ ፈቀድሁኝ። የዳነ ~ ሃሳብ ጋር ስሆን የሚኖረኝ የማሰብ አቅም እና የጤናዬ ሁኔታ፤ ከብስጩ ሃሳብ ጋር ስቆይ የሚገጥመኝ የጤና እክልን ለረጅም ጊዜ በህይወቴ መረመርኩት።    እርግጥ ነው የሚያበሳጨኝ ነገር እኔ ዕውነት ሲንገላታ ነው፤ መርኽ እክል ሲገጥመው። ዕውነትም መርኽም እንደ አቅርቦታችን ስለሚለያይ እኔ መርህ ዕውነት በምላቸው ጥሰት ተፈጽሟል ብዬ ሳስብ ነው በሰጨኝ የሚመጣው። ሙሉ ዕድሜ ላይ እንኳን ስክነቱ በራሱ ይቆጣጠራል። የተፈጥሮ ጸጥታ አስከባሪ ስለሚሆን አይቸግርም። እኔ አብዛኛውን ጊዜየን እማሳልፈው በአገራዊ ጉዳይ ነው። በመፃፍ፤ ሌሎችን በጥሞና በማድመጥ እና በትጋትም በመሞገት።    እራሱን #አንቱ ያለ፤ ወይንም በሌላው አንቱ የተባለ ዕውነት በሆነ አቅም ላይ ምስክርነት ለመስጠት ይሳነዋል። ቆጥቋጣ ነው። ሌላውን ሲያስተልቅ እሱን የሚያሳንስ ይመስለዋል። ደፍሮም አስተያዬት በሚታወቅ ሥሙ ለመስጠትም ራድ የሚይዘው ይመስለኛል። በሌላ በኩል ከክብሩ ዝቅ ያለም ይመስለዋል። በእኔ ቤት ...

አጫጭር ዕይታወቼ።

    #መባረክ #ጥበቃ #ይፈልጋል ። #መመረቅም #ጠባቂ #ይፈልጋል ። #መባረክ #መጨመትን #ይሻል ። #መመረቅም #ስክነት #ይናፍቀዋል ። ሥርጉትሻ 2025/10/11   #ጊዜ #የእግዚአብሄር ነው። #የሰው #ልጅ #በጊዜ #ላይ #የሰናፍጭ ታክል   #አቅም የለውም። ሥርጉትሻ 2025/10/11   #መሰጠትን #አክብሮ የመያዝ #አቅም #እንዲኖር #ጸሎት ያስፈልጋል። #መሰጠት #ከእዮር #ዘንድ ነውና #የጥሞና እንክብካቤ ይሻል። ሥርጉትሻ 2025/10/11   #በግል ህይወት፤ #በማህበራዊ ህይወት፤ #በፖለቲካ ህይወት፤ #በጥበብ ህይወት፤ #በሃይማኖታዊ ህይወት፤ #በአብሮነት ህይወት #የተሰጠን #ብሩክ ፤ #ምሩቅ #ጊዜ በቅጡ ማስተዳደር ካልተቻለ፤ #ጊዜ #ራሱን #ያፈሳል ፤ እንደ አረጄ #ቆርቆሮ ። ከማየት በላይ #አትኩሮት የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። #መሰጠት #መመረጥ ነው። ያን ፈቅዶ #መንደል #መበደል ነው። ከነዳደሉት በኋላ ልለብጠው፤ ልወታትፈው ማለትም ያመለጠ ዕድልነትን ያስታቅፋል፤ ይህ በራሱ ተስፋ ቆራጭነትን ይጸንሳል፤ መጨረሻው አዲስ #ገረጭራጫ ባህሬ እና #ጋድም የማንነት ቀውስን ይጠነስሳል፤ በግልም፤ በቡድንም ሊገጥም የሚችለው የሥነ - ልቦና ቀውስም ምንጭ ሊሆን ይችላል። ሥርጉትሻ 2025/10/11     #በግል ህይወት፤ #በማህበራዊ ህይወት፤ #በፖለቲካ ህይወት፤ #በጥበብ ህይወት፤ #በሃይማኖታዊ ህይወት፤ #በአብሮነት ህይወት #የተሰጠን #ብሩክ ፤ #ምሩቅ #ጊዜ በቅጡ ማስተዳደር ካልተቻለ፤ #ጊዜ #ራሱን #ያፈሳል ፤ እንደ አረጄ #ቆርቆሮ ። ከማየት በላይ #አትኩሮት የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። #መሰጠት ...