ልጥፎች

ከኖቬምበር, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ፍቱን። • የአቶ በቀለ ገርባን #ጸረ ሰው የባቢሎን ግንብ ድምጥማጡን ያጠፋ ድንቅነት። የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ ፊክሽንም ነኮተ። • የህወሃትን ትብትብ ጸረ እኛነት ሴራ የበጣጠሰ ዕፁብነት። • ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

ምስል
  #ፍቱን ።   • የአቶ በቀለ ገርባን #ጸረ ሰው የባቢሎን ግንብ ድምጥማጡን ያጠፋ ድንቅነት። የጸሐፊ ተስፋዬ ገብረአብ ፊክሽንም ነኮተ። • የህወሃትን ትብትብ ጸረ እኛነት ሴራ የበጣጠሰ ዕፁብነት። • ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ምዕራፍ ፲፯       #ዕፍታ ።   ዛሬ ሦስት ዕርዕስን በአንድ ኃይለ ጎዳና "ፍቱን።" አዋዶ የሚገልጽ የጭብጥ ውርርስ ናፈቀኝ። ዓጤ ኢትዮጵያዊነት ዲካህ ያሳሳኛል!   #ጠብታ ።   ይህን የአቶ ፍጹም ፍሰኃ ቃለ ምልልስ እና የመምህር ሲሳይ ቤተሰብ ታሪክ አዳመጥኩት እስኪ። ሊንኩ ከሥር አለ። ከላይም ይደረጋል። ልዕለ ነውና።    «ኢትየጽያዊ ሁሉ ሊሰማው የሚገባ ታሪክ ፥የብሄር ልዮነት አይገድበንም ፍቅር ይበልጣል #story #lovestory » https://www.youtube.com/watch?v=TRFKBTVzcRs የሲሳይ ዮቱብ ቻናል ይህ ነው https://youtu.be/uFWZD0avfVw?si=zMbBmggCobYfOW_u Ethio School Tube   የአቶ ፍጹም ፍሰኃን ፔጁን ሳብስክራይብ ስላደረኩት ኖትፍኬሹኑ ስለመጣልኝ ብዘገይም አዳመጥኩት አርብ ዕለት። ይህን ያህል ግን ከደስታ በላይ ገኃዱን ዓለም እና ሰማያዊውን ዓለም የሚያገናኘውን ውስጣዊ #ሐሤት ይለግሰኛል ብየ አላሰብኩብም። አቶ ፍጼ የሚሠራበት መስክ ላይ ወድቆ እንደማያውቅ ባውቅም። በዚህን ያህልም የረጅም ጊዜ ህልሜን ከተመድም፤ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተፃፃፍኩበትን የፍቅር ተፈጥሮን ካሪክለማዊ የማድረግ ህልሜን በቃለ- ምልልሱ ውስጥ አገኛለሁ ብዬ አላሰብኩም። ለማድመጥ የዘገየሁት...

#እኔን። በዛ በመተማ ቃጠሎ እያገለገለ በግፍ ታግቶ የተገደለ ታናሽ ወንድማችን ነው።

ምስል
  #እኔን ። በዛ በመተማ ቃጠሎ እያገለገለ በግፍ ታግቶ የተገደለ ታናሽ ወንድማችን ነው።      #እናትህን #አያድርገኝ ። #አዳኝ #ታድኖ እንደምን #በጭካኔ #ይገደላል ???? ተጎጅውስ ማህበረሰቡ አይደለምን??? "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ጭንቅን #ተጋሪወች ፤ #መፍትሄም #አመንጭወች #አዛኞች እና #ተንከባካቢወችን የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያወችን #ማን ይሆን ያላቸው? የህክምና ባለሙያወች አገር አቅኝም ናቸው። የሰው ልጅ አለ በሚባልበት ቦታ ሁሉ በቀን ሃሩር፤ በሌሊት ግርማ ሞገሱን ታግስወ በቅንነት የሚተጉ ሊቀ ትጉኃን።    እንደዚህ በየሄዱበት እያገለገሉ ደመ ከልብ ሆነው የሚቀሩ አሳዛኝ ፍጥረቶች ሆኑ። በስንት ድካም፤ በስንት ልፋት የሚገኝ ሙያ እና የጥረት ስኬትም ለባሩድ ጭካኔ ተዳረገ። አገልግሎቱ ቢቋረጥ በዚህ ጭንቅ ጊዜ ምን ትጠቀሙ ይሆን? የቻለ ወደ ተሻለ ቦታ ሄዶ እንዳይታከም ሁሉ ነገር ዝግትግት ብሏል። ማህበረሰቡ ለዓይኖቹ ስለምን ጥበቃ አያደርግም በየተራ????ለምንስ በጋራ አይመክርም??? መፍትሄ ፈልጉ እባካችሁን???   ለሰማቱ ሊቀ ትጉኃን ለመላ ቤተሰቡ ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁኝ።    ሥርጉትሻ 2025/11/2025   እግዚአብሄር አምላክ ሁሉ ይቻለዋል እና ሰማያዊ ርትህ ይስጥበት።    ውቦቹ ውዶቹ ቤተ ቅንነት እስኪ ደህና አርፍዱ። ቸር ያሰማን። አሜን።   /// ከመተማ ኮምኒኬሽን ያገኜሁት ነው። ይህ ግን መፍትሄ አይሆንም። ሌላ ነፍስ አድን የተደራጄ ጥበቃ ለባለሙያወች ሊደረግ ይገባል። መኖር ይፈትናቸዋል። ደግሞ እንዲህ ህይወታቸው ይነጠቃል። " ………በግፍ እና በአሰቃቂ ሁኔታ ሂወቱን ለተነጠቀው ...

ብጹዑ አባታችን በመከራችን ሁሉ ቀድመው የሚገኙ #ሐዋርያችን ናቸው። ማገዶነት ለብጹዕነታቸው ብርቃቸው አይደለም። የኖሩበት ነው።

ምስል
  ብጹዑ አባታችን የመከራችን ሁሉ #ሐዋርያችን ናቸው። ማገዶነት ለብጹዕነታቸው ብርቃቸው አይደለም። የኖሩበት ነው።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     በዛ ግራጫማ ህወሃታዊው ዘመን እንኳን ሳይፈሩ፤ ሳያርዱ ከተከፋ ልጆቻቸው ጋር ሆነው #ግማድ የተሸከሙ፤ አንደበተ #ርዕቱ ፤ ብቁ እና #ጥንቅቅ ያሉ ስጦታችን ናቸው። እንደምን ያለ #እብድ ዘመን እንደሆነ ትናንት አየሁኝ። በብፁ አባታችን አቡነ አብርኃም ፎቶ ላይ #ኤክስ ምልክት እንደምን ያለ መዳፈር ነው? እንደምንስ ያለ ህግ መተላለፍ ነው? ክርክር አላስፈለገኝም። መራራ ስንብት ነው ከወዳጄ ጋር ያደረኩት።    ከዚህ ቤት፤ ከቤተ - ቅንንነት እንኳንስ #ሐዋርያትን ማንም ሰብዕ፤ እንሰሳ፤ ዕጽዋት ሳይቀር የሚከበርበት ነው። የሰብዕን ፎቶ #መዘቅዘቅ ፈጽሞ #አይፈቀድም ። በማንኛውም ሰው ላይ የኤክስ ምልክት ማድረግም የተከለከለ መንገድ ነው። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ፤ ሰብለ ሕይወት የማንን ጎፈሬ እማበጥር ይመስላችኋል። ነገረ ትውልድ ትርታዬ ነው። ስለ ትውልዱ ስጽፍ በፆም በጸሎት በመጠሞን ነው። ከልጆች መፃህፍት ቅንጣት ዝበት አታገኙም። ልጆቻችን እኛ ባለፍንበት ትርኪ ምርኪ፤ ግፋፎ ሁነት ማለፍ የለባቸውምና።   ስለሆነም ከባህላችን ውጭ የሆኑ ፆታ ነክ ጉዳዮን ተደፍረው ከዚህ ቤት አይለጠፋም። ካገኜሁም አይቀሬው ስንብት ይሆናል። ሌላው ቀርተው በቋንቋችን ውስጥ ያሉ ጸያፍ የሆኑ አገላለፆችን መጠቀም እንኳን አይፈቀድም። አማርኛ ቋንቋ #ዲታ የለማ ቋንቋ ነው። እንደ ጀርመንኛ ቋንቋ።    አንድ ፊደል ብቻውን ከትርጉም አልፎ ዕጣ ነፍሱን #ቅኔን ይቃኛል። ዕርዕስ መሆን ይችላል። #ቃ የሚለው አንድ ፊደል ዘርፈ ብዙ ትርጉም አለ...