ልጥፎች
ከ2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡ የአለፋ ጥቁሳን መንደድ ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት። ህወሃት የተነሳበት ዓላማ እየተሳካለት ነው። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰። #በምልሰት የጣና ወርቅ ትዝታን። ጭልጋ አውራጃ ጭልጋ ወረዳ፤ ማጠቢያ ወረዳ፤ ቋራ ወረዳ ውስጥ አንዱ አለፋ ጣቁሳ ነበር። አለፋ ጣቁሳ የቅቤ፤ የማር፤ የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን ማንኛውም #የቅመማቅመም ዓይነት የሚመረትበት፤ በእንሰሳት ተዋፆ ከአሳ ጀምሮ ዕምቅ ሃብት ያለው፤ በዕት ነው። እራሱ ደልጊ ከመድረሳችሁ በፊት የመኪና መስኮቱን ስትከፍቱት የደንቢያን ለጥ ያለ የሽንብራ አዝመራ ሲዘናጠፍ እያያችሁ የደልጊ የቅመማቅመም ህብር ጠረን አቀባበል ያደርግላችቿል። ሆቴል ይዛችሁ ምሳ ስታዙ #ዓሳ በዓይነት ይቀርባል። እኔ ጎርጎራ እና ደልጊ የበላሁት የዓሳ ጥብስ ጣዕሙ አብሮኝ ይኖራል። ጎንደር ከተማ ክርምትን ተከትሎ የዓሳ ገብያ የደራ ነው። የዓሳ መሰናዶም በየቤታችን ልዩ ነው። ያው በልጅነት እሾ ቢያስቸግረንም። የሆነ ሆኖ ወዛችሁን እርፍ አድርጋችሁ ሥራ እስክትጀምሩ ድረስ #ሰላምለኪ ጣና ለማለት ወደ ወደቡ ጎራ ትላላችሁ። ጣና እራሱ #አገር ነው። ዲካ የለውም። በሁሉም አቅጣጫ ብትዘዋወሩ ጣናን የዓይኔ ጥግ እስከዚህ ድረስ አይቶታል ብላችሁ መወሰን አትችሉም። የእቴጌ ጎንደር ዝክረ - ማንነትም ከዚህ መሰል እዮራዊ #ትንግርት የተቀዳ ነው። እንዴት ዋልክ ጣናሻ/ እንዴት ሰነበትክ ጣናወርቅ? እንደምን ባጀህ የእኔ ጣና ብላችሁ የቤተ - ዘመዱን፤ የዘመዳ ዘመዱን ወግ ካደረሳችሁ...
የረዳት ፕሮፌሰር አውግቸው ሲሳይ #አድራሻ #ታወቀ ይሆን?
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የረዳት ፕሮፌሰር አውግቸው ሲሳይ #አድራሻ #ታወቀ ይሆን? #መረጃው ያላችሁ እባካችሁ አጋሩኝ። የድርጊቱ አፈፃጸም የሚጨንቅ #ጠረን አለውና? እራሱ በህይወት መኖራቸውን ማረጋገጥ የሚያስፈልግ ይመስለኛል? ልጅ ሞገስ ዘውዱን ባለፈውም መረጃ እንዲያፈላልግ በፔጄ ላይ አሳስቤው ነበር። እሱ ስለ ረ/ ፕሮፌሰር አውግቸው ያለውን #የቀደም በትውቃቸው ዘመን ያለውን መረጃም በቅንነት አጋርቶ፤ እኔም አጋርቸለት ነበር። የብልጽግናን ሹመኞች ከሚያገኙ ሚዲያወች አንዱ የሃሳብ ገበታ ነው። ይህን እኔ #በአወንታዊነት ነው የማዬው። ሁሉም ሰው መብት አለውና ያሻውን፤ የፈለገውን አቅጣጫ የመደገፍ። ዴሞክራሲ እኮ ይኽው ነው። በእኛ ላይ ሲደርስ እንፈራዋለን፤ እንሸሸዋለንም። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ግን እንዴት አደራችሁ? እንደምንስ አረፈዳችሁ? ቸር ያሰማን ፈጣሪያችን። አሜን። ሥርጉትሻ 07/03/26 ፍትህ ለረ/ ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው
#ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ ንጉሥ ለእየሱስ ክርስቶስ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ ንጉሥ ለእየሱስ ክርስቶስ። #ሰማይ ቤት። ዛሬን ሰንበትን ለካቴና ላሉ ወገኖቻችን። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ጌታ ሆይ!… መቼ ይሆን የኢትዮጵያ እናቶች ከጭንቀት ወህታቸውን የምትመርቅላቸው? #ወገኖቼ ሆይ! እንዴት ሰነበታችሁ? እንደምንስ አላችሁ? እንዴትስ እየሆናችሁ ነው? በምንስ ሁኔታ ትገኛላችሁ? #ውስጤ ። ባለፈው ጊዜ ቲክቶክ ላይ የሎዛ ሚዲያ ቲም በቃሊቲ የሚገኙ የእናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን በቃሊቲ ተገኝተው ሲያጽናኑ ነበር። ዕውነቴን ብነግራችሁ #ዕንባዬን ፈጽሞ መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር። በቃ! ሁለመናዬ ተበጠበጠ። ተሸበርኩኝ። በዚህ አጋጣሚ የሎዛ ሚዲያ ቲምን እጅግ ላመሰግን እወዳለሁኝ። የእስር ቤቱን ኃላፊወችንም እንዲሁ። ብዙ፤ በጣም ብዙ ሥማቸውን የማናውቀው እስረኞች በየአዳራሹ አሉ። #እርግጥ ነው። ማዕከል ላይ የፖለቲካ ስጋትም ፍርሃትም ነው። ከመዕከል፤ ከክልል በታች ባሉት ዞን እና ወረዳ ላይ ግን፤ #በቀል ፤ ምቀኝነት ሊኖርበት ይችላል። ጦርነቱ፤ መፈናቀሉ የኑሮ ውድነቱ ላይበቃ እስር በጣም የሚያስጨንቅ ክስተት ነው። ለእሰረኛ ቀለብ ለማቅረብም ለታሳሪ ወገኖች እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ነው። መተዛዘንም ይገባል። #የፍትህ ሚኒስተር እና የስኬት ተስፋው በኢትዮጵያ። ለኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስተር የተመደቡት አንዲት ገና በለጋ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣት ናቸው። በሌላ በኩል ተቋሙ ከፖለቲካ ድርጅት ነፃ መሆን ሲገባው የፍትህ ሚኒስተሯ ወ/ ሮ ሃና አርያሥላሴ ብልጽግናን ወክለው በፋና የምርጫ የመሞገቻ መድረክ ላይም ተገኝተዋል። በጣም አስደንጋጭ ክስተት ...
"Ethiopia: Authorities must investigate sexual violence, summary killings and torture by OLA fighters Warning:
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
https://www.amnesty.org/.../ethiopia-authorities-must.../ "Ethiopia: Authorities must investigate sexual violence, summary killings and torture by OLA fighters Warning: This press release contains descriptions of sexual violence and torture. Members of Ethiopia’s Oromo Liberation Army (OLA) have subjected women and girls to sexual violence committing rape, gang rape, sexual slavery, summary killings and destruction of civilian property which may amount to war crimes, during the conflict which started in the Oromia region in 2019, Amnesty International said in a new briefing today. The briefing, “No one came to my rescue: Gang rape, sexual slavery and mass displacement of women in Oromia, Ethiopia,” documents the atrocities against civilians particularly women and girls committed by the OLA armed group in Sayo and Anfillo woredas (districts) of Kellem Wallaga zone between 2020 and 2024. “For seven years, under the cover of darkness caused by a communicat...
BBC. "አምነስቲ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ሴቶችን "በወሲብ ባርነት" ይዘዋል እና "በቡድን ደፍረዋል" ሲል ከሰሰ
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
· የአምንስቲ ዘገባ። BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/c74334ywn0jo "አምነስቲ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ሴቶችን " በወሲብ ባርነት " ይዘዋል እና " በቡድን ደፍረዋል " ሲል ከሰሰ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት በሴቶች እና ሴት ልጆች ላይ " የወሲብ ባርነት " እንዲሁም " በቡድን መድፈርን " ጨምሮ የተለያዩ ወሲባዊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲል አዲስ ባወጣው ሪፖርት ከሰሰ። የታጣቂ ቡድኑ አባላት በሴቶች ላይ የፈጸሟቸው ፆታዊ ጥቃቶች፣ ከፍርድ ውጪ የሆነ ግድያ እና የንጹኃንን ንብረት የማውደም ድርጊቶች " በጦር ወንጀልነት ሊፈረጁ የሚችሉ " እንደሆነ አስታውቋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አርብ የካቲት 27/2018 ዓ . ም . ይፋ የደረገው የምርመራ ሪፖርት፤ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱት የታጣቂ ቡድኑ አባላት ከአውሮፓውያኑ 2020 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት የፈጸሟቸውን ድርጊቶች የዳሰሰ ነው። ምርመራው የተደረገው በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ በሚገኙት ሳዮ እና አንፊሎ ወረዳዎች ውስጥ እንደሆነ ገልጿል። የሰብአዊ መብቶች ተቋሙ ምርመራውን ሲያከናውን በቡድኑ አባላት ወሲባዊ ጥቃት ለተፈጸመባቸው 10 ሴቶች ቃለ መጠይቅ ማድረጉን እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ማነጋገሩን እና የሕክምና መዝገቦችን መመርመሩን አስረድቷል። በምርመራው ...