ልጥፎች

ከማርች, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአማራ ትግል የህልውና ከተባለ ለምን "መግደል፤ መጨከን፤ ማስጋት፤ #ዛቻ አጀንዳ ሊሆን ቻለ?

  የአማራ ትግል የህልውና ከተባለ ለምን "መግደል፤ መጨከን፤ ማስጋት፤ #ዛቻ አጀንዳ ሊሆን ቻለ?   የሰው ልጅ ሰርክ ሞቱ ከሆነ እንደ እህል #ያልቃል ? #መገደልን ለማስቆም አነጣጥሮ #መግደል መፍትሄ አይሆንም። ማስጨነቅን ለማስቆም ጫናዊ ማስጨነቅ ጎዳና ሊሆን አይችልም። መሳደድን ሃራም ለማለት #ዛቻ ስጦታ ሊሆን አይገባም።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።   እኔ የአማራን ትግል በሁለት ከፍዬ አየዋለሁኝ።   1) የማንነት ትግል። 2) የህልውና ትግል ብዬ።   ይህን የምልበትን አመክንዮ ፌስቡክም ሳልጀምር፤ ከ፲፪ ዓመታት በላይ ብዙ ጊዜ በዝርዝር ስለፃፍኩበት ደክሞኛል። የአሁኑ ዝምታዬም ማህበራዊ መሠረቱ የተናደበት ሁሉ ወደ ዘርፋ #ስለተመመ በጥሞና ማድመጡ ይበቃል ብዬ ስለወሰንኩኝ ነው።   "በሉት! በርቱ! አሳዱት! ግረፋት!" የሚላችሁ የሚዲያ ባለቤት ሁሉ ሙሉ ሦስት ዓመታት የተፈጠሩበት የደቡብ ቀጠና፤ ለብልጽግና ቀጥ ለጥ ሰጥ ብሎ እየተገዛ መኖሩን አስከብሮ ይገኛል። ደቡብ ጫካ ጠፍቶ ነውን አንድ የፋኖ ሻለቃ ማደራጀት ያቃተው? ዛሬ በብልፄው ካቢኔ ውስጥ 50+ ደቡብ ነው። በዘመነ ህወሃትም እንዲሁ።   ድል ቢቃረብ እዛው ሚዲያቸው ላይ እንደተለመደው የእንቶኔ የነፃነት ፋኖ ተብሎ ተደራጅቶ የድል አጥቢያነቱን ሲታወጅ እናዳምጣለን። አሁን ግን ሰርክ ሞት፤ መከራ፤ ጭንቅ፤ ፍርሃት በገፍ ይቀናለታል ለአማራ "ጀግና" በሚል ቅጥያ።    እነሱ ህዝባቸው #ማገዶ እንዲሆን ፈጽሞ አይፈቅዱም። ፡ተቋሞቻቸው ደርጅተው ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ፤ ተጨማሪም አዳዲስ ፕሮጀክቶች ተወጥነው ከግብ እንዲደርሱ ነው የሚጥሩት። በብልፄው መዋቅርም ከውጭ ጉዳይ ...

«#ፍቅር እስከ መቃብር» በደቡብ አፍሪካ። የላቀ #ሐዋርያነት በእማማ አፍሪካ።

ምስል
  « #ፍቅር እስከ መቃብር» በደቡብ አፍሪካ። የላቀ #ሐዋርያነት በእማማ አፍሪካ።    "ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም።"   የሐዋርያው፤ የድንግሉ የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ፩ ወደ ቆሮንቶስ ሰወች፦ ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፰። እኔ ይህ መልዕክትተ - ቆረንቶስ የያዛቸው ዶግማወች ሁሉ የዓለም መዳኛወች ናቸው ብዬ አምናለሁኝ። ከባዶች ናቸው። የሚችሉ ግን ህይወቱን እንዲህ ይኖሩበታል።   #ምዕራፍ ፲፰።       https://www.youtube.com/watch?v=dJHU3VpaFDI ባለጠጋው በመጨረሻም ወደ ህዝብ መጣ! Eyoha Media |Ethiopia | Habesha https://www.youtube.com/watch?v=5EUNo6RvTLY የባለጠጋ ሚስት ለመሆን ከሃገር ወጣሁ! ከባዱን የኔን ሚስጥር ዛሬ ላጋራችሁ ነው! Eyoha Media |Ethiopia | Habesha   #ጠብታ ።   የዮሃ ሚዲያ ላይ የወጣውን ክፍል ፩ የክብርት ኤንጅልን ታሪክ እህቴ ልካልኝ አዳመጥኩት። ከዛ ክፍል ፪ ስጠብቅ ወጣ እና ሁለት ጊዜ አዳመጥኩት። #ሐዋርያዊ ተልዕኮ ያለው ገጠመኝ ነው።   ለማህበረ ቅንነት በትህትና የማሳስበው መጀመሪያ ክፍል ፩ አድምጦ፤ ክፍል ፪ መቀጠል የሚገባ ይመስለኛል። ታሪኩ ልበወልድ አይደለም። መሠረት ያደረገው የዕውነት #ዕውነትን አድርጎ ነው። ለጋብቻ ውጭ አገር የሄደች ኢትዮጵያዊት ሴት፤ የኤድስ ፈተናን እንደምን እንደተጋፈጠችው፤ የፈጣሪ ስጦታ ከሆኑት ክቡር ሚስተር ኬኒ ጋር ነው ታሪኩ። ይመስጣል። ያስተምራል። የፍቅር ተፈጥሮን የፈተና ስቅዛቶች እና ጀግኖች ሲገኙ ደግም እንደምን መቋቋም እንደሚችል ያስተምራል። ቁሞ #ይሰብካልም ።    የገኃዱን ዓለም የሥ...

ለመላ የዕስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ እንኳን #ለ1147ኛው በዓለ ዒድ አደረሳችሁ።

ምስል
      እንዴት ሰነበታችሁ የእኔወቹ፣ የእኛወቹ ቅኖቹ ፣ #ዛሬ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የፆም #መፍቻ ነው።    ለመላ የዕስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ እንኳን #ለ1147ኛው በዓለ ዒድ አደረሳችሁ።   የእናንተ #ዱዋ ይጠቅማል እና እባካችሁን የዓለማችን #ጢስ መሆንን ፈጣሪ ያስታግስ ዘንድ በርቱል።   ሥርጉትሻ 20/03/026

#ለመክሰስ ያልበቃን፤ ይህ ተይዞ ነው #ስንካሰስ ውለን የምናድረው። ቤታቸውን እስኪ #ከውስጡ ሆነን እንየው። ሰውኛነት ከእኛ ጋር ከሆነ።

ምስል
  #ለመክሰስ ያልበቃን፤ ይህ ተይዞ ነው #ስንካሰስ ውለን የምናድረው። ቤታቸውን እስኪ #ከውስጡ ሆነን እንየው። ሰውኛነት ከእኛ ጋር ከሆነ።    "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፰።       #ለመክሰስ ያልበቃን፤ ይህ ተይዞ ነው #ስንካሰስ ውለን የምናድረው። ቤታቸውን እስኪ #ከውስጡ ሆነን እንየው። ሰውኛነት ከእኛ ጋር ከሆነ። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" #ምዕራፍ ፲፰። #ስንት #እኛወች ይሆን #ያለነው ? #ስንትስ #ስንቶችስ ነን። ቀና ብሎ ለመሄድስ ያስችለን ይሆን?? አደጋው ብቻ አይደለም። #መኖራቸው ብዙ ይናገራል። የለበሱት፤ የቤታቸው ሁኔታ ይናገራል። የከረባት፤ የገበርዲን፤ የሽብሽቦ፤ የሚኒ፤ የኩላኩል፤ የልብስ ፋሽን፤ የስታይሊንግ ዓይነታችን እና #ዕውነቱ #ገብያ ላይ ሲሆን እኛ ይህን ኑሮ እንመስላለን። ቢቀድም የውስጣችን መጎሳቆል፤ እኛን እና እኛን የሚያፎካክር፤ የሚያቧክሰን፤ ፊት የሚያዞር፤ ከመቃብርህ፤ ከመቃብሬ የሚያስብለን ምንም ፋክት፤ ምንም ዕውነት ባልኖረ ነበር። ከዚህ በላይ የእኛነት ገላጭ ራዲዮሎጂ የለምና። ልብ እያለን በልባችን ላይ #ሸፍተን ፤ ማስተዋል ተሰጥቶን በቅጽበታዊነት ስንካሰስ ዘመኑ እንሆ የተደከመበት፤ የተለፋበት በግልም በጋራም የተለፋበት፤ ሳያፈራ፤ ወቅታት #ዕንቡጣቸው ጠውልጎ፤ ወራት ቡቃያውን #ማስቻል አቅቷቸው፤ በሳምንታት ዘሩ #ለችግኝ ሳይደርስ እዛው መክኖ ይቀራል። ያፈሰስነው - ጉልበት፤ የምንጋጭበት ወዘተረፈ ገመና፤ በከንቱ የባከነው አቅም፤ ወጣትነታችን ተምሎበት መኖ የቀረበት ዕውነቱ ይህ ነው፤ በምስሉ የምታዩት። ይህም ሆኖ፤ ዛሬም እኛ ግን እራሳችን #ሽሽት ላይ ነን። እኛን በእኛ ውስጥ እንዳናዬው ግርዶሹ ዕውነትን፤...