አዲስ አበቤ ሆይ ይቅናህ!
ለዘላቂ ህልውና አይ ተመራጭ መንገድ ነው። „ጽኑ ፍለጋ ታሳያለህና ወደ መርከብም በመውጣት ኖኅን አድነሃልና።“ መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ቀጣዩ የአዲስ አባባ ዕጣ ምን ይሆን? ከአልጎሼ አይጠራም። ብራቦ አዲስ አባባ! ህልውናህን የሚጠ በ ቀው በአቅምህ ልክ ነው። ክብርህ የሚጠ በ ቀው በህሊናህ ልክ ነው። መኖርህ የሚረጋገጠው በጥበባዊ የአይ ተጋድሎህ ልክ ነው። አዲስ አበቤ ሆይ! የእኔ አዲስ አባባ ብለህ መነሳትህ የተገባ እና ፍትኃዊም ነው። አዲስ አባባ የእኔ፤ የአንተም፤ የእንቺም፤ የእርስዎም ናት ብለህ መነሳትህ መልካም ነው። ተቋማዊ ካልሆነ ግን የወረት ነው የሚሆነው። ጤዛ! አዲስ አበቤ ሆይ! አቅምህ ዝምታህን ጥሶ መውጣቱ ጎሽ የሚያሰኝ ቢሆንም ይህን አቅምህን ወደ ባለቤት ያለው ተቋም ማሰደግ ግን ግድ ይለሃል። ተጋድሎው በዚህ መልክ እንደ ሳሙና አረፋ ተኩረፍርፎ መቅረት ሳይሆን 50 ዓመት በትጋት እና በታታሪነት ተዶልቶ 27 ዓመት ተመስጥሮ የቆዬው ለመደራደሪያነት የነበረው የአንተ የህልውና ክስመት ድንጋጌ ነበር። የአንተ የቁም የቀብር ሥርዓት ነበር። የአንተ የብትን አፈር ለማኝነት ሌጋሲ ነበር የ50 ዓመቱ የታጋድሎ ዝክረ ድንኳን። አዲስ አበቤ ሆይ! ህልውናህን ከነገ ባሻገር ማዬት፤ ከማግስት ባሻገር ማድመጥ፤ ከበስቲያ በላይ በርቅት ገና ላልተወለዱት፤ በጽንስም ላልታሰቡት ልጆች እና የልጅ ልጆችህ ስለሆኑ ዛሬ ብቻ ሳይሆን በተከታታይ ሳትሰለች፤ ፈጽሞም ሳትደከም በጀመርከው መልክ ትግልህን አቀናጅተህ በትእግስት፤ በማስተዋል፤ በፍር ኃ እግዚአብሄር፤ በፈር ኃ አላህ ማድርግ ይኖርብሃል። አዲስ አ...