"ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግሥት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም"
የአቨው ተጋድሎ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" "ሰምቸዋለሁ ፁሁፋን ያገኜሁት ከአቶ አብይ ጥላሁን ነው። "ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግሥት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም" ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጻቸው በአስተላለፉት መልዕክት በሻሸመኔ ከተማ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ኦርቶዶክሳውያንን ከክልሉ የማጽዳት ዘመቻ የሚመስል ኢ-ሰብዓዊ እና ኢ-ሕገ መንግስታዊ ድርጊት መፈፀሙ መላው ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ድርጊት ነው በማለት ገልፀዋል። ብፁዕነታቸው አያይዘውም ለሕዝብ የተቋቋመው መንግሥት የሕዝብን ሰብዓዊ መብት አለማክበሩ ሳያንስ በአንዳንድ አካባቢዎች ብሎም መንግሥት በሚመራቸው ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ሠራተኞች ኦርቶዶክሳውያን መልበስ የምትችሉት እኔ የመረጥኩላችሁን ብቻ ነው በሚል ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣውን ቀኖናዊ ትዕዛዝ ምዕመናን እንዳይፈጽሙ ብሎም እንዲሸማቀቁ በማድረግ እያካሄደ ያለው አፈና ዲሞክራት ነኝ ከሚል መንግሥት የማይጠበቅ ፣ መብታችንን የረገጠ እና ከቀደሙ አፋኝ መንግሥታት ሥርዓት የተለየበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያዳግት ተግባር ነው ብለዋል። ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን ከምን ጊዜውም በላይ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ እና አቅጣጫ ብቻ በመከተል የመብት ጥያቄያችን በተግባር እስከሚመለስ እና የመኖር መብታችንን እስከምናረጋግጥ ድረስ በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንድንቀጥል ሲሉ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል። በተጨማሪም የጸጥታ አካላት ለሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ጠባሳ ከመጣልና ሰላማዊ ክርስቲያኖችን ከማሳደድ እንድትቆጠቡ እንጠይቃለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።"