መደራጀት ሊፈራ አይገባውም።
ይህ ግርባው ብአዴን ዬወጣቱን መንፈስ ሲያደነዝዝ በነበረበት በ2011 ዬጻፍኩት ነው። መደራጀት ሊፈራ አይገባውም። • እፍታ። መደራጀት ኃይል ነው። መደራጀት አቅም ነው። መደራጀት ስንዱነት ነው። መደራጀት ፍቅር ነው። መደራጀት አብነት ነው። መደራጀት የታማኝነት ማስፈጸሚያ ነው። መደራጀት የህሊና መቅኖ ነው። መደራጀት ዓላማና ግብ ያለው ሰብዕና ማለት ነው።መደራጀት የአብሮነትም አንባ ነው። መደራጀት የሥን - ልቦና ቅዬሳ ተቋም ነው ለአዎንታዊ ከተጠቀምንበት። ይህችን ለመግቢያ ከከሽንኳት በኋላ እምጠቅሰው በመደራጀት ዙሪያ ያሉ ጥቂት ነገሮችን ነው። በጽንሰ ሃሳቡ ዙሪያ ሌላ ጊዜ ብመለስበትም ትንሽ የአማራ ወጣቶች በገጠማው አንኳር ችግር የምለው ይኖረኛል። • ወግ። የአማራ ወጣቶች እዬተደራጁ ነው። ማህበራቸው ነፃ እና ገለልተኛ ነው። ማህበራቸው ዓላማ እና ግብ አለው። ዓለማ እና ግብ ደግሞ የአንድ ድርጅት መሰረታዊ ጉዳይ ነው። የአማራ ወጣቶች መደራጀት የአዳማን ሥርዕዎ መንግሥት አላስደሰተም። ስለሆነም እውቅና እንዲነፈገው ተደርጓል። ከሰኔ 15 በፊት በነበረው ሰንበት የደብረታቦር ወጣቶች ኢንጂነር ይልቃልን ጌትነትን ጋብዘው ነበር ነገር ግን ታግደዋል። ይህ መቼም እኔ እብደት ነው የምለው። ሰው ያበደ ዕለት ጋብቻን ያግዳል። ልክ እንደ ባቢሎን ግንብ ቀያሹ እንደ አቶ በቀለ ገርባ ማለት ነው። ነፍሳቸውን ይማረውና ዶር አንባቸው መኮነን በመሩት ጉባኤ ደብረታቦር ላይ የወጣቶች ጉባኤ ነበር። አቶ ዮኋንስ ቧያለውም ተገኘተው ነበር። ሁለተኛ የወጣት ድርጅት አስፈላጊ አለመሆኑ በአጽህኖት ሲገልጹ ሰምቻለሁኝ። በፖለቲካ በሳል ከሆኑ አንድ የፖለቲካ ሊሂቅ የማልጠብቀው ገለጻ ነበር። በተፎካካሪያቸው በአብን ላይም የነበራቸው ምልከታ ጤናማ አልነበረም። ፖለቲካ በ...