ልጥፎች

ይድረስ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን። ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ።

ምስል
  ይድረስ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን። ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም" የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማን እና ስለማን ይሆን የተቋቋመው??? #ስለአለቅትነት ይሆን??? አነሳችሁብኝ። እንደምን ሙሁራን ለሚያቀርቡትገንቢዕይታ ዕውቅና መስጠት ተሳናችሁ???? #ቁስለት ! የተከበሩ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ከአደባባይ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በጥሞና ለአራት ጊዜ ያህል አዳመጥኩት። አምስተኛውም ለአዲሱ ዓመት ተቀጥሯል። አይጠገብም። ተቋም ነው። የአወያዩ የአቶ አቤል ጋሹ የአጠያዬቅ ዘዬም ለፕሮፌሰር ሚንጋ ሜጋ አቅም ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ አግኝቼዋለሁኝ። በዚህ ዓመት በመቆጠብካዳመጥኳቸው ቃለ ምልልሶች ቀንዲሉ ሆኖልኛል ለእኔ። የኢትዮጵያን ክብረት እና አዱኛም ፏ ብሎ ያዬሁበት አጋጣሚ ነበር ማለት እችላለሁኝ። መስጦኛል። ተደምሜበታለሁኝ። ውስጤንም አግኝቸበታለሁኝ። ፕሮፖጋንዲስት ለማያስፈልገን ኢትዮጵያዊ ዜጎች ልካችን አግኝተናል ብዬ አስባለሁኝ። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያነበቡ፤ የተረጎሙ እና ያመሳጠሩ ከሳይለንት ማጆሪቲ ውስጥ ያሉ በቲም ፈላስፊቷን አገሬን ይመሩ ዘንድ ዕድሉን እንዲያገኙ እምመኜውም። ፌስ ቡኬ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ሼር የማደርገው። ባሉኝ ሁሉ ሚዲያወቼም ብሎጌን ጨምሮ ሼር አድርጌዋለሁኝ። ከማህበራዊ ሚዲያ ርቀው ለሚኖሩ ወገኖቼም ሼር አድርጌዋለሁኝ። የጠራ አቅጣጫ ያለው ብቻ ሳይሆን አብዝቶ ቅንነትን ማዕረጉ ያደረገ መሰጠትን ስለአገኜሁበት። የጨመተ እና የሰከነ፤ እላፊ ያልሄደ ጠፈፍ ያለ የእኛነት የኔታነትን አይቸበታለሁኝ። መስታውትም ራዲዮሎጂም ማለት እችላለሁኝ። በፍፁም ሁኔታ የገረመኝ ደግሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወቴ ከልጅነት እስ...

ለምን ሥማችሁን #አብይ አትሉትም? ጓዘ ቀላል ጥያቄ ለፋና፤ ለዋልታ፤ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ፤ #ለኦሚኮ።

ምስል
  ለምን ሥማችሁን #አብይ አትሉትም? ጓዘ ቀላል ጥያቄ ለፋና፤ ለዋልታ፤ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ፤ #ለኦሚኮ ። ኢትዮጵያ አዲስ አበባ። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"     እንዴት ናችሁ ማህበረሚዲያወች። የማንእንበላችሁ? የማንስ ትሰኛላችሁ? መቼ ይሆን ለገባችሁት ሙያዊ ቃል ሟች ሆናችሁ የምትገኙት? ዘወትር አንጋችነት አይሰለቻችሁም? ግን ስለምንሥማችሁን አብይ አትሉትም።መሃያ ቆርጠው የሚያስተዳድሧችሁ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ናቸውን? በቃ የሳቸው ውሎ አዳር ዘጋቢ ብቻ ሁናችሁ ቀራችሁ እኮ? ግን የቀራችሁንስ መቼ ታስደምጡን ይሆን? የሌሊቱን አዳርንም፤ የጠሎት ሥርዓቱን ሁለመናውን ልጠቅሰው የማልሻውን ሁሉ? እሳቸውም እኮ እንደ እናንተ ኢትዮጵያ ቀጥራ የምታስተዳድራቸው አገልጋይ እንጂ አሰሪያችሁ አይደሉም። ይህንያክልግልምት ብሎን እስኪያቅለሸልሸንድረስ ዝክረ እሳቸው ብቻ? ሥራጠፋን? የሚገርመኝስለ ራሺያ እና ዩክሬን፤ ስለ ፍልስጤም እና እስራኤልሐተታ አላችሁ። አንዳንድጊዜ ፋና፤ ዋልታ፤ ኢቲቢ፤ ጁቢተር ላይ ያላችሁ ይመስለኛል። በቃ የመጠቃችሁ። የደም አላባ፤ የዕንባ ጎርፍ፤ የድሮንሥልጣኔ በህዝብ፤ በቅርስ፤ በውርስ፤ በሃይማኖት፤ በትውልድ ላይቀንከሌት በጭካኔ እዬዘነበእናንተ የጠቅላይ ሚር አብይአህመድን ፋንታዚስታቆላምጡ፤ ስታሽሞነሙ ግንመሬት ላይ ስለመኖራችሁ ይረዳኛል። ለእኔ በኢትዮጵያ መከራ ላይ እያላገጠ፤ እዬተጫወተ ያለው እናአረመኔነት እንዲንሰራፋ፤ ትውልድ በባዕቱ፤ ትውልድ በሁለመናው ይነቀል ዘንድ እዬሠራችሁ ያላችሁ ሚሳኤሎች እናንተው ናችሁ። የጥፋት መልዕክተኝነትን ስለምን እንደምንትከባከቡ ይጨንቃል። ይጠባል። የኢትዮጵያ አምላክም ሩቅ ይመስላችኋል። የኢትዮጵያአምላክም የማይፈርድይመስላ...

ፅናት ማሸነፍ ነው።

ምስል
 ያጣኽውን በማጣትህ ከፀፀተህ በገደልከው በደል ውስ ለመኖር አትፍቀድለት።   አገርን ፈጣሪ ከመረቃት አይዞሽ ባይ እረኛ ይሰጣታል። ይህ ካልሆነ አገር የህዳር ዝናብ እርግማን እንደታዘዘባት ትረዳለህ። ሰብል አልባ ትውልድም አደራም እራፊ መጠጊያ ዬልብ ዓይን የላቸውም እና።    የክፋት ሽርሽር በደግነት ላይ ማፈናቀልን ለመተግበር ነው።    ገዳዮች እርቃናቸውን ተወልደው፣ እርቃናቸውን ኖረው፣ እርቃናቸውን ከመሬት ጋር እርክክብ ይፈፅማሉ። ክትመት።    ትዝታ ሲሄዱ ማደር ነው።    ፅናት ማሸነፍ ነው።    የህሊና ድንግልና የትውፊት ማህደር ነው።     ማድመጥ ሥጦታ ነው። እራሱን የማድመጥ አቅም ያለው ሌላውን ለማድመጥ ዳጥ አይሆንበትም። አቅል ያለው ትውልድ የሚገነባውም ይህ መሰል ሰብዕና ያላቸው መሪዎች ሲኖሩት ብቻ ነው። መታደል ከበለፀገ፣ ምርቃትም ከተበራከተ የተስፋ አዝመራ ይኖራል።    ትውልዱን የምናባክነው እኛ ነን። ከትናንት የተሻለ ሥርዓት መፍጠር ስላልተቻለን። ለምን? በውዳሴ ሥካር አቅም ስለሚባክን።  ትውልዱ ይረገማል። ረጋሚዎቹ ዘመኑን አባካኞች ናቸው። የእነሱን ዘመን አክስለው፣ የዛሬውን ቀምተው፣ የነገን ማሳረር የተፈጠሩበት ነው።  ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019        

ደግነት የሚያኖረው የራስን ኑሮ በማኗኗር ነው

ምስል
 ደግነት የሚያኖረው የራስን ኑሮ በማኗኗር ነው። ይህ ደግሞ ለትውልድ ያለአስተማሪ የመኖር የኔታ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ክፋዎች ሳይኖሩ የኖሩ ይመስላቸዋል። መኖራቸውን ቀምተው የሚኖሩት ኑሮ ሙጃ መሆኑን አያስተውሉትም እና።

ምስል
 ክፋዎች ሳይኖሩ የኖሩ ይመስላቸዋል። መኖራቸውን ቀምተው የሚኖሩት ኑሮ ሙጃ መሆኑን አያስተውሉትም እና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

የዕድሜ ዕርጅና አይጭነቅህ፣ በጭንቅህ ውስጥ እራስህን የሸጥክበት ዘመን ከሌለ።

ምስል
 የዕድሜ ዕርጅና አይጭነቅህ፣ በጭንቅህ ውስጥ እራስህን የሸጥክበት ዘመን ከሌለ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ልብ ከሰጠህ።

ምስል
 የፍቅርን ሙሉ ዋጋ ለሰጠኽ ቀን ካላከበርከው ያጣኽው ዕለት ተቋም ይከፍትልኃል። ትማርበት ዘንድ አዲስ ህሊና ይሸልመኃል፣ ልብ ከሰጠህ።  ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ምን ብላ?

ምስል
 በእሾህ ውስጥ የበቀለች ፅጌረዳ ለእሾኽ ምክር ትለግሰዋለች። ምን ብላ? አትዋጋ እያለች። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ቅን ልብ ቧ ፏ ያለ የተከፈተ የገነት በር ነው

ምስል
 ቅን ልብ ቧ ፏ ያለ የተከፈተ የገነት በር ነው። የቅኖች ዘመን ቅንነት ብቻ ነው። ቅኖች ምንም አይኑራቸው በህሊና ድንግልናቸው ብቻ የመንፈስ ዲታዎች ናቸው። ቅኖች የአደራ ዕዳ የለባቸውም። የሰው ልጅ የተፈጥሮ መርህ ነው። የተፈጠረበትን ሲጥስ ማን ይባል፣ ምንሥ ይባል ይሆን? Sergute©Selassie ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019      

የሳንባን ሥራ ለማቃለል ዕውነትን ይፈልጉ።

ምስል
 የሳንባን ሥራ ለማቃለል ዕውነትን ይፈልጉ። ዕውነት ያለበት ቦታ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ድርሽ ላይል እርግማን አለበት እና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ገላጣ ላይ የተጋለጠ ዕብለት ብዙም ፕሮፖጋንዲስት አያምረውም።

 ገላጣ ላይ የተጋለጠ ዕብለት ብዙም ፕሮፖጋንዲስት አያምረውም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019

አማራነት ሰውነት ነው።

ምስል
 አማራነት ሰውነት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019    

ድፈሩት! አማራ ነኝ በሉ!

ምስል
 አማራነት ከፀጋው የሚነሳችሁ፣ ከበረከቱ የሚነፍጋችሁ፣ ከምርቃቱ የሚያሳጣችሁ የለም። ድፈሩት! አማራ ነኝ በሉ! ቸሩ አማራነት ሁሉም አለውና ያሰብላችኋል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019  

አማራ ነኝ የምትሉ ዝም ብላችሁ አዳምጡት፣ አጥኑት። ወደ መልካም ነገር ይመራችኋል።

ምስል
 አማራ ነኝ የምትሉ ዝም ብላችሁ አዳምጡት፣ አጥኑት። ወደ መልካም ነገር ይመራችኋል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2019  

አማራ ስትሆን ፈርኃ እግዚአብሄር ፈርኃ አላህ ይገዛኃል። ይልኙታም ይዳኝኃል።

ምስል
 አማራ ስትሆን ፈርኃ እግዚአብሄር ፈርኃ አላህ ይገዛኃል። ይልኙታም ይዳኝኃል። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019    

ጥበብን በሴቶች ተፈጥሮ ውስጥ ተመስጥሮ ታገኜዋለህ።

ምስል
 ጥበብን በሴቶች ተፈጥሮ ውስጥ ተመስጥሮ ታገኜዋለህ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019 

ቅኖችንም፣ ቅንነትንም የፈጠረልን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን

ምስል
 ቅኖችንም፣ ቅንነትንም የፈጠረልን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን። የእነሱ መኖር ከጨለማዊ ቀስት እንድንበት ዘንድ ልዩ ምርቃት ነውና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019 

ክፋነት የህሊና እድገት ዘገምተኝነት ነው።

ምስል
 ክፋነት የህሊና እድገት ዘገምተኝነት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 17.12.2019 

#ጤናችን።

  #ጤናችን ። ከአቶ ኃይሌ አሳምነው ገፅ የተወሰደ ለጤናችን። "የሳምባ ምች/Pneumonia የሳምባ ምች በአንዱ ወይም በሁለቱም ሳምባ ላይ የአየር ከረጢቶች ላይ ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ የሳምባ ምች ከመጠነኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ሲሆን በህፃናት፣ እድሜያቸዉ ከ65 ዓመታት በላይ ለሆኑ አዛዉንቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ በተዳከመባቸዉ ሰዎች ላይ እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሊያመጣ ይችላል፡፡ የህመሙ ምልክቶች የህመሙ ምልክቶች:- የህመሙ ምልክቶች ህመሙን እንዳመጣዉ የጀርም አይነት፣ የታማሚዉ እድሜና አጠቃላይ የጤንነት ሁኔታ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡ መጠነኛ የሳምባ ምች ያላቸዉ ሰዎች የህመም ምልክቶቻቸዉ ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም ህመሙ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ የህመም ምልክቶቹ የሚከተሉትንም ሊያጠቃልል ይችላል፡- • ትኩሳት፣ማላብና ብርድ ብርድ ማለት • ሳል • በሚያስሉበትና በሚተነፍሱበት ወቅት የደረት ላይ ህመም • የትንፋሽ ማጠር • ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣ተቅማጥ ናቸዉ፡፡ የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ? የአተነፋፈስ ችግር፣ የደረት ላይ ህመም፣ የማይቀንስና ከ39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት፣ የማያቋርጥ ሳል በተለይ መግል የመሰለ አክታ ከገጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡ ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች የሳምባ ምች ማንኛዉንም ሰዉ ሊያጠቃ ይችላል፡፡ነገር ግን በጣም ተጋላጭነትን ከሚጨምሩት ዉስጥ • ከ2 አመትና ከዚያ በታች የሆኑ ህፃናት • ከ65 አመትና በላይ የሆኑ አዛዉንቶች ሌሎች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ • የበሽታ መከላከል አቅምዎ የተዳከመ ከሆነ፡- የኤች አይቪ ኤድስ፣ የአካል ንቅለ-ተከላ የተደረገላቸዉና የካን...

እኔ የሚገርመኝ ጦርነቱ ሲጀመር ምን ሲሉ የነበሩ፣ ዛሬ ምን እያሉን እንደ ሆን ሳዳምጥ ይገርመኛል። ዝም ቢሉ ምን አለ?

ምስል
 እኔ የሚገርመኝ ጦርነቱ ሲጀመር ምን ሲሉ የነበሩ፣ ዛሬ ምን እያሉን እንደ ሆን ሳዳምጥ ይገርመኛል። ዝም ቢሉ ምን አለ? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20/12/2021