#ድርድር ፍላጎትን #ሴንትራላይዝድ ያደርጋል።
#ድርድር ፍላጎትን #ሴንትራላይዝድ ያደርጋል። እ ንዴት አደራችሁ? ማደር በራሱ ከፈጣሪ ጋር ባለ ስምምነት የሚከወን ነው። አድረን ሲነጋልን ፈጣሪን እናመስግነው። #ድርድር መንፈሱ በተፈጥሮው #ፖዘቲብ ነው። ድርድር የተዳዳሪን የጋራ ቅንነት መሠረትም ግንባታ ይጠይቃል። ቅንነት አቅም፤ ጊዜ፤ ተጨባጭ ሁኔታዊ የመሟላት ብቃትን ይጠይቃል። ድርድር መስዋዕትነትን ይቀንሳል ብቻ ሳይሆን ጠቅላላውንም ሊያስቆም ይችላል። ድርድር በአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባላት እና አካላት እንኳን በደንቡ እና በፕሮግራሙ ይገለጣል። የአንድን የፖለቲካ ድርጅት ደንብ እና ፕሮግራም ሲቀበል አንድ ሰው አባል ይሆናል። በቀጣይም በአቅሙ ልክ አካልም ሊሆን ይችላል። አካል እና አባልነት የኃላፊነት እና የተጠያቂነት ጉዳይ ነው። የሆነ ሆኖ አንድ ሰው የአንድን የፖለቲካ ድርጅት አልቀበልም ካለ አባልነቱም ከፍ ሲል አካልነቱም አይኖርም። በሁለቱ ማህል ያለው አንኳር ጉዳይ ድርድር ነው። አንድ የፖለቲካ ፍላጎት ከድርድር መንፈስ ውጪ ኤግዚት ሊያደርግ አይችልም። ፖለቲካ በውስጡ የሚያካታቸው ሥነ - ምግባሮች፦ የርዕይ እና ግብ ፍላጎቶች የአፈፃፀም መሪ ሰነዶች በውስጣቸው ድርድር ይዘው ነው። ድርድር ለፖለቲካ ተቋም የምንግዜም #ጽንሱ ነው። ድርድር ቅንነትን አብዝቶ ይይዛል። #አወንታዊነትንም #አዳብሮ እና #አሰልጥኖ ይይዛል። ድርድር #የስልጡን #ህሊና #ጭማቂም ነው። ድርድር ከልብ ከሆነ ብልጠት ሳይሆን #ብልህነት ነው። እምትሰጠው ይኖራል። እምታገኜውም። ድርድር ፍላጎትን ሴንትራላይ ያደርጋል። እርግጥ ነው ድርድር ጥንቃቄን፤ እርጋታን፤ ስክነትን፤ ጥሞናን፤ አርምሞን አብዝቶ ይጠይቃ...