#ድርድር ፍላጎትን #ሴንትራላይዝድ ያደርጋል።

 

 

 
#ድርድር ፍላጎትን #ሴንትራላይዝድ ያደርጋል።
ንዴት አደራችሁ? ማደር በራሱ ከፈጣሪ ጋር ባለ ስምምነት የሚከወን ነው። አድረን ሲነጋልን ፈጣሪን እናመስግነው።
 
#ድርድር መንፈሱ በተፈጥሮው #ፖዘቲብ ነው።
 
ድርድር የተዳዳሪን የጋራ ቅንነት መሠረትም ግንባታ ይጠይቃል። ቅንነት አቅም፤ ጊዜ፤ ተጨባጭ ሁኔታዊ የመሟላት ብቃትን ይጠይቃል። ድርድር መስዋዕትነትን ይቀንሳል ብቻ ሳይሆን ጠቅላላውንም ሊያስቆም ይችላል። ድርድር በአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባላት እና አካላት እንኳን በደንቡ እና በፕሮግራሙ ይገለጣል።
 
የአንድን የፖለቲካ ድርጅት ደንብ እና ፕሮግራም ሲቀበል አንድ ሰው አባል ይሆናል። በቀጣይም በአቅሙ ልክ አካልም ሊሆን ይችላል። አካል እና አባልነት የኃላፊነት እና የተጠያቂነት ጉዳይ ነው። የሆነ ሆኖ አንድ ሰው የአንድን የፖለቲካ ድርጅት አልቀበልም ካለ አባልነቱም ከፍ ሲል አካልነቱም አይኖርም። በሁለቱ ማህል ያለው አንኳር ጉዳይ ድርድር ነው። 
 
አንድ የፖለቲካ ፍላጎት ከድርድር መንፈስ ውጪ ኤግዚት ሊያደርግ አይችልም። ፖለቲካ በውስጡ የሚያካታቸው ሥነ - ምግባሮች፦ የርዕይ እና ግብ ፍላጎቶች የአፈፃፀም መሪ ሰነዶች በውስጣቸው ድርድር ይዘው ነው። ድርድር ለፖለቲካ ተቋም የምንግዜም #ጽንሱ ነው።
 
ድርድር ቅንነትን አብዝቶ ይይዛል። #አወንታዊነትንም #አዳብሮ እና #አሰልጥኖ ይይዛል። ድርድር #የስልጡን #ህሊና #ጭማቂም ነው። ድርድር ከልብ ከሆነ ብልጠት ሳይሆን #ብልህነት ነው። እምትሰጠው ይኖራል። እምታገኜውም። ድርድር ፍላጎትን ሴንትራላይ ያደርጋል።
 
እርግጥ ነው ድርድር ጥንቃቄን፤ እርጋታን፤ ስክነትን፤ ጥሞናን፤ አርምሞን አብዝቶ ይጠይቃል። ከሁሉ በላይ ቂም እና በቀል ውስጥ አለመኖርን ማረጋገጥ ጉልላታዊ ጉዳይ ነው። በስተቀር ይናዳል።
 
#እርገት ይሁን ለሃሳቤ።
 
ለመዳራደር ፈቀድክ ማለት ትግልህን አቦዝንክ ማለት አይደለም። ወይንም ተስማማህ ማለት አይደለም። ለድርድር ፈቀድ ማለት ተስፋን ሰነቅ ማለት ነው። በተጨማሪም የውስጥ ሰላምህን ፍላጎት አደመጥክ ማለት ነው። በተለይ ለህዝብ ተስፋ በጥንቃቄ ነገረ ድርድር ካልተያዘ የማይታዩ ተስፋ መቁረጥ እና የሥነ ልቦና ችግርም ያመጣል። ድርድርን ሃሳቡን ስትቀበለው የዓለም የሰላም አባት አማኑኤል፤ ደጋጎች ቅዱሳን ሐሤት ያደርጋሉ። ለምን? አባታችን የውስጥ ሰላሙን ብራንድ አድርጎታል። ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ፈቅዶ፤ ባርኮ እና ቀድሶ ሰጥቶናልና።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04/06/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።