ለትውልድ ጤናማ ዕድገት

 ለትውልድ ጤናማ ዕድገት ስክነት፤ መረጋጋት፤ ለችኩል ጉዳዮች አደብ ገዝቶ መመርመር፦ #መመካከር ያስፈልጋል። በስተቀር ኮሽ ባለ ቁጥር መበርገግ ዓላማን ያስታል። ተስፋን ያኮማትራል። 

ሁልጊዜ ተደላድሎ በማድመጥ ብቃት ክህሎትን ስለሚያጎናጽፍ፦ ደራሽ ጉዳዮችን አትኩሮት በመስጠት አብሮም ባለመግለብለብ እራስንም ትውልድን ያድናል። 

ጥድፊያ፤ ግልብልብ ነገር፤ ብስጭት፤ እልህ #ለሰብላማነት ሩቅ የሚያጓጉዙ ሳንኮች ናቸው። #ጥሞና ለዬትኛውም መስክ ጠቃሚ እና አትራፊ ነው። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


ሥርጉ03/06/2024

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።