ጥቂት ስለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ስለ ፋኖሻ። አፈጣጠሩ #ክስተትም ነው። የፋኖ መንፈስ።

 

ጥቂት ስለአማራ ህዝብ ቀይ የደም ሴል ስለ ፋኖሻ።
አፈጣጠሩ #ክስተትም ነው። የፋኖ መንፈስ።
(በኦዲዮም ሠርቼዋለሁ በመሃል የአሜሪካ መግለጫ ሲመጣ ታገስ ተብሎ ነው።)
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of text
 
ፈኖ መሠረቱ #ገጠር ነው። ገበሬው ነው መሠረቱ። ይህ ማለት ተፈጥሮው #ተፈጥሯዊ ነው ማለት ነው። ችግር ኖረ አልኖረ ፋኖ ለተፈጥሮም ጥበቃ ታጥቆ በተጠንቀቅ ይጠብቃል ሁልጊዜም። ውሩሱ ቅርሱም ነው። ፋኖ #ቆቅ ነው። ፋኖ ጥሪቱ በራስ የመተማመን አቅሙ እና ፈራሃ አላህ ፈርሃ እግዚአብሄር መሆኑ ነው።
በፋኖ ቤት #ዕብለት#ክህደት ዝር አይልም። ታማኝነቱ ተማላ አይደለም። ፍፁም እንጂ።
ሰባዕዊ ትጉህ እና ታታሪ። ሥራ ወዳድ፤ በቲም ወርክ የሚያምን ዓራት ዓይናማ ነው።
 
በጀቱ የራሱ የመኖር ዘይቤ ብቻ ነው።
 
አደረጃጀቱ በተፈጥሮዊነት በሚያውቀው በዕቱ አበጥሮ፦ አንተርትሮ የሚያውቀውን መሪ በመፍጠር #በጎበዝ #አለቃ ይመራል።
 
በፋኖ ቤት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚል ውራጅ ማንነትን አይቀበልም። ያስፈነጥረዋል። አያውቀውም። 
 
#ተጠያቂነት እና ኃላፊነት።
 
በራሱ ፈቅዶ የሚደራጀው ፋኖ በተፈጥሯዊ ይትብኃል፦ በአባት አደሩ ዘይቤ በጎበዝ አለቃ ደስ ብሎት ይመራል። ይህን ወዶና ፈቅዶ ስለሆነ ይቀበለዋል። ደስ ብሎትም ይፈጽማል። እጅግ በጣም ዲስፕሊን ነው። የተከረከመ። ጥንቁቅ እና የተግባር አንባ ነው።
#ፋኖ እና የፖለቲካ ድርጅት።
 
ፋኖ ፖለቲካ ድርጅት የሚባል የትውስት አሰራር እና አረዳድ ግጥሙ አይደለም። እሱ በተመሰጠረችው እናቱ ሥር ስለሚሆን ሚስጢሩን ሳያፈስ በርጋታ ይጠቀምበታል። ፋኖ ተሸንፎ የማያውቀውም በተፈጥሯዊ ሚስጢሩ ሥር ስለሚሆን ዊዝደም ይቀርበዋል።
#ፋኖ በአንድ ዕዝ ሥር ስለማድረግ።
 
ይህ ለፋኖ ከባድ ፈተና ነው። ፈተናው ሲከብደው እርግፍ አድርጎ ወደ መደበኛ ሥራው ይመለሳል። ኢትዮጵያ ያለተፈጥሯዋ ስለሆነ ነው ሶሻሊዝም ሙሉ 50 አመት ርካታ የመከነበት የሆነችው። ስለዚህ ፋኖ በአንድ ማዕከል እናድርገው ቢባል #ይፈርሳል#ይናዳል። 
 
#ሊሆን የሚገባው።
 
ፋኖ በአባታደሩ አመራር ዘይቤ ቢበዛ ክፍለአገር ላይ መቆም ይኖርበታል። እንጂ ፋኖ ከምክትል ወረዳ በላይ አደረጃጀት ኑሮት አያውቅም።
 
1) አገር ቤት ያሉ ፋኖወች መሪወቹ ተነጋግረው #ግብረ ኃይል ሊፈጥሩ ከቻሉ ጥሩ ነው። የሁሉም ፋኖ ጉባኤ በዬጦር ወረዳቸው ተሰባስበው የክፍለ አገር መሪያቸውን መምረጥ ይችላሉ። ሽዋ፤ ጎንደር፤ ጎጃም፤ ወሎ አራት መሪወች እዬተመካከሩ #ሁሉም #እኩል #ኃላፊነት እና ተጠሪነት ባለው ሁኔታ ሊስማሙ ይችላሉ። አንድ ሰው ይምራ ከተባለ ግን #ይናዳል
 
ውጭ አገርም በአንድ ለመምጣት የአራቱ አካላት በአንድ ላይ ሆነው እኩልነት ባለው ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ማደራጀት ይችላሉ። ሲዊዞች እኮ በ7 መሪ ነው የሚተዳደሩት። የላቀ ትዕግሥትና የማስተዋል ልዕልኒቸውም አንቱ ስለሆነ። 
 
አንዱ ጠቅልሎ ላስተዳድር ካለ ግን ፍርሻ ይሆናል። ምክንያቱም በበጀት ስለማይተዳደር፤ ማዕከላዊ የእዝ ቀጠናለመፍጠርም አስቸጋሪ ስለሆነ ለሽምቅ ተዋጊ። ተፈጥሮውም #ገበሪያዊ ስለሆነ በአንድ ፈሰስ እናማክለው የሚባለው አይሳካም። የተስፋ መራራ ስንብት ይሆናል።
ሥርጉትሻ ዳገት ቁልቁለቱን፤ በርኃ ደጋውን ማስና አደራጅታለች። ስለዚህ የገበሬው ሰብዕና ልኩን ታውቃለች። በሥራ የጎንደርን እና የአርሲን፤ በጉብኝት የጎጃም እና የሽዋን፤ የጋሞን በግል ጥረት በስሱ አይቸዋለሁ። ገበሬ ገርነቱ በአምላክ በአላህ መጠጋቱ ርህርህና እና ተፈጥሯዊነቱ ይመሳሰላል።
 
በሰብዕና አወቃቀር ደግሞ የደጋ፤ የቆላ፤ የወይና ደጋ ገበሬ ልዩ ነው። አሁን የእብናት ገበሬን ከራስ ጋይንቱ፤ የጭልጋን ገበሬ ከፋርጣ ጋር ላውህድህ ቢባል ጋዳ ነው።
#የገበሬ ንቅናቄ።
 
አሁን ያለው ንቅናቄ #የገበሬ ንቅናቄ ነው። ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ሙሁራን አሉ። መኖራቸው መልካም ነው ግን የገበሬውን ሥነ ልቦና አጥንቶ አክብሮ መነሳት ይገባል። ገበሬ ሳይማር የተማረ ነው። መነሻው ገበሬ የሆነ ደግሞ ከመነሻ ተፈጥሮው ላፈንግጥ ቢል ፍርሻ ይሆናል። ፈጽሞአይቻልም።
 
ወጥ የፖለቲካድርጅትም፤ ወጥ የእዝ ማዕከልም ለማምጣት ከባድ ነው። ዘዬው አይገጥም። በተፈጥሯቸው ልክ ሲሆን ግን በዓይን በመንፈስ ይግባባሉ። ምክንያቱም ፋኖ ዛሬ የተፈጠረ አይደለም። ዕድሜ ጠገብ ባህልና ትውፊት ያለው ክስተታዊ መንፈስ ነው።
 
 ይህን መንፈስ ፖለቲካ ድርጅት ይፈጠር፦ የዕዝ ማዕከል ይኑር ድል ከተገኜ በኋላም ልዩ ጥበብ ይጠይቃል። ገበሬ ሲያምን በሙሉ ልብ ነው። ወለም ዘለም የለም። ክህደት ሲፈፀምበትም ሃራም ብሎ ጥቁር ውሻ ውለድ ተባብሎ ተረጋግሞ ተከርክሞ ይኖራል።
 
የፋን እንቅስቃሴ በልባቸው መስጥረው የፖለቲካ ድርጅትን አካል ያደረጉ እንዳሉ ይሰማኛል። ያ የማይሆን ካልኩሌሽን ነው። ተስፋው ሳይፀድቅ መራራ ስንብት ይሆናል። በእርግጠኝነት ነው እኔ እምናገረው። 
 
ይህን መሰል ዝንባሌ ያላቸው ወገኖች እንደአሉ አስባለሁ። ግፍ ነው። ያ ራፊ የለለው አራሽ የተሰዋበትን ለፖለቲካ ድርጅት አሳልፎ መስጠት.? ፋኖም እራሱን የቻለ የፖለቲካ ሥልጣን ሊኖረው ይገባል። እራሱን ወክሎ እንጂ ተዳብሎ ወይ በአንጋችነት አትሰቡት። ትቢያ ላይ ያለ መንፈስ ገድል ሊሠራ ይችላል። የሆነ ሆኖ ፋኖሻ የደማበትን፤ ኑሮውን የበተነበት ሞፈር ቀንበር የፈታበት የተገበረበትም ነውና እንዲህ ያለ የዋዛ ልግጫ ሊቆም ይገባል።
 
ሌላው የፋኖ ሥም ሽሽትም አያለሁ። እሱ እዬሞተ እሱ ለሚሞትለት ዓላማ እና ተግባር ግን የሌላ ፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ ተሸካሚ ማድረግ ወንጀልም ነው ለእኔ። 
 
ሌላው የተዥጎረጎረ ዓርማ ነው ያላቸው ሁሎችም። ፋኖ እኮ ዓርማው እናቱ ናት። ዓርማ እኮ ምንም ነገር አያስፈልግም። የኢትዮጵያ ንፁሁ ሰንደቅ የሁሉም መለያ ሊሆን ይገባል። እንደ ፖለቲካ ድርጅት ዘንባባ ሚዛን ወዘተ አያስፈልገውም። ለነገሩ እሱም ተረት ተረት ሆኖ የቀረው። አቤት ስንት ዓይነት ዓርማ አዬን። አብሶ ለገበሬው ውስብስብ ያለ፦ ጥንቅርቅር ያለ ጉዳይ አያስፈልግም። ንጡኋ ሰንደቁ በቂ ናት። 
 
ሰማዕትነት ዩዳንቴል ሥራ አይደለም። የሰው ልጅ በአንድ ቀን ተፀንሶ በአንድ ቀን ዩንቨርስቲ አይመረቅም። ተጣድፎ መቀላቀል ተቧክሶ በአንጃ መለያዬት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የኖረበት አሳር ነው። አሁን ኦሮሞወች ከ10 በላይ // ተጋሩም አምስት፤ አማራም ሲቢክሶች ብዙ ናቸው። የሆነ ሆኖ ንፁህ ዓላማ ድንግል ግብ ያለው ጉዳይ ወጥነት፦ አህቲነት ምኑ እንደሚያቅት አይገባኝም። ገበሬውን በዚህ ሽንቁር ለመሰንቀር ያለው ሃሳብ ተገቢ አይደለም።
አራቱ ክፍለ አገሮች እንደ አንድ ይሆኑ ዘንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ በቂ ነው። እሱም የገዘፈ ፈተና ስላለበት የፋኖ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን የሚገባው ነገረ ሰንደቅ ዓላማ ነው። ያን በፈቀዱ ዕለት ሚስጢረ ኢትዮጵያ ታምር ትሠራለች። ዊዝደም ይገሰግሳል።
ድርድር።
ድርድር የፖለቲካ ማኒፌስቶ አካል ነው። ግን ድርድሩ ?
1) በቂ ዕውቅና ሊኖር ይገባል። ጠቅላይ ሚር አብይ የገና ጨዋታ አድርገውታል። ይህ የተገባ አይደለም። ፋኖሻ የአማራ ልጅ ነው። የአማራን ህዝብ አክብረው ሊነሱ ይገባል። በጦርነቱ ጊዜ እኩል ተጎድተው የዲፕሎማሲውን ማህበረሰብ ነጥለው ትግራይ እንዲሄዱ ዕውቅና ይሰጡ ነበር። አሁንም ለሌሎች የሰጡትን ዕውቅና ለመስጠት ይሸፍጣሉ። ለአሉበት ሥልጣን እኮ አማሬዬ ነው የሰጣቸው። ዕድሉ እያለው።
2) ትርፍ እላፊ መሄድ አያስፈልግም። የታረመ አንደበት ይጠይቃል።
3) ፋኖሻ ጦርነት የባጀበት ስለሆነ ጊዜው ቸኩሏል። መሪወችም ጊዜ ያስፈልጋቸዋል።
4) አክብሮ መነሳት ይገባል።
5) ግራ ቀኙ ትሁት ሊሆኑ ይገባል።
6) ግራ ቀኙ አንዱ ሌላውን ሊያቃልል፤ ሊዘልፍ አይገባም።
7) ግራ ቀኙም ውሳኔ ከመስጠት በፊት ህዝብን በተናጠል፤ አላህን // እግዚአብሄርን ማማከር ይገባል። የበሰለ ጥሞና ማድረግ ይገባል። የአርምሞ ጊዜ።።
6) ደረጃውን የጠበቀ ጥያቄ እና የአፈፃፀም ሥርዓት ሊነደፍ ይገባል።
7) ሁነኛ ዋስትና ሰጪ አካል ያስፈልጋል። አገርም። እንደ እኔ ዕይታ ሲዊዲን የአማራን አጀንዳ የተቀበለ ዕንቁ አገር ስልሆነ አደራዳሪ አገር ቢሆን ትርፍ ይኖረዋል።
7) ሁለቱም እልህ፤ ብስጭትን አስታግሰው በግራ ቀኝ እንደ ባቄላ ሹቅ ወይንም እንደ ድፎ በላይም በሥርም ለሚንገበገብ ህዝብ ማስተዋል የሚመራው የመፍቴ ጎዳና ሊከተሉ ይገባል።
 ማቃለል፦ ማጣጣል፤ ቅጥል ሥም ማውጣት አይገባም። እንደ ነውርም ሊታይ ይገባል።
ውዶቼ
ውቦቼ
ደህና እደሩ። አሜን። ነገን በጉጉት እንጠብቃት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
03/06/2024
አማራነት ይከበር!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።