ልጥፎች
የኢትዮጵያ ፖለቲካ መለያ ባህሬ #ስስታምነት ብቻ አይደለም #ቆንቋነትም።።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የኢትዮጵያ ፖለቲካ መለያ ባህሬ #ስስታምነት ብቻ አይደለም #ቆንቋነትም። ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሶሻሊዝምን ርዕዮት መከተል ከጀመረበት ጀምሮ ስስታም የሆነ ይመስለኛል። ባለፈም ቆንቋነነት። ከስስታምነት ያለፈ #ስግብግብነት ። ተዳብለህ በተወሰነ ደረጃ ህሊናህ የሚልህን አድምጥ እንኳን አይፈቀደም። #ልጠቅልልህ ፤ #ልሰልቅጥህ የተሰጠህ ህሊና በእኔ ቁመና ከሆነ ይሁን በስተቀር ቆልፈህ ተቀመጥ። የአንተ ህሊና በእኔ ህሊና ይመራ ነው መከራው። ይህ የሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በሽታ ሲሆን ወታደሮች ደግሞ ደጋፊወች ናቸው። አይታወቃቸውም እንጂ ሳይለንት ዲስክርምኔሽንም ነው። በራሱ ህሊና ሊመራ የወሰነ፤ አለኝ የሚለው የራሱ የሆነ ነገር ያለው ባይፈጠር ይሻላል። ተረባርበው ድራሹን ያጠፋታል። ይህ ስልጣን ላይ ሆነ ስልጣን ላይ አልሆነ የሁሉ ድዌ ነው። #ወረርሽኝ ። አሻም ያሉ እንደ እኔ አፈንጋጮች ህሊናቸውን ያላከራዩ ወይንም ያልገበሩ በውራጅ ማንነት ፋንታዚ ያለቀዘፋ ወይንም የማይቀዝፋ በስውር እስከ ቤተሰባቸው ይመነጠራሉ። ከእስር ሳንፈታ እናልፋለንም። እስሩ ቤት ለቤት ስለሆነ ብቻችን እንዳአዝን ይሆናል እምናልፈው። በዚህ መሰል ህይወት ለመጣው ለሄደው ያላደገደጉ የእኔ መሰል መከረኞች አሉ። ትልቁ ፀጋቸው ግን በነፃነታችው ልክ መኖርን ፈቅደው ማሸነፋቸው ነው ሳይገብሩ። ስለዚህም ኢትዮጵያ ጥሪ ይዘው ከሚወለዱ ልጆቿ በረከት #እዬተነፈጋት አሁን ካለችበት ደርሳለች። በጥንት ዘመን በ13ኛው መቶ ክ/ ዘመን ጎንደር ያደገው በሊሂቃኑ፤ በሊቃናቱ የመጠቀም ደንበር የለሽ መብት ስለነበረ ነው። እኔ ሳድግም የጎንደር ትውፊቱ ብልህ ሰው ከተገኜ ወደ እትብቱ ወደ ተፈጠረበት እንዳይሄድ #በጋብቻ ይያዛል። የጎንደር ስልጣኔ ሁለገብነቱ...
ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ናት። ተስፋዋም መርቆ የፈጠራት አምላኳ ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ናት። ተስፋዋም መርቆ የፈጠራት አምላኳ ነው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የፖለቲካ ሊቃውንታት ይሰጋሉ። ስጋት ለምን ተፈጠረ ልል አልችልም። ገፊ ምክንያቶች አሉና። ተጨባጭ የአመክንዮ ምልክቶችም አሉና። ኢትዮጵያን አብዝተው ከሚቀናቀኗት፤ ከሚቀኑባት፤ ሊበቀሏት ከሚሹ እጆች በማህበረ ኦነግ ሥር ስለወደቀችም። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ከመሆኗም በላይ የተበጀችበት መሠረታዊ አመክንዮ #ዊዝደማዊ ስለሆነ ኢትዮጵያ ተስፋዋ ተንጠፍጥፎ ፍስስ የምትል አገር አድርጎ ማዬቱ መብት ቢሆንም ግን እኔ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ እኮ ደርግ እና ህወሃት ሻብያም ታክሎ በኃይል ርክክብ ሲያደርጉ ብዙው በዕት የመንግሥት አስተዳደር አልነበረውም። ያ የሆነበት ምክንያት እኔ እንደምረዳው የተሠራችበት #የዊዝደም ቅመም ንጥር ጠንካራ በመሆኑ ነው። በኋላም እንዳትቀጥል ተደርጎ በተሠራው ህወሃት ሠራሽ የዞግ ክልል ውስጥ እራሷን ማስቀጠሏ እኮ የጥበቦች ጥበብ #ልቅና ነው። ይህም ሆኖ መላ የአፍሪካ አገራት፤ መላ ቡኒ ዕንቁ ሁሉ ይመኩባታል። ይጽናኑባታል። ተስፋ ያደርጉባታል። ሙሉ ስድስት ዓመት እንደ ነሃሴ ዶፍ ደም ሰርክ እዬፈሰሰም አፍሪካውያን ኢትዮጵያ #መራሂት እንድትሆን ይመኛሉ። በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የአደባባይ ሹመት አፍሪካውያን ያስተላለፋት መልዕክት እኮ መጸሐፍ ይወጣዋል። አፍሪካውያን ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ተስፋ የላስታ አለት ዓይነት ነው። ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን እንደ #ኃይማኖታቸው እንደሚዮዋት ነው እኔ እማስበው። ኢትዮጵንይዝም እኮ መቼውንም ቢሆን ሊፈቀፈቅ የማይችል ኮከብ #አስተምህሮ ነው። ፋና "ከሲንጋፖር ምን እንማራለን" የሚል መሰናዶውን የኢትዮጵያን ሥም በአረንጓዴ ቢጫ ቀ...
ሞገድ ጋዜጣ እና ሄሮድስ አብይ አህመድ?
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ሞገድ ጋዜጣ እና ሄሮድስ አብይ አህመድ? ( ዶር፣ ጠቅላይ ሚር፣ ፕሬዚዳንት፣ የጦር ኃይሎች አዛዥ።) ይህን ጭብጥ ለ7ኛ ጊዜ መፃፌ ነው። ሁልጊዜ ሞት አዲስ እንደ ሆነው ሁሉ የሄሮድስ ትራጀዲ አዲስ ለሚሆንባቸው። እነ አቶ ጣሂር፣ እነ አቶ ዬሱፍ በዕምነታቸው ስስ እጅግ ስስ ስለሆኑ የጎንደሩንትራጀዲ አጀንዳቸው አድርገውታል። የስልጤው ግን አጀንዳቸው አይሆንም። ሞገድ የሚባለው ልብ ወለድ ጋዜጣ ምን ያሳካል? ሞገድ ስኬቱ #ሽብር ነው። ሽብር ያደራጃል። ሲያደራጅ 2 ማሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሊፈጅበት ይችላል።ሲያሳካ ግን 8 ሚሊዮን ዶላር ይሆናል። የአርቲስት ሃጫሉ ህልፈት እና ፕሮጀክቱን እዩት። ሙሉ ኦሮምያን፣ ሙሉ አዲስ አበባን ምን ያህል በአንድ የስጋት ጉርና እንደገፋው። ዛሬ የሚያነሳው የለም አርቲስቱን። አርቲስቱ የተገደለበት ምክንያት ወዘተረፈ ነው። እናም ተሳክቷል። ሞገድ አንድ ታዋቂ ሙዚዬም ያወድማል። ውድመቱ ከዜናው ጋር እኩል ይወጣል። በ2 ሚሊዮን በጀት የተጠናቀቀው ሽብር ጋዜጣው ሲሸጥ 8 ሚሊዮን ይሆናል። በዛ ላይዕውቅናው። አያችሁ አይደል ዘንድሩ በግራጫማ ጉዞ ከ100 ተፅዕኖ ፈጣሪወች አንዱ እንደሆኑ ሞገዳዊው የሽብር ካፒቴን። የሄሮድስ አብይ አህመድ የአመራር ዘመን እንዲህ ነው። አሁን የሚቀር ያለ አይምሰላችሁ። ሲነሪት፣ ዕውቅና ያለው፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሁሉም ተረኛ ነው። መታሰር ሽልማት ነው። ምነው እነ ቲም አንባቸው በታሰሩ። የሳቸው ፕሮጀክት ጥልቅ ነው። አስር አለቃ መሳፍንት። አማራ ነው። በምን ቀመር ከጄኒራል ሳህረ መኮነን ጋር በጠባቂነት ይመደባል። እሳቸው እስከዚህ በጥልቀት ነው የሚሄዱት። አማራ አንድ የተጋሩ ቀደምት ከፍተኛ መኮነን ያውም በርዕሰ መዲናዋ በአዲስ አበባ ገደለው። ትልቅ ግሎባል ዜና ነበር። የጎረቤት አገሮች ጦር እንላክል...
Qualifizierte Leiterschaft ist der abstrakte Heilige Geist.
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
• Qualifizierte Leiterschaft ist der abstrakte Heilige Geist. Wo fange ich an? • Die Führung ist ein Beruf. • Die Führung ist ein Segen. • Die Führung ist auch ein himmlisches Geschenk. • Die Führung ist eine Begabung. • Die Führung ist Weisheit. Wo fange ich an? • Einführung. Heute möchte ich meine Gefühle zum Thema Führung zum Ausdruck bringen. Einfluss zu haben bedeutet nicht, ein Anführer zu sein. Man kann nur beeinflusst werden, indem man unbekleidet herumläuft. Ich denke besonders für das Management; Es reicht nicht aus, nur für Kunst oder irgendetwas anderes berühmt zu sein, um ein Land verantwortlich zu führen. Es ist meine Meinung. • Also, meiner Meinung nach … Eine Führung ist eine Weisheit. Eine Führung ist tief. Eine Führung ist Urteilsvermögen. Eine Führung ist ein Versagen des politischen Wissens. Eine Verwaltung ist Stabilität. Bei einer Verwaltung geht es nicht um Frustration. Eine Führung ist wie Mutterschaft zu sein. Die Führung bede...
#አብረን እንፈር።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#አብረን እንፈር። ለካንስ ደካማ መንግሥት እንዲህም ይናፍቃል። እሱንም ነው ያጣነው እኮ። እንደዚህ ዓይነት ብትክ የሆነ በጭካኔ የተከዘነ ዘመን ኢትዮጵያ ገጥሟት አያውቅም። የሚከሱበትን ምክንያት እንኳን አያውቁትም። እሁድ ዕለት ያን ሁሉ ትርዒት አይታችሁ በህሊና ጭብጥ ስትመጡ ብትክ። እብቅ ነገር። ደጋግመው የኔታ ጎዳና ያዕቆብ የሚሉት ነገር ነበር "ቢያንስ ስህተቱን አስተካክላችሁ ተሳሳቱት።" አሁን አንድ ጊዜ በአማራ ክልል ሚዲያ ለዛውም ተቆራርጦ ከቀረበው ውጪ የት ቦታ፣ በምን አግባብ ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ዩቱብ፣ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ያውቃል? ልክ እንደ ንግሥት ኤልሳቤጥ ቃለምልልስ ደፍሮ አያውቅም። ብዕሩ ብቻ ነው እምትናገረው። ብዕሩ ብቻ ነው እምትሞግተው። ዓይን አፋርም ነው። ቁጥብ ነው። የሚፅፈው ለራሱ ለኦዳገዳ የሚጠቅም ነው። አቅም አልገናኝ አለ እንጂ። የሆነ ሆኖ አብረን እንፈር ስል እኛ ምን በወጣን ልትሉ ትችላላችሁ ይህን ያህል መታበይ በባዶ መስክ የመጣው እኛ በገፍ በሰጠነው አቅም ነው። እኔ ኦህዴድ፣ ደህዴን፣ ብአዴን የሚባሉ ድርጅቶች መፈጠራቸው ትዝ ብሎኝ አያውቅም ነበር። ያው ሱሴ ሱስ አድርጎ ኩም አደረገን እንጂ። ከሳሽ ሆነህ በማታውቀው ነገር ከሰህ መንጨባረቅ? ሎቱ ስብኃት። ዬጃራን ኦነግ መንገዴን እንዳይደናቀፍ ሰግቻለሁ የአባት ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 07/06/2022
#መለስተኛ ጆኖሳይድ በኮሮጆ መሸቀጥ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#መለስተኛ ጆኖሳይድ በኮሮጆ መሸቀጥ። "ልብ ያለውሸብ።" ብልህ ሁን አማራ! ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) አማራ ክልል የቅማንት፣ የአርጎባ፣ የከሚሴ፣ የኦሮሞ፣ የአገው የሚባሉ የዞን፣ የወረዳ ደረጃ ያላቸው የውክልና ጣቢያወች አሉ። ይህ በዬትኛውም ክልል የማይደፈር አመክንዮ ነው። ሌላው ቀርቶ እማከብራቸው አቶ ሙስጠፌ ኡመር ክልሉን ህብራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል የፖለቲካ ዕድምታ ነበራቸው። በሸኜነው ሳምንት መጨረሻ ከዋልታ ቴሌቪዥን ከጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈርስ ጋር በነበራቸው የሁለት ክፍል ቆይታ የፖለቲካው ውክልና ህብራዊነት ተስፋው ልሙጥነቱን ነግረውናል። ዕሳቤው በሳቸው ህሊና ብቻ እንደ ተሰነቀ አርድተውናል። መኖር ቢፈቀድም የፖለቲካ ውክልና ሰማይ ቤት ስለመሆኑ "መጫን" የሚል ስጋት እንዳለ ገልፀዋል። ሌላው ከሳቸው የገረመኝ የሚመሩበት የኦዳገዳ ፍልስፍናም "መደመር" ያልገባቸው መሆኑን ነው። የሚጨበጥ ነገር አላገኜሁበትም። ከገመትኩት በታች ነው የሆነብኝ ግንዛቤያቸው። ወደ ቀደመው ስመለስ የውክልና ጉዳይ ከዚህ ተነስታችሁ አብዛኛው አማራ የሚኖርባት አዲስ አበባ እና የአማራ ክልል ደግሞ ያሻው ሁሉ ይቀራመተዋል። ይህ ከግፍም በላይ ነው። የፖለቲካ ድል ድምፅ ነው። ሙሉ ኦሮምያ፣ ሙሉ አፋር፣ ሙሉ ሱማሌ፣ ሙሉ ሐረሬ፣ ሙሉ ሲዳማ፣ ሙሉ ደቡብ፣ ድሬ፣ ሙሉ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ሙሉ ጋንቤላ ለምርጫ በተከለሉ ቦታወች ሁሉ ሰፊው አማራ ይኖራል ግንውክልና የለውም። ዕድሉ ካገኜ ገዳ 5 ዓመት አማራን ያጭዳል...