ሞገድ ጋዜጣ እና ሄሮድስ አብይ አህመድ?
ሞገድ ጋዜጣ እና ሄሮድስ አብይ አህመድ?
( ዶር፣ ጠቅላይ ሚር፣ ፕሬዚዳንት፣ የጦር ኃይሎች አዛዥ።)
ይህን ጭብጥ ለ7ኛ ጊዜ መፃፌ ነው። ሁልጊዜ ሞት አዲስ እንደ ሆነው ሁሉ የሄሮድስ ትራጀዲ አዲስ ለሚሆንባቸው። እነ አቶ ጣሂር፣ እነ አቶ ዬሱፍ በዕምነታቸው ስስ እጅግ ስስ ስለሆኑ የጎንደሩንትራጀዲ አጀንዳቸው አድርገውታል። የስልጤው ግን አጀንዳቸው አይሆንም።
ሞገድ የሚባለው ልብ ወለድ ጋዜጣ ምን ያሳካል?
ሞገድ ስኬቱ #ሽብር ነው። ሽብር ያደራጃል። ሲያደራጅ 2 ማሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሊፈጅበት ይችላል።ሲያሳካ ግን 8 ሚሊዮን ዶላር ይሆናል።
የአርቲስት ሃጫሉ ህልፈት እና ፕሮጀክቱን እዩት። ሙሉ ኦሮምያን፣ ሙሉ አዲስ አበባን ምን ያህል በአንድ የስጋት ጉርና እንደገፋው። ዛሬ የሚያነሳው የለም አርቲስቱን። አርቲስቱ የተገደለበት ምክንያት ወዘተረፈ ነው። እናም ተሳክቷል።
ሞገድ አንድ ታዋቂ ሙዚዬም ያወድማል። ውድመቱ ከዜናው ጋር እኩል ይወጣል። በ2 ሚሊዮን በጀት የተጠናቀቀው ሽብር ጋዜጣው ሲሸጥ 8 ሚሊዮን ይሆናል። በዛ ላይዕውቅናው። አያችሁ አይደል ዘንድሩ በግራጫማ ጉዞ ከ100 ተፅዕኖ ፈጣሪወች አንዱ እንደሆኑ ሞገዳዊው የሽብር ካፒቴን።
የሄሮድስ አብይ አህመድ የአመራር ዘመን እንዲህ ነው። አሁን የሚቀር ያለ አይምሰላችሁ። ሲነሪት፣ ዕውቅና ያለው፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሁሉም ተረኛ ነው። መታሰር ሽልማት ነው።
ምነው እነ ቲም አንባቸው በታሰሩ። የሳቸው ፕሮጀክት ጥልቅ ነው። አስር አለቃ መሳፍንት። አማራ ነው። በምን ቀመር ከጄኒራል ሳህረ መኮነን ጋር በጠባቂነት ይመደባል።
እሳቸው እስከዚህ በጥልቀት ነው የሚሄዱት። አማራ አንድ የተጋሩ ቀደምት ከፍተኛ መኮነን ያውም በርዕሰ መዲናዋ በአዲስ አበባ ገደለው። ትልቅ ግሎባል ዜና ነበር። የጎረቤት አገሮች ጦር እንላክልህ እስከማለት ደርሰዋል።
ስለገደለውም አማራ መቀጣጫ ይሆናል። በበቀል ይቀጠቀጣል። ቀጥቅጠው አካለ ጎደሎ አድርገውታልም። አካለ ጎደሎ ብቻ ሳይሆን በሞት ሊቀጥቱ ወስነው በዕድሜ ልክ ሆኖለታል። የዛን ጊዜውን ወጀብ እሰቡት።
እሳቸው ሌላ ትራጀዲያቸውን ፀጥ ብለው ይሰራሉ። እኛ በዛ ወጀብ ውስጥ ሆነን ድንጋጤ ሲያርደን እሳቸው ቤተመንግሥታቸው ሆነው ይስቁብናል።
ገና መቶ ቀኑ ሳይታሰብ እሳቸው የሰኔ16/2010 ትራጀዲ አዘጋጅተዋል። የአማራ ልዑካንን አሜሪካ ሲልኩ የሰኔ 15/2011 ትራጀዲ አዘጋጅተው ነው።
የሚገርመው ቀንድ ቀርቶ ጅራት መሆን አለመቻላችን ነው። በዬትራጀዲው የማይታወቁ ሰወች ያልፋሉ። ለቤተሰቦቻቸው ግን ቀድሞ ሊከፍልላቸው ይችላል።
አቶ ሴኩተሪ ሞቱ ተባሉ። የማን ነበሩ? መልስ ያለው ሰው የለም። ስሜን ዕዝ መኮንኖች አመራወች አለቁ ስንት ናቸው? ስማቸው ማን ይባላል? ቤተሰብ አላቸው ወይ? የሚያውቅ ሰው የለም።
ሌላው ቀርቶ የዶር አንባቸው መኮንን እናት በሞቱ በማግሥቱ፣ የአቶ ምግባሩ ከበደ አባት አለፋ፣ በማግስቱ የአቶ ምግባሩ እናት አለፋ። የሌሎች የአማራ ሊቃናትም እናት አልፈዋል። ለምን? እንዴት? ጠያቂ የለም።
ወጣት አስምራ ሹምዬን ለቀቋት። ቃለምልልስ ሰጠች ከዛ በኋላ ስለ እሷም ስለቤተሰቧም ውሹ የለም። ከታፈኑት ልጆች ጋር ይጨምሯት፣ በትውስት ሌላ አገር ይላኳት፣ ታማ ሆስፒታል ትሁን፣ ወይ ያጥፏት ጠያቂ የለም። ከዛ በኋላ ሂደቱን አንከታተለውም።
እንዳንከታተለው ሰምተናቸው የማናውቅ ትራጀዲወች ይመጣሉ። ለሺህ ዘመናት የቆዬው ጎንደሬ በሮመዳን ሰለባ ሆነ፣ አሁን ትናንት ሰው ተቃጥሎ ማክሰኝት አሮ ሞተ። ሁለቱም አይበገሬውን ጎንደር ማስበርገጊያ ነው።
የአባይ ግድብ ታሪክን እንደምን መዳፋቸው ውስጥ እንዳስገቡት እዩት። መምህራን ሰብስበው ፕሮጀክቱን ሲያጣጥሉት የገባው አልነበረም። የኢንጂነር ስመኜው ሰማዕትነት ሁነትም ጥረታቸው ቢያሳዝንም እንዲህ የታሪክ ዘረፋ ይሆናል ብሎ ያሰበ አልነበረም።
ግብፅ፣ ራሺያ ሄደው የበጠበጡትም። አልገባነም። በኢትዮጵያዊነት ሥም ግድቡ የእኔ ነው ሎጎ እኔ ታግዬ መብታችን አሰጠብቅኩ የኦሮሙማ ዓይነታ የተግባር ማሳ ሆነ።
ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ በዛ ሁኔታ ማለፍ እና ዛሬ የአማራ ሁኔታን ተመልከት። ሲገባ አገር ዕውቅና አልተሰጠውም። ሲያልፍም ዕውቅና አልነበረውም።
የኖሞር ጋዜጠኛ ሄርምላ አረጋዊ ባለቤት ምን ያህል እንደ ከበረች ተመልከት። በነገራችን ላይ ወጥ አማራ ብትሆን ይህን ያህል ክብር አይኖራትም ነበር። ጋዜጠኛደምስ በለጠ ኤርትራ ድረስ ሄዶ የታገለ ነበር።
ከላይ እስከታች የሚመሩ የሽብር ፕሮጀክቶች መሪያቸው አንድ ነው። አስተዳዳሪያቸው አንድ ነው። ፕሮጀክተሩ አንድ ነው። ስኬቱም ሥልጣን ማስጠበቅ ነው።
የሞገድ ጋዜጣን ብታነቡት ሚስጢሩ ይገባችኋል። የህፃን ንገረው አዲስ የተረሸነው ታቅዶ የተከወነ ሽብር ነው። ለምን? የአማራ ልጆችን ልበ ሙልነት ቅስም መስበር የፕሮጀክቱ ክፍለ አካል ነውና። በጭልፋ፣ በቅርንጫፍ አትዩት። የፖለቲካ ሥልጣን ላይ የአማራ ልጅ የሚገለልበትም በዚህ ነው።
አንድ ሊቅ ወጥተው ነበር። ዶር ደረጀ ዘለቀ። ሳንጠግባቸው አሁን የሉም። በህይወት ሊኖሩ ይችላሉ። ግን የሆነውን ነገር አናውቀውም። የራሳቸው አጃቢ ከባህርዳሩ ትራጀዲ በኋላ አልታዬም።
በማስተዋል፣ በእርጋታ፣ አርቆ በማሰብ ከስሜታዊነት የዘለለ ወጥ የፖለቲካ አቅም ይጠይቃል። ይህ ደግሞ የለንም። በዕለታዊ ኩነት ስንዳክር መሽቶ ይነጋል። በፋክክር እንደ ጎረምሳ ትልልቅ ፖለቲከኞች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲወጡ ሲወርዱ አያለሁኝ።
እዩት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን። አለን? በምን ሁኔታ ይገኛል? እምናውቀው ነገር የለም። ጥሞናውን ብወድለትም።
ምን እናድርግ?
1) ቁጥር አንድ አሳቻውን መሪ መረዳት ነው።
2) ቁጥር ሁለት የአክሽኖችን ተዛማጅ ሁነቶችን ማጥናት ነው።
3) ቁጥር ሦስት እራስን በዲስፕሊን ለማስገዛት መጣር።
4) ቁጥር አራት ዘመኑን ማጥናት።
5) ቁጥር አምስት የሚመጥን አቅም መፍጠር ነው። ሰክኖ።
ይህ ውድድር፣ ፋክክር፣ መልስ መሰጣጣት ለኮበሌ ፖለቲከኛ ነው የሚሆነው። አዛውንት መሆን ባይቻልም ቢያንስ ጎልማሳ ፖለቲከኛ ለመሆን ይሞከር።
አንድ የነጠረ ዕውነት ኢትዮጵያን እንደ ተፎካካሪ ነው የሚዮዋት። ባትኖር ምርጫቸው ነው። አቂመዋታል። ከእሳቸው ዝቅ እንድትል ይሻሉ። በካርታም ብትሰረዝላቸው ደስታውን አይችሉትም። ለዚህ ነው ሙልጭልጭ፣ ዝልግልግ የሆነው ነገረ አለሙ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/06/2022
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ