እራስን ለማሸነፍ፦ እራስን #ማድመጥ ይገባል። አብሶ #ለመሪነት።

 

እራስን ለማሸነፍ፦ እራስን #ማድመጥ ይገባል። አብሶ #ለመሪነት
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 2 people, people smiling, body of water and text that says 'የህላችን የታዝቱእህቶቻችንባለትኳይይ!!! የታገቱ እህቶቻችን ባስቸኳይ ይፈቱ!!! Bring Back Our Students!!!'
አቨው #የጥሞና#የአርምሞ ጊዜ አላቸው። #ኢትዮጵያም #የአርምሞ እና #የተደሞ ውጤት ናት። ከእኛ የቀደሙት ይህ የስክነት ሂደት ምርጫቸው ነበር። ዛሬስ? #መጋለብ ነው። ጠቅላይ ሚር አብይ ሥልጣኑን ሲያገኙ ወዲያውኑ ነበር #የ100 ቀን ፕላን አውጥተው አህዱ ያሉት። እሳቸው ብቻ አይደሉም። ሌላውም እንዲሁ። ተፎካካሪ፦ ተቀናቃኝ፤ ተጠማኝ፤ ተቃዋሚውም እንዲሁ።
ወደቀደመው ምልሰት ሲሆን የዶር አብይ ጥድፊያው አሜሪካን አውሮፓንም አካሏል። ውጤቱስ??? ጥናት ስላልሰራሁበት መዝኑት። ፐርሰንት በስማ በለው አይሰጥም። ያ ግምት እንጂ #ፋክት አይሆንም እና።
የሆነ ሆኖ #ጥሞና#አንክሮ#ተደሞ #ስንቅ እና #ትጥቋ #መኖሯም ለሆነች አገረ ኢትዮጵያ ካለ ተፈጥሯዋ #ግልቢያ ተመገቢ ተብላ እንሆ በህውከት ትናጣለች። በእኔ ዕድሜ አርምሞ/ ጥሞና// ተደሞ የወሰደ መሪ ሰምቼ አላውቅም። ለዚህም ነው "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል" የትውልዱም፤ የአደራም ጥሪት ሆኖ የሚታይ።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ፓን #አረቢክ ስለሆኑም ጥሞና፤ አርምሞ፤ ተደሞ የፈጠራቸውን ቅርሶች፤ ጥሪቶች፤ ማስታወሻወች፤ መልዕክተኞች በመንቀል የሚችላቸው አልተገኘም። በነቀላው ውስጥ ቀደም ብሎ ለዛ ዕንቁ ጥሪት የፈሰሰው ፀሎት፤ ደዋ፤ ጉልበት፤ ዕውቀት ተመክሮ ጉዳያቸው አይደለም። ሲያፈርሱ፤ ሲነቅሉ፤ #ሲቀዱ፦ ሲተረትሩ፦ ሲቦጫጭቁ የሚያማክሩት የለም። የሚያዋዩት የለም። በአንድ ሰው ያልተበጀት አገር፤ በአንድ ጀንበር ያልተሰራች አገር በአንድ #ኮበሌ ፈቃድ እንሆ ትታረሳለች። እርግማን ይመስለኛል። እሳቸውን የሚተቹ እጩ መሪወችም ተደሞ፤ አርምሞ ጥሞናን አይሞክሯትም። ነገ መሺ ሩጫ ነው። ታዲያ መዳህኒተ ዓለም ክርስቶስ አላህ እንደምን ይማለደን????
የሚገርመኝ አሻንጉሊት እንደተሰጠው ልጅ እሳቸውም ተከታዮቻቸው መፈንደቃቸው ነው። ግራሞቴ ይህ ብቻ አይደለም የክልል አስተዳዳሪወች ቤተ - አራት ኪሎ ሹማምንትገበርዲን እና ከረባት ተንቧለሉም የዝምብሎ ውክሎች በምረቃ ዕለት አጃቢነት ነው። ሳይማከሩ ለሚፈርሰውም ተተካ ለሚባለው ታድመው ዕውቅና ይሰጣሉ።
ሌላው ቀርቶ ዓለምን ያስደነቀው የዓድዋን #ድል ከህዝብ በዕልነት ነቅለው የግለሰብ ሥም የከንቱ ውዳሴ ፍራሽ ሲያደርጉት ብቻም ሳይሆን ዕፁብ ድንቁን ሥም #ዜሮ ብለው ሲሰይሙት የበረከት ያህል አጃቢወቻቸው ተቀበሏቸው። ደጋፊወቻቸውም በራሳቸው መደርመስ የሚደሰቱ ፍጡራን ናቸው። እንደምን ዓለም ዓቀፍ ድል ዓድዋ #ዜሮ ይባላል????
በዚህ ልክ አንበሳን ነቅለው ፒኮክ ሲተክሉም #ሃግ ያላቸው የለም። ወሸኔ¡ ማለፊያ¡ ተብለው ተውደሱ። የበቀሉ ሰብዕናዋችን አስተንፍሰው፤ አሟሽሸው ኩርምትምት አድርገው እሳቸው ብቻ ዘለግ ብለው ይታያሉ። በመባቻው ሰሞናት ኮነሬል ጎሹ ወልዴ፤ አንባሳደር ካሳ ከበደ፤ አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ ዶር ምህረት ደበበ፦ ፕሮፌሰር ብርኃኑ ነጋ፤ አርቲስት ታማኝ በዬነ፤ ወዘተ በገዘፈ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ወዘተ ይታወቁ ነበር። ዛሬ እሳቸው ብቻ ነጋ ጠባ ሲመርቁ ሲያስመርቁ ይመሻል ይነጋል።
ለመሆኑ አቶ ኦባንግ ሜቶ የት ገባ???? ኮነሬል ጎሹወልዴስ????
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08/06/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።