#መለስተኛ ጆኖሳይድ በኮሮጆ መሸቀጥ።

 

#መለስተኛ ጆኖሳይድ በኮሮጆ መሸቀጥ።
"ልብ ያለውሸብ።" ብልህ ሁን አማራ!
ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
አማራ ክልል የቅማንት፣ የአርጎባ፣ የከሚሴ፣ የኦሮሞ፣ የአገው የሚባሉ የዞን፣ የወረዳ ደረጃ ያላቸው የውክልና ጣቢያወች አሉ። ይህ በዬትኛውም ክልል የማይደፈር አመክንዮ ነው።
ሌላው ቀርቶ እማከብራቸው አቶ ሙስጠፌ ኡመር ክልሉን ህብራዊ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲኖረው ለማድረግ የሚያስችል የፖለቲካ ዕድምታ ነበራቸው።
በሸኜነው ሳምንት መጨረሻ ከዋልታ ቴሌቪዥን ከጋዜጠኛ አቶ ሥሜነህ ባይፈርስ ጋር በነበራቸው የሁለት ክፍል ቆይታ የፖለቲካው ውክልና ህብራዊነት ተስፋው ልሙጥነቱን ነግረውናል።
ዕሳቤው በሳቸው ህሊና ብቻ እንደ ተሰነቀ አርድተውናል። መኖር ቢፈቀድም የፖለቲካ ውክልና ሰማይ ቤት ስለመሆኑ "መጫን" የሚል ስጋት እንዳለ ገልፀዋል። ሌላው ከሳቸው የገረመኝ የሚመሩበት የኦዳገዳ ፍልስፍናም "መደመር" ያልገባቸው መሆኑን ነው። የሚጨበጥ ነገር አላገኜሁበትም። ከገመትኩት በታች ነው የሆነብኝ ግንዛቤያቸው።
ወደ ቀደመው ስመለስ የውክልና ጉዳይ ከዚህ ተነስታችሁ አብዛኛው አማራ የሚኖርባት አዲስ አበባ እና የአማራ ክልል ደግሞ ያሻው ሁሉ ይቀራመተዋል። ይህ ከግፍም በላይ ነው።
የፖለቲካ ድል ድምፅ ነው። ሙሉ ኦሮምያ፣ ሙሉ አፋር፣ ሙሉ ሱማሌ፣ ሙሉ ሐረሬ፣ ሙሉ ሲዳማ፣ ሙሉ ደቡብ፣ ድሬ፣ ሙሉ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ሙሉ ጋንቤላ ለምርጫ በተከለሉ ቦታወች ሁሉ ሰፊው አማራ ይኖራል ግንውክልና የለውም። ዕድሉ ካገኜ ገዳ 5 ዓመት አማራን ያጭዳል ያሳጭዳል።
የአማራ ህዝብ ውክልና በሚያገኜው አማራ ክልል እና አዲስ አበባ ደግሞ እንደ ቅርጫ ሥጋ ሁሉም አለ።
#ይህ #መለስተኛ #ጆኖሳይድ ነው። ይህን አውቆ በመላ አማራ እና አዲስ አበባ በሚካሄደው ምርጫ ላይ አማራ ተሟሙቶ አቅሙን ለአቅሙ ብቻ መስጠት ግድ ይለዋል።
ቅድስት ተዋህዶ አንድም ሰው ስሌላት ነው ይህ ሁሉ ፍዳ የምታዬው። አማራም ቢያንስ በራሱ ክልል ጠብ ያለች አቅም እንዳትኖር ብርቱ እጅግ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል።
ለአጥቄወቹ ብጣቂ አደብ ሊኖረው አይገባም። ዴሞክራሲ መንትሶውን ኦሮምያ ሄደው ይሞክሩት። በቃ በቃ ነው። በቃ ድርጊት ላይ ሊውል ይገባል። ብልህነት ብልጥነት አሸንፎ ለድል ሊበቃ ይገባዋል። ይሉኝታ አያስፈልግም። ተቆራርጦ በቀረው ቦታ ቢያንስ አማራ ልጆቹን ብቻ ሊመርጥ ይገባል። ቀልዱ ሊቆም ይገባል።
ጉራጌ መሬት በለው አፋር፣ አፋር በለው ጅጅጋ፣ ጅጅጋ በለው ሲዳማ በራሱ በአማራ ክልል አርጎባ፣ ቅማንት፣ አገው፣ ከሚሴ ሁሉም ቦታ የሚመረጡት የብሔረሰቡ አባላት ብቻ ናቸው።
ቢያንስ በቀሪወቹ ቦታወች አብን መምረጥ ግዴታ ሊሆን ይገባል። ከዚህ ውጪ አማራ ሪዚስት የሚያደርግበት አቅም አይኖረውም። አማራ ክልልን አብን ሊረከብ ይገባል ከህብር ጋር። መዳን በእጅ ነው። እጅን ቆርጦ እጅ መለመን ሙት መሬትን መናፈቅ ነው።
ብልጦቹ ገዳኦዳ አቅማቸው በሙሉ ደቡብ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ ጋንቤላ፣ ቤንሻንጉል አፋር ላይ አይደለም። የበሬ ግንባር በሚያክለው በአማራ ክልል እንጂ። "ልብ ያለውሸብ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/06/2021
በቃን መጨበርበር።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።