ድብድቡ መቼ እንዴት ይቁም።
ድብድቡ መቼ እንዴት ይቁም። "አድርገህኛል እና አመሰግንኃለሁ።" ክወና ነው። ለምን ማፍራት ተስኖን #ፈሰስን ? #ቀዳዳችን ስለምን በረከተ? #ቦክሱስ መቼ ይቁም? #ክፋነት መቼ ይቀበር? በራስ ላይ መዝመት ከተቻለ ሁለንም ብትክ ጉዳዮች ቀብረን ወደ ቀደመው ዊዝደማችን ጉዞ መጀመር እንችላለን። ዊዝደማችን ለተፈጥሯችን ዕውቅና ሰጥቶ በሱ ውስጥ ለመኖር መፍቀድ ነው። ወጪ አይጠይቅም። ትልም አይጠይቅም። ከራስ ጋር መታረቅ ብቻ ቁልፋን የመፍትሄ ትልምን ያስረክበናል። ስህተት ውስጥ ትናንትም፤ ዛሬም ብቻ ሳይሆን ስህተትን ለማስቀጠል ትጋታችን ሊገታ ይገባዋል። ሁሉም በግድፈት ተነክሮ ነው የኖረው። በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም አለኝ የሚለው አቅም አለው። ለድክመቱ መሻሪያው የራስ ዳኝነት ነው። ለአቅሙ ደግሞ በውጭጭ አቅም ቅንነትን መግቦ አገርን፤ አደራን፤ ትውልድን ማዳን ይገባል። የታሠሩ #እስረኞች ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል። #ተኩስ #አቁም ሁሉም ሊያውጅ ይገባል። አቅምን ንቆ ከመነሳት ለአቅሙ ዕውቅና ሰጥቶ #በልኩ #ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። #እላፊ መሄድም አይገባም። ስድብ፤ ማዋረድ፤ ማቃለል ለምን??? መውደቃችን ከውስጥ መቀበል አለብን። በመውደቃችን ልናፍር ይገባል። የሚሠሩ መልካም ነገሮችንም ዕውቅና መስጠት ይገባል። ግን ምንም ዓይነት ሥልጣኔ ከሰው ልጅ ህይወት፤ የመኖር ዋስትና በላይ ሊታይ አይገባም። ፈጽሞ። በጣም ስጋት አለኝ። የአማራን ህዝብ #አቅሎ የማዬት ፖለቲካ። በፍጥነት ሊታረም ይገባል። የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና " የአማራ ህዝብ እገነጠላለሁ" ካለ ኢትዮጵያ #ባላ የሌለው ቤት ትሆናለች። የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካም ሙሉ በሙሉ ይቀዬራል። ብዙ ያልነገርኳችሁ ተሳትፎ አለኝ። ብቻዬን የሠራሁት። ...