ልጥፎች

ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ መሪነትን ይመትራል።

  ኢትዮጵያን ቁም ነገር የማድረግ ዓላማ መሪነትን ይመትራል። መሪ ለመሆን የፀና ተጋድሎ ይጠይቃል። በአንድ ምሽት መሪነት አይወለድም ይፀነሳል እንጂ። መሪነት በአጃቢ ብዛት ሳይሆን በሃሳብ ጥራት ፍሬ ነገር ይለካል። መሪነት ኢትዮጵያን ቁም ነገር ለማድረግ ከመቁረጥ ይነሳል። ከኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ጋር ፀበለ ፃዲቅ ጀምረህ ኢትዮጵያን ቁም ነገር ለማድረግ እራሱ ሃሳቡን ማሰብ አይቻልም። አገር ለውለታ አይሸጥም አይለወጥም። በአገር ጉዳይ ላይ መሪም ቢኮን እንደ እኔ እንደ ተርታዋ ዜጋ አንድ ድምፅ ብቻ ነው ያለው። ኢትዮጵያ አገራችን አይደለችም የሚሉ የመብትም የግዴታም ታዳሚ አይደሉም። አሁን ያለው የኦሮሙማ ሥርዕዎ መንግሥት ትንፋሹን ማስተካከል ያልቻለ ስለሆነ በአገር ውስጥም፣ በውጭም ባሉ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች መታቀብ አለበት። ኢትዮጵያን ለኤርትራ ጥገኛ ማድረጉን ጨምሮ። ኤርትራ የወትሮ አካላችን የዛሬ ጎረቤታችን ናት። ኢትዮጵውያን ቁርሾኛ አለመሆናችን ዓለም መስክሮታል። አገር መሆን ፈልገው አድርገውታል። ተከባብሮ መኖር ያባት ነው። ነገር ግን ሆድ ዕቃ እንዲሆኑ ማድረግ እና ማስደረግ ግን ውርዴት ነው። የሚታዩ ነገሮች ቸር ወሬ አይደሉም። አገር በራሷ ብቁ ልጆች እንጂ በሞፈር ዘመት ጉርድነት ልትመራ አይገባም። ይህ ሊስተካከል ይገባል። ዩፖለቲካ ድርጅትህ ስለሚፈልገው ብቻ ውስጥን አውልቆ መስጠት ለልዑላዊነት የተከፈለውን መስዋዕትነት አጥንት ከመቃብር አውጥቶ አንድዶ መሞቅ ነው። ይህ እኛን አይገልፅም። ይህ እኛን አያብራራም። ይህ እኛን አይተነትንም። ይህ እኛን አይተረጉምም። ይህ እኛን አያመሳጥርም ወደ እራሳችን እንመለስ። ቅኝ ተገዢነት አይናፍቀን። ለሉዕላዊነታችን ለተሰውት ጥቃት አውጪ እንሁን። መንፈሳቸው ይረግመናል። በእኛ ውስጥ እኛ እንኑር። በእኛ ...

ፖለቲካ ሰው ነው።

  ፖለቲካ ሰው ነው። ኦ! ይህ አባባሌ ፈላስፎችን እንዳያስቆጣ ሰጋሁ። ስጋት በልኩ ጥሩ ነው። ህግ ተላላፊነትን መመከት ስለሚችል። ማስማማትም ይቻላል። እንዲህ … ፖለቲካ ለሰው የተሠራ የአስተዳደር፣ የአመራር፣ የአደረጃጀት ሥርዓታዊ ሰበነክ ፍልስፍና ነው። እርግጥ ነው ሰው እና ተፈጥሮ በሚያገናኛቸው ጉዳዮችም አስተናባሪ ጥሩ ሊጋባ ነው ፖለቲካ። የሆነ ሆኖ ማዕከሉ ሰው ነው። ፖለቲካውን ሳይረዱ ዘው የሚሉ ነፍሶች ግን ያሳዝኑኛል። የቀጠሮ ስለሆኑ። ለምን ብትሉ ማህል ቤት ተቋርጠው ስለሚቀሩ። ሲገቡ ሜዳው አይበቃቸውም ያዙኝ ልቀቁኝ ነው። ሲወጡ ደግሞ ድብዛቸው አይገኝም። እግር ጣላቸው እግር ሸኛቸው። የሚገርመው ከባህር የወጣ አሳ ስለሚሆን ብቅ ጥልቅ እያሉ ማተራመስም ይኖራል። እንደ ወራጅ ወንዝ አይቶ መተው ነው። ፖለቲካ በቃህኝ የምትለው አይደለም። በእያንዳንዱ የህይወት መሥመር እንደ ሃሳብ አብሮ ይኖራል። ልዩነቱ በነቃ ህሊናዊ ወይንም ባልነቃ ህሊናዊ ክፍል መወራኜቱ ብቻ ነው። ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ስለ ዘዌዎች ችግሩ ያለው በሚቆዩበት ወቅት የሚያተራምሱት፣ የሚያምሱት፣ ባልወለደ አንጀታቸው ሰቅስቀው የሚደፋት ሃቅ እና ለዛ መስሎት የሚማገደው፣ ኑሮው የሚታወከው፣ ሰላሙን የሚያጣው፣ አምኖ የሚቀቀለው ነፍስ ዕልፍነቱን እሰቡ እና እግር የጣለው ታጋይ ባሰኜው ሰዓት ሲሾልክ ባክኖ የሚቀረውን የትውልድ ዕጣ ፈንታ እሰቡት። ኪሳራው ታያችሁ? የሚደቀው የሰው ልጅ የመኖር ዕጣ ፈንታ ነው። ራዕይ ብለህ አቆላምጠው፣ ዓላማ ብለህ አሽበልብለው፣ ግብም ብለህ ቀሽረው ልማታዊም በለው፣ ማህበራዊ ፍትህ ማዕከሉ ሰው ነው። በሰው ውስጥ መኖር አለ። ፖለቲካ ሰውን ለማኖር አኗኗሪ ጥበብ ነው። ሰው ከሌለ ድርጅት የለም። መንግሥት ህንፃ አይደለም። የሰዎች የተማከለ የአመራር ...

ህም። ልክን አለማወቅ ያቅለሸልሻል - በጣም።

  ህም። ልክን አለማወቅ ያቅለሸልሻል - በጣም።   የዛሬ አራት ዓመት ዬተፃፈ ነው። አገር ምድሩ ተደማሪ ሳለ። ያን ጊዜ አማራ ተደራጄ ኡኡታ ነበር። እንኳንስ ራሱን መከላከል የሚያስችል ኃይል ማደራጀት። አይታሰብ ነበር። አቶ ውብሸት ገርሟቸው ፁሁፍን አጋሪው አሉኝ። እኔም ይህን ያህል ይመስጣል ብዬ አላሰብኩም። ሳነበው ግን ተገረምኩኝ። 24/06/024 ……?እንሆ   ሠራዊት ወታደራዊ ከሆነ ከአዛዡ ትዕዛዝ ውትልፍ የለም። እና ሲቢሉ ምን ልሁን ብሎ ይሆን ዓይንህ አፍህ ላይ ነው ያለ ሲባል የሚቀበለው?   አገር የፈታው ነገር፣ አቅም ዋጮው ጉዳይ ሁሉም ለማልያ ፍቅር በሚካሄድ ቡጢ መሽቶ ይነጋል፣ ነግቶ ይመሻል። ተቋማዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ሲገባ በግለሰብ ዝና እና ወርቀዘቦ ሌት ተቀን መታመስ።   አንድ ሰው ስለራሱ ሲፅፍ የፈለገውን ይፃፍ። መሪዬ ይበል፣ ዓይኔ ይበል፣ ምርኩዜ ይበል ወዘተረፈ። " መሪያችን " ብሎ ፕሮፖጋንዲስት መሆን አይችልም። መሪ አለን የማንል ሰዎች እንዳለን ማወቅ ይገባል። በተጨማሪም ለእሱ መሪ የሆነው ነፍስ ለሌላው ላይሆን ይችላል። መሪ አለን የሚሉትም ቢሆኑ የራሳቸው ምርጫ ሊጠበቅላቸው ይገባል። በሌላው ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር የሚሹ ነፍሶች ዝልብ ሰብዕና ጎርፍ ይሆንብኛል። እንደዚህ ያሉ የሰውን ልክ የማያውቁ መብት ዳጭ አለሎ ሰብዕናዎች ስለሚያቅለሸልሹኝ በበዛ ሁኔታ ታግሼ መልዕክቴ ካልገባቸው ማሰናበት ተፈጥሯዊ መብቴ ነው መሪነት ገብያ ተሂዶ የሚሸመት ሸቀጥ አይደለም። መሪነት አይሸጥም አይለወጥም። መሪነት ስክነት - ፀጋ - ቅብዐ - ልቅና - ልዕልና - ጥበብ - ክህሎት - መሆን - ኪዳን - መታመን - ዝቅ ማለት - ተመክሮ - በችግር መገኜት ተጠያቂነትን ፈቅዶ መውሰድ - ርህርህና - ፍ...

#አዲስ #አበቤወች።

ምስል
  #ሙሉ 5 #ዕድሜያቸው #በግፍ #የተዘረፈ #አዲስ #አበቤወች ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ወደ ሥልጣን እንደመጡ ንቅል ብሎ የደገፈው አዲስ አበቤ እንጂ ኦሮምያ አልነበረም። ጉራጌ እንጂ አዲስ አበቤ አልነበረም። ደቡብ አዋሳ ላይ እንጂ ኦሮምያ አልነበረም። ድፍን አማራ ክልል እንጂ ኦሮምያ አልነበር። ለአመል አንቦ ላይ ጥቂት ነገር አይተናል። አካሉን የገበረ ግን አዲስ አበቤ ነበር። ዙሪያ ገባ የሚቀቀለውም #አማራ ።     ጳጉሜ መግቢያ ግንቦት 7 አገር ሲገባም፤ ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪወች ሲገቡ አዲስ አበቤ ለጋስ፤ ቅን እና ህብራዊ ስለሆነ #ፏ ብሎ ብሄራዊ ሰንደቁን ተጎናጽፎ ኢትዮጵያ በውስጡ መስጥሮ ሳይሆን ቀን ወጣልሽ ሳቂልኝ ብሎም እንግዶቹን አክብሮ አልቆ ተስፋ ሰንቆ ተቀበለ። እናቱን እምዬን ውስጡ አድርጎ።    ከዛ በተበታተነ ሁኔታ የነበረው ማህበረ ኦነግ በመስከረም አምስት 2011 ዓም ኢትዮጵያ ገባ። ኢትዮጵያን ድል አድርጎ የገባ ይመስል ነበር። ምድሪቱ በኦነግ የፖለቲካ ድርጅት ዓርማ #ተጥለቀለች ። መሬትን ለመርገጥ የተጠዬፋ የተንሳፈፋ ቄንጠኛ ፖለቲከኞችንም አስተውያለሁ። ዛሬ ስደት ላይ ናቸው አቶ በቀለ ገርባ። በውነቱ ከሩቅ ቦታም የመጡ ስለነበሩ አዲስ አበቤ በተለያዬ ሁኔታ #ቢዋከብም አክብሮ በፍቅር ተቀበለ።   አቀባበሉ በቡራዩ ንፁኃን የደም አላባ ነበር። በድምጽ የተመረጠ በድምጽ ሥልጣን የተሰጠው ኦህዴድ #ቡራዩ ላይ፤ ሻሸመኔ ላይ በኢትዮጵያ ታይቶ የማይታወቅ ይፋዊ ጭካኔ ፈፀመ። በተከታታይም ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ሰንበታ የሚኖሩ ነዋሪወች አራስ ቤቷ በላዮዋ እዬፈረሰ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀሉ። በርካታ ወገን ተፈናቀለ። ደቡብም ተመሳሳዩ ተፈፀመ። #ጭካኔ #ሽቅድድም ላይ ሆነ።...

ባለ #ቄንጠኛ ባለጎሏ ቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ እና ጀርመን በፋራንክፈርት አማይን የምድብ A ጨዋታቸውን በአቻ ነጥብ ከውነዋል።

ምስል
  ባለ #ቄንጠኛ ባለጎሏ ቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ እና ጀርመን በፋራንክፈርት አማይን የምድብ A ጨዋታቸውን በአቻ ነጥብ ከውነዋል። "የቤትህ ቅናት በላኝ"። የሲዊዚሻ ተጫዋቾች በራቸውን #ሳያስደፍሩ ሙሉ ዘጠና ደቂቃውን አንድ ለምንም መሩ። በባከነ ጊዜ በተጨመሩ ደቂቃወች ጀርመኖች አንድ ነጥብ በማስቆጠር #በአቻነት ወጥተዋል። ቲም ሲዊዝ #የመጀመሪያውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜም // #ሁለተኛውንም የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ ለምንም ጠንካራውን የጀርመን ቡድን #በአስደናቂ ብቃት #ተቋቁመው ቆይተዋል። ጀርመኖችን ያስደነገጠ አንድ ተጨማሪ ጎልም ተሰርዞ እንጂ ጎሏ ከመረብ ጋር ተዋህዳ ነበር በሲዊዝሻ በኩል። ሲዊዞች በአጭር ቅብብል፤ በቲም ወርክ ኮኦርድኔሽን ዘና ብለው ነበር የተጫወቱት። ጀርመኖች በጨዋታው መግቢያ ላይ ጎል ስለገባባቸው የመዛል ስሜት ታይቶባቸዋል። ይህ ደግሞ ልማዳቸው ነው። የመጨረሻዋም የመቅናት ያህል ነው እንጂ #ዝለው ነበር። እርግጥ ጎሏ ነፍስ ያላት ነበረች። አስደሳች አገባብ ነበር። ከአፍ እስከ ገደፋ ጢም ብሎ የሞላው የፍራንክፈርት አማይን ስቴዲዮም በጥቂት ደጋፊ የተደገፋት የሲዊዝ ቲም ያሳዩት #የአልበገርባይነት ተጋድሎ በህዝብ ቁጥሯ አናሳ ለሆነው እና #ለቀለም #ትምህርት #ቅድሚያ #ለምትሰጠው ሲዊዚሻ ይህ ታላቅ #በረከት ነው ማለት እችላለሁ። ሲዊዝ ውስጥ ያልተማረ አይገኝም። እያንዳንዱ ልጅ ተምሮ #ሙያ ሊኖረው ግድ ነው። ቅድሚያ ለቀለም ትምህርት። ቅድሚያ ለሙያ ሥልጠና በኽረ መርህ ነው። ታለንት እንደ አጀንዳ ብዙም አይታይም በስሱ ነው። ብዙወቹ ሄደው የሚወዳደሩት ጀርመን ነው። ሙዚቀኛ ሉካ ሄኒ፤ ሙዚቀኛ ፓትሪስ ኤንግል በጀርመን ተወዳድረው ነው አሸንፈው ከዕውቅ የሙዚቀኛ ሊስት ውስጥ የገቡት። ከዚህ በ...

ወድቆ መነሳት እንደ ጀርመን ተረክ ሚዛን Salon Terek

ምስል
ዘባስትያን እራሱ ትውልድ ነው። ዘገባህ ቢያወሳው ጥሩ ነበር። ጥሩ ትንተና ነው።