ህም። ልክን አለማወቅ ያቅለሸልሻል - በጣም።

 

ህም። ልክን አለማወቅ ያቅለሸልሻል - በጣም።
 የዛሬ አራት ዓመት ዬተፃፈ ነው። አገር ምድሩ ተደማሪ ሳለ። ያን ጊዜ አማራ ተደራጄ ኡኡታ ነበር። እንኳንስ ራሱን መከላከል የሚያስችል ኃይል ማደራጀት። አይታሰብ ነበር። አቶ ውብሸት ገርሟቸው ፁሁፍን አጋሪው አሉኝ። እኔም ይህን ያህል ይመስጣል ብዬ አላሰብኩም። ሳነበው ግን ተገረምኩኝ። 24/06/024 ……?እንሆ
 
ሠራዊት ወታደራዊ ከሆነ ከአዛዡ ትዕዛዝ ውትልፍ የለም። እና ሲቢሉ ምን ልሁን ብሎ ይሆን ዓይንህ አፍህ ላይ ነው ያለ ሲባል የሚቀበለው?
 
አገር የፈታው ነገር፣ አቅም ዋጮው ጉዳይ ሁሉም ለማልያ ፍቅር በሚካሄድ ቡጢ መሽቶ ይነጋል፣ ነግቶ ይመሻል። ተቋማዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ሲገባ በግለሰብ ዝና እና ወርቀዘቦ ሌት ተቀን መታመስ።
 
አንድ ሰው ስለራሱ ሲፅፍ የፈለገውን ይፃፍ። መሪዬ ይበል፣ ዓይኔ ይበል፣ ምርኩዜ ይበል ወዘተረፈ። " መሪያችን " ብሎ ፕሮፖጋንዲስት መሆን አይችልም።
መሪ አለን የማንል ሰዎች እንዳለን ማወቅ ይገባል። በተጨማሪም ለእሱ መሪ የሆነው ነፍስ ለሌላው ላይሆን ይችላል። መሪ አለን የሚሉትም ቢሆኑ የራሳቸው ምርጫ ሊጠበቅላቸው ይገባል።
በሌላው ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር የሚሹ ነፍሶች ዝልብ ሰብዕና ጎርፍ ይሆንብኛል። እንደዚህ ያሉ የሰውን ልክ የማያውቁ መብት ዳጭ አለሎ ሰብዕናዎች ስለሚያቅለሸልሹኝ በበዛ ሁኔታ ታግሼ መልዕክቴ ካልገባቸው ማሰናበት ተፈጥሯዊ መብቴ ነው
መሪነት ገብያ ተሂዶ የሚሸመት ሸቀጥ አይደለም። መሪነት አይሸጥም አይለወጥም። መሪነት ስክነት - ፀጋ - ቅብዐ - ልቅና - ልዕልና - ጥበብ - ክህሎት - መሆን - ኪዳን - መታመን - ዝቅ ማለት - ተመክሮ - በችግር መገኜት ተጠያቂነትን ፈቅዶ መውሰድ - ርህርህና - ፍትኃዊነት መርኃዊነት - ይቅርታዊነት ወዘተ ነው።
 
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሸፍጥ፣ ሴራ፣ ገዳይነት፣ ግላዊነት፣ ከሳሽነት፣ ቀውስ አደራጅነት፣ ካህዲነት፣ ኢጎዊነት ብዙ ብዙ እክል ነው ያለው።
መሪ አለኝ የእኔ የሚሉ ባከብራቸውም " መሪያችን " ብለው በእኔ መንፈስ ላይ ሊጭኑ ግን አይችሉም፣ አይፈቀድላቸውም። ኢትዮጵያ እራሷ እጁም አንደበቱም ከደም የፀዳ ስኩን መሪ እንደ እኔው ናፋቂናት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ሰውኛ መሪ ይናፍቀኛል።
20.06.2020

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።