ባለ #ቄንጠኛ ባለጎሏ ቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ እና ጀርመን በፋራንክፈርት አማይን የምድብ A ጨዋታቸውን በአቻ ነጥብ ከውነዋል።
ባለ #ቄንጠኛ ባለጎሏ ቅድስት አገር ሲዊዘርላንድ እና ጀርመን በፋራንክፈርት አማይን የምድብ A ጨዋታቸውን በአቻ ነጥብ ከውነዋል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ"።
ጀርመኖችን ያስደነገጠ አንድ ተጨማሪ ጎልም ተሰርዞ እንጂ ጎሏ ከመረብ ጋር ተዋህዳ ነበር በሲዊዝሻ በኩል።
ሲዊዞች በአጭር ቅብብል፤ በቲም ወርክ ኮኦርድኔሽን ዘና ብለው ነበር የተጫወቱት። ጀርመኖች በጨዋታው መግቢያ ላይ ጎል ስለገባባቸው የመዛል ስሜት ታይቶባቸዋል። ይህ ደግሞ ልማዳቸው ነው። የመጨረሻዋም የመቅናት ያህል ነው እንጂ #ዝለው ነበር። እርግጥ ጎሏ ነፍስ ያላት ነበረች። አስደሳች አገባብ ነበር።
ሲዊዝ ውስጥ ያልተማረ አይገኝም። እያንዳንዱ ልጅ ተምሮ #ሙያ ሊኖረው ግድ ነው። ቅድሚያ ለቀለም ትምህርት። ቅድሚያ ለሙያ ሥልጠና በኽረ መርህ ነው። ታለንት እንደ አጀንዳ ብዙም አይታይም በስሱ ነው። ብዙወቹ ሄደው የሚወዳደሩት ጀርመን ነው። ሙዚቀኛ ሉካ ሄኒ፤ ሙዚቀኛ ፓትሪስ ኤንግል በጀርመን ተወዳድረው ነው አሸንፈው ከዕውቅ የሙዚቀኛ ሊስት ውስጥ የገቡት።
የጀርመን ቲም መፈናፈኛ አጥተው በረጅም ምት ሞካክረው ነበር። በጀርመን የጨዋታ ሂደት ጊዜው እያለቀ ሲመጣ ወደ ቅጣት ምት ስልት ይገባሉ ብዬ ሰግቼ ነበር። አልሞከሩትም። ምናልባት በቲሙ ሙለር ስላልነበረ ሊሆን ይችላል። የጥንቱ የሆላንድ ዓይን ተጨዋችም በኋላ የባዬር ሙንሽን ይህቺ የቅጣት ምት ስልት ነበረችበት።
የሆነ ሆኖ እኔ ሲዊዚሻ አቅሟን በልጆቿ ያሳዬችበት #ደግ አጋጣሚ ነው ብዬ አምናለሁ። ለአውሮፓም፤ ለዓለም ዋንጫም ማጣሪያውን ስታልፍ የሚወርፏት የስፖርት ተንታኞች ስለነበሩ። በሌላ በኩል ሲዊዘርላንድ እኔ ከመጣሁ ካዬኋቸው አሰልጣኞች ቢሆኑ ብዬ ስመኛቸው የነበሩት ናቸው የሆኑት። ይህም ሌላው ዕድል ነው። በተጨማሪም በረኛው ጥንቁቅ እና አስተዋይ ነው።
#የትናንቱ የሮማንያ እና የቤልጀም ጨዋታ።
ትናንት ሮማንያ እና ቤልጀም ጨዋታ ነበራቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ ያዬሁት የሩማንያ ቡድን እንደ ጣሊያን ጉልበታም ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ቤልጀሞች ከነበራቸው ብቃት አነስ ቢሉም ሁለት ለምንም በሆነ ውጤት ሮማንያን በለቱ ጨዋታ ረተዋል። ቢጫ ለባሾች ሮማንያወች አይቻቸው ስለማላውቅ በመደነቅ ነበር ስከታተላቸው ዬነበረው። ቀላል የማይባል ደጋፊም ነበራቸው። እነሱም ቀላል አይደሉም።
ክብረቶቼ ደህና አምሹልኝ። ሲዊዚሻ ለቀጣዩ ጨዋታ ታጭታለች። ይቅናልኝ ቅኒትን። ዕውነተኛ ሰባዕዊነት የሚሰማት ጭምት ገዳማዊ በዐት ሲዊዝሻዬ ይቅናሽ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/06/024
ኳስ የፍቅር እናት ኑሪልን። አሜን።
google.com
Schweiz gegen Deutschland
Spielinformationen, Neuigkeiten und mehr
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ