ይህ ቤተ - ሰለሞን #የድውያን #ማገገሚያ #ጣቢያ የለውም።
ይህ ቤተ - ሰለሞን #የድውያን #ማገገሚያ #ጣቢያ የለውም። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" በውነቱ ለዛሬ የሚሆነኝን ፈፅሜ ነበር። ነገር ግን መዳኛ የሌላቸው ነፍሳት እዬመጡ ቤቱን ያውኩታል። እዚህ እኮ ጎንድ ተክለኃይማኖት #መጠመቂያም የለም ወፈፍ ለሚያደርጋቸው። የአማኑኤል #ማገገሚያ ጣቢያ የለም። ቢያውቁት ቢረዱት የሃሳብ አቅም ያለው በትህትና፤ በአክብሮት በጥሞና የሚያነብበት፤ የሚያዳምጥበት፤ ሃሳቡን አቅርቦ የሚሞግትበት ነው። የውቂ ደብልቂ፤ የቅጽበተኞች መጋለቢያ አይደለም ቤቱ። ይህን ያሰኜው ሌላ ቦታ መፈለግ ነው ያለበት። ኢትዮጵያን #የተፀዬፈ ሰብዕና ይህ ቤት ልኩ አይደለም። ከዘለለው ጋር የማልዘል፤ ከጎረፈው ጋር የማልጎርፍ መሆኔ ይታወቃል። #መልካምነት ፤ #ቸርነት ሲነሱ ያንገፈግፋቸዋል። ኢትዮጵያ ስትነሳ ደማቸው #ይንተከተካል ። ጎርፍ አምጥቶ ደለል የሠረባት ሁሉ እዬመጣ ልቤን ያወልቃል። እንዲያውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማም እንደ ጠላት ያዩታል። #ይድከሙ - አይችሉም። #ይኳትኑ - #ነኩተው ይቀራሉ። የአረብ ስፕሪንግ ተነሳ ኢንፖርት ኤክስፖርት ህግ ይግዛው፤ ፓኪሳትን ቤተ -:መንግሥት ንቅናቄው መጣ እኛም እንቀላቀለው የተነሱበትን የማያውቁ፦ ሰው በገነባው አቅም ተንጠላጥለው እንደ #ፌንጣ እዬዘለሉ ባጉም ባጉም። "ከበሮ በሰው እጅ" ሆኖ የፖለቲካ ድርጅቱም ተመሰረተ ጨዋታው ፈረሰ ቅሉ ተሰበረ አሟራው በረረ ሆኖ አዬን። ስንት አቅም የፈሰሰበት። አቅልም አደብም ጠፍቶ በምኞት ሰረገላ የፋንታዚ ልዑል ተሁኖ መከራን ማበራከት። አዬ የአማራ ህዝብ ቻል የተባለው ገመና እኮ ወዘተረፈ ነው። ኩፍትርትር ያለ...