ልጥፎች

መሪነት መፍትሄ አመንጭነት ነው።

 መሪነት መፍትሄ አመንጭነት ነው። #አጤ #ሽዋስ እንዴት አደረ ይሆን? ዬአጣዬ መከራ ከውስጡ ያልገባ የአመራር ሂደት ያ ሁሉ መከራ አልበቃውም፦ የአጣዬ የሽዋ ሮቢት ያ ሁሉ ስቃይ ተዘሎ አሁን ደግሞ እንደ ዳንቴል #በእጅ #በተሠራ #መከራ #አሳሩን እያዬ ነው።  አዝናለሁ ሕዝባችን እንዲህ ከመከራ ላይ መከራ ተሸከም ተብሎ ፍዳውን ማዬቱ። ደብረብርኃን መጠለያ ያሉት ወገኖቻችን ስቃይ እራሱ #ሐዋርያ በሆነ ነበር።  መጠለያ ላሉትም #ተስፋቸውን ሙልጭ አድርጎ #የዘረፈ // #ስጋትን #አጭቶ ያነገሠ ጉግስ ነው እያዬሁት ያለሁት። ልብ ይስጣቸው ለመሪወቹ። አሜን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"  ሥርጉትሻ 2024/07/24

#ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል።

  #ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል። ቢያንስ ለአማራ እናት #ዕንባ መቆም እንዴት ይሳናል? ባልተለመደ ሁኔታ #በእናቶች ላይ የሚፈፀመው፤ በግራጫማ ፀጉር ባበቀሉ ወገኖች ላይ ያዬሁት የእንብርክክ ስቃይ፤ የከፋም እርምጃም ሰማሁ ለዚህ ነው ሙሉ ቅኔው ጎጃም ከሐምሌ 5 ጀምሮ መኖሩን የሰጠው? ለዚህ ነው? ለጭካኔ? ከጨካኝ ተሽሎ መገኜት እንዴት አይቻልም? ሙሉ የጦርነቱ አቅም የፈሰሰው እኮ ቅኔው ጎጃም ላይ ነው።  የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አገዛዝ የውጭ አገር ቅኝ ገዢ እስኪመስለኝ ድረስ #በእልህ ማቱን ያፈሰሰው በዚህ ጨዋ ህዝብ ላይ ነው። ከመጀመሪያዋ ከሐምሌ 5ቱ የተጋድሎ ንቅናቄ ጀምሮ #በጠና አቅም እና #አቋም ሳይሽረከረክ፦ ለመደለያ ሳያድር የትግሉን መንፈስ ያስቀጠለ ጀግና ህዝብ እንዴት በተስፋወቹ ይቀጣ? ግፍ አይሆንም? አልቅሻለሁ። የት ይሂድ ይህ ህዝብ? ምርጫ አለውን? ማስተማር መንገር ማሳመን እያለ እንደዛ? ነገስ??? ሥርጉ2024/07/24

ጎፋን ለምትደግፋ ጥሩወች።

ምስል
 

ብዙ ያልተነገረ ታሪክ እዚህ ቤት አለ! #italy#addisababa#gizachewashagrie#marakiweg ዕንባዬን መቆጠር አልቻልኩም መቀጠልም አልቻልኩም። ሼር ግን አደርገዋለሁ።

ምስል

ልቅና በልዕልና

ምስል
·        https://www.lora.ch/programm/alle-sendungen?list=Tsegaye ·        https://www.facebook.com/sergute.selassie/ ·        https://sergute.blogspot.com/2021/02/blog-post.html?spref=tw ·         

የ200 ብር ቤት ኪራይ መክፈል አቅቶኝ ነበር | ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ ክፍል 1 | Beyond the screen | ...

ምስል

አዲስ ፈተና ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ።

ምስል
  አዲስ ፈተና ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በዚህ የጠለፋ እና የእገታ ክስተት ውሳኔያቸው ምን ሊሆን እንደሚችል እጠብቃለሁኝ። በእገታ፦ ከእጃችሁ የገቡት አርበኛ ኮነሬል አሰግድን እንደምን እንደሚይዟቸው አያለሁኝ። የቀደምቶችን ታሪክ ውስጥ የእኔ አሻራ አለበት ብለው በብዙ ሁኔታ አዳዲስ ሁነቶችን አያለሁ።   ለምሳሌ ከሥሙ ጀምሮ ጨፍላቂ የሆነው ዓድዋድዋ " #ዜሮ ዜሮ" በዚህ ላይ ጽፌበታለሁ ተዚህ ቀደም። የዓድዋ ድል መታሰቢያ ምን እና ምን እንደሆነ፤ የህወኃት እና የእርስወ መንግሥት ጦርነት የአገልግል የውሎገብ የጦር ዘመቻወት ከአንገተወት ላይ ስካርፕ እንደ ህወሃት ጣል አድርገው ብዙ በጣም ብዙ ነገሮችን ማንሳት እችላለሁኝ።   እምዬ ሚኒሊክ ከእጃቸው የገቡትን የጣሊያን መኮንኖች እንደምን እንደያዟቸው ያውቃሉ። ያውም #በምርኮ ። ከንጉሦች ንጉሥ ከእምዬ ሚኒሊክ እስኪ ይማሩ። ይህ #ጠለፋ ነው። ይህ እገታ ነው። ፊትለፊት ተጋጥማችሁ በተመዘገብ የድል ስኬት የተገኜ ዕድል አይደለም። #ምርኮም ወይንም #እጅ #መስጠትም አይደለም። ይህን ተቆራርጦ ከተለቀቀው ቃለ ምልልስ ደጋግሜ ሳዳምጥ ያገኜሁት ግንዛቤ ነው። ዕድሉ #አጤ ስልክ ያመጣው ጣጣ ነው።   የሆነ ሆኖ መሪነት በቀል አይደለም። መሪነት #ቂመኝነት አይደለም። መሪነት የአማራን ህዝብ እና ቱሩፋቶችን መሪወቹን፤ #ተምሳሌወችን #ማቃለል ፦ #ማጣጣል አይደለም። መሪነት በእጅ የገባን ዕድል በቅጡ መያዝ ነው። ማንገላታት፤ ዱላ፤ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ለመዋል መጣር፦ #ማዋረድ የሚገባ አይደለም። የሰው ልጅ ፈጣሪ ቤተ መቅደሱ አድርጎ የፈጠረው ክቡር ፍጥረት ነው። ዕምነት ሃይማኖት ክብርን ሲቀበሉ ፍጥረቱን

አደራው ለድንግል ነው።

ምስል
  አደራው ለድንግል ነው። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም።    መጠንቀቅ በኽረ ዲስፒሊኑ ይመስለኛል ለወቶአደር። አሳሳቢ ነው። እጅግም ከባድ ነው። አደራው ለድንግል ነው።    ያው ሲጨንቅ፤ ሲቸግር ለላይኛው ነው አቤቱታው። ሲንገላቱ ነበር የሰነበቱት። በራስ አካል ያን ያህል መኖሪያ ቤት ድረስ??? ዝምታዬ አዛዦች ወዘተረፈ ስለሆኑ ነው።    ይህን ማድረጌ ደግሞ ይጠቅማል። ላም እረኛ ምን አለ ቢደመጥ መልካም ነበር። የዛሬ 3 ዓመት ከእስር ቤት ሲወጣ ፋኖን እመራለሁ እንዳትል ብዬ ጽፌ ነበር። የታዘብኩት ስለነበረ።    እኔ እኮ ስልክ የለኝም። አልደዋወልም። ካለ ስልክ መኖር ይቻላል። ሦስት ዓመቱ ነው እዬከፈልኩበት ግን ሶኬቱ ተነቅሎ ተቀምጧል። የማይታይ የሁለት ሰወች #ስውር የባለቤትነት ሁኔታ ስለተገኜ።  ቢከሰሱ ሲዊዝ ቀልድ የለም። ግን እኔ ልጎዳ። መካሰስም በእኔ ሕይወት? እእ። አልከሰስኩም።    በተፈጥሮዬም ስልክ አልወድም። እምታወቀውም በዚህ ነው። ስልክ አታነሳም።። እንኳንስ ግንባር ላይ። አሁንም ልብ ይስጣችሁ። አሜን።    እመቤቴ አደራሽን ክፋ እንዳታሰሚን።    "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ 23/07/024

ሃሳብ መኖርን ያበጄ የሰማይ ፀጋ ነው። ሃሳብን ማደራጀት ከዕለት መኖር ይነሳል። የሰው ልጅ ሚስጢር ነውና። እኛን እንሁን። የአላዛሯ ኢትዮጵያ ልጆች በሚስጥራችን ልክ እንሁን። ልመና።

ምስል
  ሃሳብ መኖርን ያበጄ የሰማይ ፀጋ ነው። ሃሳብን ማደራጀት ከዕለት መኖር ይነሳል። የሰው ልጅ ሚስጢር ነውና። እኛን እንሁን።  የአላዛሯ ኢትዮጵያ ልጆች በሚስጥራችን ልክ እንሁን።  ልመና።    "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"     እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ስለምን አምላኳን ፈጣሪዋን "ከሰይጣን ጋር ታረቅ ብላ ሞገተች?" ይህ ጥሪያዋ ገድሏን ካነበብኩ ጊዜ ጀምሮ ይጠራኛል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ውስጧ እራስ እግሩ ዕንቁ። ግን አፈሰስነው።    ተቋም ሲፈጠር፤ ወይንም የተፈጠረ ተቋምን ለመምራት #የሃሳብ #ጥራት እና #ብቃት ይጠይቃል። ለመኖሩ ሃሳብ የሌለው ማለቴ ሃሳቡ ሊኖር ይችላል ግን ያልተደራጄ፤ አዋኪ፤ #ገርባባ ፤ ተርገብጋቢ፤ #ቅጽበታዊ ፤ የሚያረገርግ፤ ተጣዳፊ፤ ተጣጅ፤ አማሽ ከሆነ ባክኖ ይቀራል። በመኖር ውስጥ ዙሪያ ገብ ፈተናወችን ለማለፍ ስለሚያዳግተው። ተሸናፊም ይሆናል።    የኢትዮጵያ ተቋማት የማይፀኑትም ጎርፍ ላይ ይነሳሉ፦ ማዕበል ሲመጣ መቋቋም ስለሚሳናቸው ምራቅ ይሆናሉ። ወይንም የሳሙና አረፋ።   አስቦ የሚነሳ መኖር ግን ከራሱ አልፎ የሚሊዮኖች #መዳኛ መሠረት ይሆናል። በብዙ ማይል ርቀት ውስጥ ሆነን ያ የተደራጀ ሃሳብ ይዞ የተነሳ ሰብ ዕይታ የታመመውን፤ የተንገላታውን፤ መተንፈሻ፦ መፈናፈኛ ያጣውን መንፈሳችን ይፈውሰዋል። #ያጽናናዋል ። #አይዟችሁ ይለናል።   የሰው ልጅ #ህሊና በምግብ እና #በመጠጥ ብቻ አይኖርም። የሰው ህሊና #በጥሩ መንፈስ መኖርን ይሻል። ይመኛል። ይፈልጋል። በፈለገ ርቀት ይሆን ተመሳሳይ መመሰጥ ያላቸው ሰብዕናወች ፍላጎታቸውን ሲያገኙ ውስጣቸውን ይሰጣሉ። #ሚስጢራቸውን ያጋራሉ።  የጨመቱም ቢሆኑ "በይበቃኛል" የሚኖሩ