ልጥፎች

"የአማርኛ ሳይንስ ኮሌጅ መቋቋም" Lij Elias University Addis Ababa, Ethiopia

  "የአማርኛ ሳይንስ ኮሌጅ መቋቋም"   "ሕልም እውን ሆነ ዛሬ አንድ አማርኛ የሳይንስ ኮሌጅ የመመስረት ህልም በመጨረሻ እውን ሆኖ በመገኘቱ አስደሳች ጉዞ መጀመሩን አመላካች ነው። በአንድ ወቅት ራእይ የነበረው ነገር አሁን የዕውቀትና የእድል መበራከት ሆኗል። ኮሌጁ በታህሳስ 2017 ዓ.ም በአውሮራ ኮሎራዶ ዋና ቢሮው ሲከፈት የህልምና የቁርጠኝነት ሃይል ማረጋገጫ ሆኖ ቆሟል። በዓይነቱ ልዩ የሆነ የትምህርት ተሞክሮ   አማርኛ ሳይንስ ኮሌጅ አማርኛ ተናጋሪውን እና ከዚያ ባሻገር ያለውን ማህበረሰብ ሁሉ ለማገልገል የተነደፈ አደረጃጀት ያለው ተቋም ነው። ኮሌጁ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በመስጠት የቋንቋ መሰናክሎችን ድልድይ የሚያደርግና ለብዙዎች ሳይንሳዊ ዳሰሳ በር የሚከፍት ጠንካራ የትምህርት መሳሪያ ለመፍጠር ጥረት ያደርጋል።   ቋንቋና ሳይንስን መቀበል   ኮሌጁ በመላው የሳይንስ ዘርፍ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ያቀርባል። ሁሉም በአማርኛ ናቸው። ይህ ልዩ አቀራረብ የአማርኛ ቋንቋን ጠብቆ ለማቆየትና ለማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ተማሪዎች ውስብስብ የሆኑ ሳይንሳዊ ጽንሰ ሐሳቦችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ያደርጋል። በአማርኛ መማር የሚያስገኛቸው ጥቅሞች   ባህላዊ ጥበቃ - ኮሌጁ በአማርኛ በማስተማር የኢትዮጵያንና የኤርትራን ማህበረሰብ ሀብታም ባህላዊ ቅርሶች ጠብቆ ለማቆየት ያግዛል። የተሻለ ግንዛቤ፦ ተማሪዎች በዋነኛ ቋንቋቸው ሲማሩ ሳይንሳዊ ጽንሰ ሐሳቦችን በፍጥነትና በደንብ መረዳታቸው አይቀርም። ማህበረሰብ ኃይል - በአማርኛ ትምህርት መስጠት ማህበረሰቡን ኃይል ይሰጣል። ተጨማሪ የአማርኛ ተናጋሪዎች በሳይንስ ሙያ እንዲሰሩ ያበረታታል።   የወደፊቱን ጊዜ የተመለከተ ራእይ   የአማርኛ ሳይንስ ኮሌጅ ምሥረ...

#የገለበጠም #የተገለበጠም #የለም! #በሞቴ መንግስት መገልበጥ #አይሰልችህና #ሞካክረው። እኛም እንይ ………

ምስል
  #የገለበጠም #የተገለበጠም #የለም ! #በሞቴ መንግስት መገልበጥ #አይሰልችህና #ሞካክረው ። እኛም እንይ ………   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት ሰነበታችሁ ማህበረ ቅንነት? እንዴት አላችሁልኝ። ውጭ የምትኖሩ ወገኖቼ ዓውደ- ዓመቱ እንዴት ይዟችኋል? ጥሞና መልካም ነገር ነው። ከቅንነት፤ ለመልካምነት ከታሰበ። መታደልም ነው።   ዛሬ ዕለቱን በአቶ (በሃጂ) ጃዋር መሃመድ ዙሪያ የግል ዕይታዬን ላጋራ ወደድኩኝ። ፁሁፋ ሊረዝም ይችላል። ለብሎጌም ጭምር ስለምሰራም። በተጨማሪም የምዕራፍ ፲፬ መከወኛ ፁሁፌም ስለሆነ።   የአቶ (የሃጂ) ጃዋር ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱ ከምን አንፃር ነው? 1) የማህበረ ኦነግ የቤተ - መንግሥት ቆይታ እንዳያጥር ከመስጋት። 2) የማህበረ ኦነግ በትረ ሥልጣን ከተናደ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ። #ሁለቱ ሃሳቦች መነሻወች መንታ ፍላጎት አላቸው። 1) አገር እናድን ጥሪ። ይህ ለውጥ #ፈላጊነትን ያሳያል። ለውጡ ግን ወደ አመራር ሽግሽግ ዝንባሌ ያለው ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ። 2) ምንም ቢሆን በኦሮሞ ሊቃናት የበላይነት የምትመራ ኢትዮጵያ ለመሪው አካል #ጥገናዊ አጥሚት አዘጋጅተን እናድነውም ዓይነት ነው።    #ፖለቲከኛ ።   …… ለዛውም ፕሮፌሽናል ፖለቲከኛ የፍላጎቱን አቅጣጫ መንታ መንገድ ላይ ሊገትር አይገባም ባይ ነኝ። A. B. C. D ፈተና ላይ እራስን አስቀምጦ የፍላጎት አቅጣጫን ጥርት ባለ አቋም፤ ጥርት ባለ ውሳኔ ላይ መነሳት ያስፈልጋል። አገር እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣብያ አይደለችም እና። ኤንም፦ ቢንም፥ ሲንም፥ ዲንም፥ ልሁን በትውልድ ላይ መፍረድ ይሆናል።    #አቶ (ሃጂ) ጃዋር መሐመድ።   በቅጽበት ከተከሰቱ ጥቂት ...

አስከሬን መሃል ስፈልገው ነበር ከዛ የእሱን ጫማ...በጦርነት የተፈተነው አነጋጋሪው የፍቅር ታሪክ!ለመለያየት ብዙ ...

ምስል

'ዶቃ' ሙሉ ፊልም | DOKA | Full New Ethiopian Movie 2024 ገቢው ለመቅዶንያ ህንጻ ግንባታ የ...

ምስል
  ምን ቃል ተገኝቶ ልግለፀው። ሦስት ጊዜ አየሁት። ሐዋርያ ልበለውን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።

የርቀት ፍቅር ከባድ ነበር!! አውሮፕላን እንደ አውቶብስ ነው የምጠቀመው!! #amlesetmuchie #amleset ...

ምስል

Addisu Media በኢትዮጵያ ሰላምና እርቅ ጥያቄከዶ/ሸዋፈራሁ ኩራቱ ጋር Tuesday Dec 24, 2024

ምስል

ምስጋና። Danke schön. Dankbarkeit ist auch Aufrichtigkeit. Dankbarkeit scha...

ምስል

"ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ" BBC እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው።

    እኔ የሚያስፈራኝ ይህ ነው። ክፋ ሃሳብን ያነገቡ ሰብእናወች ዓለማችን የጥፋት እና የመከራ በማድረግ ፈሪ ትውልድ ይሻሉ። የጭካኔው ዓይነት ይዘገንናል። ይህን ጭካኔ የሚገታ ወይንም የሚመክት ተቋም አለማችን ምን አላት? የሚያስፈራኝም ይሄ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c23vezjzgzdo   "ኒው ዮርክ ባቡር ጣቢያ ውስጥ አንዲት ሴት በእሣት ተቃጥላ መገደሏ ተሰማ"   23 ታህሳስ 2024, 07:49 EAT "በኒው ዮርክ አንዲት ሴት ባቡር ጣቢያ ውስጥ በእሣት ተቃጥላ መገደሏን ተከትሎ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል። የፖሊስ ኮሚሽነር ጄሲካ ቲስክ እሑድ ዕለት የተፈፀመውን ጥቃት "አንድ ሰው ሌላ ሰው ላይ ከሚፈፅማቸው እጅግ ዘግናኝ ወንጀለኞች መካከል አንዱ" ሲሉ ገልፀውታል። ኮሚሽነሯ እንደገለፁት የተገደለችው ግለሰብ 'ስቴሺነሪ ኤፍ' ከተባለው ጣቢያ ወደ ብሩክሊን እያቀናች ሳለ ነው አንድ ሰው መጥቶ በእሣት መለኮሻ (ላይተር) ልብሷን ያቀጣጠለው። ግለሰቧ እዚያው ባቡር ጣቢያ ውስጥ ስትሞት ተጠርጣሪው በተማሪዎች ጥቆማ መሠረት ሌላ ባቡር ሲሳፈር በቁጥጥር ሥር ውሏል። ፖሊስ እንዳለው ስሟ ያልተጠቀሰው ሴት እሑድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ጥዋት 1፡30 ገደማ ነው ባቡር ስትሳፈር አንድ ሰው የተጠጋት። ከጥቃቱ በፊት በሁለቱ መካከል ምንም ዓይነት ንግግር አልነበረም ያለው ፖሊስ ሁለቱ ሰዎች ይተዋወቃሉ ብሎ እንደማያምን አስታውቋል። በባቡር ጣቢያ ያሉ የፖሊስ መኮንኖች እሣቱን ለማጥፋት ሲረባረቡ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብ ከሥፍራው ሮጦ ማምለጡ ተሰምቷል። "በባቡር ጣቢያው በላይኛው ክፍል ላይ የነበሩት ፖሊሶች በሽታ እና በጭስ አማካይነት እሣት መነ...

"በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ" BBC እኔ ደግሞ ... የዚህ ሥርአት #በቀለኝነት እኮ #የዲያቢሎስ ዓይነት ነው።

    የዚህ ሥርአት #በቀለኝነት እኮ #የዲያቢሎስ ዓይነት ነው። በእጃቸው ያሉ እስረኞችን እንዲህ እንዲሰቃዩ ማድረግ #አረማዊነት ነው። ሃይማኖት አለኝ የሚል ስርዓት በእነኝህ የአማራ ሊቃናት ላይ የወሰደው፤ በመውሰድ ላይ ያለው በቀላዊ እርምጃ ነገን #ያከስለዋል ። ዛሬንም #ቃሬዛ ላይ ያውለዋል። ከዚህ ቀደምም የአማራ ባንክ ትጉህ ሰራተኛ በቁሙ እስር ቤት ገብቶ አስከሬኑን ነው ተረከቡ የተባለው። የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና አሁንም የሚፈለገው ይህ ነው።    በየትኛውም ሁኔታ የሚደረጉ የህልውና ተጋድሎወች በብርቱ ጥንቃቄ ሊያደርጉበት የሚገባውም በዚህ መሰል አመክንዮ ላይ ያስተዋለ የፖለቲካ አቅም መፍጠር ሲቻል ብቻ ነው። በድንገቴ ግጥግጦሽ ስልጣኑን የተረከበው ማህበረ ኦነግ በአዲስ ዘይቤ መምጣቱ አይቀሬ ነው። የአማራ ቅን ህዝብ አቅሙን ቆጥቦ በስርዓት አቅሙን የማስተዳደር ግዴታ አለበት። የአማራ ህዝብ #መታመኑን ከእነ ሙሉ አቅሙ አስረክቦ ነው "ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቁሞ ማውረድ ይቸግራል" እንደሚባለው የሆነው።    የአማራ ህዝብ አመድ አፋሽ ነው። ሙሉ ድምፁን ሰጥቶ በወዘተረፈ የበቀል ዓይነት ሙሉ ስድስት አመት ተቀጠቀጠ። እንዴት ህመም ላይ ባለ ሰብዕና ይጨከናል? አንዴት? ለምንስ????    ይህ አስተምህሮ ነገንም በማስተዋል ማደራጀት እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው። እየዳሁ ያሉ አመክንዮወችን አያለሁኝ። ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቁ። በዳግም "በኢትዮጵያ ሱሴ" መደናገር እንዳይኖር ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ማህበረ ኦነግ መንፈሳቸው የሚቀዳው ከአንድ ነውና። አይደለም የይዘት የቅርጽ ልዩነት የላቸውምና። አህቲ ናቸው። እየገዙም የማይጠግቡ። እየገዙም የማይረኩ። ይሉኝታየሚባል ያልሰራላቸው።   ...