21.12.2019 የተጻፈ ነው። የህልውና ትግል ምንድን ነው?
የህልውና ትግል ምንድን ነው?
ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ የህልውና ተጋድሎ የኦክስጅን ተጋድሎ ነው። ለዚህም ነው አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ የአማራን የህልውና ተጋድሎ ብሎ መጥራት ሳይችል ቀርቶ ጣር የሆነበት። በዘመነ ግንቦት ሰባት የነፃነት ኃይሉ በሚል ተተካ። በዛ ስንት አቅም ፈሰሰ?
ደጉ ሳተናው ላይ በሥሜ ሥርጉተ ሥላሴ ተብሎ ቢገባ የአመክንዮ ሙግቱን ማንበብ ይቻላል።
ቆይቶ የአማራ የህልውና ህዝባዊ ተጋድሎን የወጣት ብቻ አድርጎ ሸራርፎ ለማቅረብ ተሞከረ፣ ህዝባዊው ተጋድሎውን የአመክንዮ፣ የዓላማ፣ የግብ ዝበት እንዲኖርበት ለማድረግ።
ይህም ብቻ አይደለም ፋኖ በሚልም ተተካ። ይህም በራሱ እራሱን የቻለ ተደሞ ይጠይቃል።
የዚህ ሁሉ መሰረቱ ግን ቅርሱ፣ ትውፊቱ፣ ታራኩ፣ ባህሉ፣ ቋንቋው ወጉ፣ ልማዱ፣ ጥበቡ ተዘርፎ ማህበረሰቡ እንዲፋቅ የተፈለገበት ምክንት ታሪክ የሚሰራው በዛሬ ጊዜ ብቻ ስለሆነ ተዝቆ የማያልቀው ታሪክ ሰሪ የአማራ ህዝብ እንዳሰቡት ከጠፋ ወራሹ ጉልበተኛው ይሆናል።
ለዚህም ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አንበልነት ማህበረሰቡም ቋንቋውም ክህደት የተፈፀመበት። ይህን እያዬ የአማራ ልጅ ለነፍሱ ለእስትንፋሱ መጥፋት ጉዳይ አልሰጠው ብሎ ማቄን ጨርቄን የሚለው።
የተጋድሎው ሥረ ነገር ኦክስጅን መሆኑን ይህን ከልብ ሆኖ ያዳመጠ አማራዊ መንፈስ ወጀብ፣ አውሎ፣ ጦሮ ቀርቶ ጦርነት አይፈታውም። ይህን ተጋድሎ ያመነበት አካል አይፍረከረክም።
ለተጋድሎው ታማኝ የሆነ መንፈስ ዛሬ ላይ ለማግኜት ይቸግራል። አቶ ጃዋር መሃመድ ለተነሳበት ዓላማ ግቡን በማሳካት መንበር ላይ ሲቀመጥ የአማራ ተጋድሎ መሪዎቹ ግን ምን ላይ እንዳሉ ማስተዋል ይመልሰው?
ኦክስጅን ያጣ ወይንም እንዲያጣ በሁሉም ዘርፍ ተሰቅዞ ያለ ማህበረሰብ እዬመራህ፣ እያደራጀህ፣ እያነቃህ በአቋራጭ እንዲህ ስለሆነ እንዲያ ስለሆነ ብለህ ያመነህን መንፈስ በትነህ ክደህ አቅሙን ቅጥ መጠን አሳጥተህ ቃልህን በልተህ አዲስ መንገድ ትጀምራለህ። ወይም እረፍት ያስፈልገኛል ትላለህ። በዬደቂቃው አማራዊ አቅም ግን ጣር ላይ ነው።
ይህም ብቻ አይደለም የአንተን አቅም ለመስበር ንጉሥ እስከ ሠራዊቱ የተሰለፈበት የሞት ዓዋጅ ላይ ሆነህ፣ የሞት ሲባል በሁሉም መስክ ቅብረት የታወጀበት ማህበረሰብ ቤተኛ ሆነህ መንደርህ ላይ፣ ወይ ዕምነትህ ላይ፣ ወይ ፆታህ ላይ፣ ወይ ሙያህ ላይ አዘጋጅተው በሚፈጥሩት መሰናክል ተጠልፈህ ዋናውን የኦክስጅን ቧንቧህን ነቅለህ እነሱ ባዘግጁልህ መረብ ተጠልፈህ ትወድቃለህ።
እነሱ አንተ እራስህ እምትፈርስበትን እስክሪብት ይፅፋልኃል አንተ ካራክተሩን አሳምረህ ትጫወትላቸዋለህ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
እና ዕውን ለአንተ ኦክስጅን ያስፈልጋህልን?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ